ሚያዚያ 04 ቀን 2008 ዓ.ም.ዜና (April 12, 2016 NEWS)
#በኢትንተርኔት አገልግሎት ኢትዮጵያ ከመጨረሻዎቹ አገሮች ተርታ ተመደበች፤ የነበሩትንም አገልግሎቶች ስሞኑን ወያኔ አፈነ
#በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤት አካባቢ የአልኮል መጠጥና ሱስ የሚያስይዙ ጎጅ ባህሎች እየተስፋፉ ነው ተባለ
#በወያኔ ጦር ውስጥ መኮንኖች ተይዘው ታሰሩ
#ቦኮሃራም በአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቀምባቸው ህጻናት ቁጥር ጨመረ ተባለ
#በብሩንዲ ያልታወቁ ሰዎች በእሩምታ ተኩስ አምስት ሰዎችን ገድሉ ከሰባት በላይ አቆሰሉ
#የደቡብ ሱዳን የጸጥታ ኃይሎች 16 የአማጽያን አባላትን ይዘው አሰሩ ተባለ
#የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሊቢያ ከአንድነት መንግስት ባለስልጣኖች ጋር ተወያዩ
ሚያዚያ 4 ቀን 2016 ዓ.ም.
Ø የእድገትና የልማት ከበሮ በሚደበድባት የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ጣራ ደርሷል እየተባለ የሚለፈፍላት ኢትዮጵያ በመረጃ ልማት ሰንጠረዥ የመጨረሻ ሶስተኛ ቦታ ላይ እንደምትገኝ አንድ ዓለም አቀፍ ተቋም ግልጽ አድርጓል። የኢንፎርሜሽን ዲቨሎፕመንት ኢንዴክክ ባለፈው ዓመት በ1967 የዓለም አገሮች ያደረገውን ጥናት ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። ጥናቱ በየአየገሮቹ ያለውን የኢንተርኔት አገልግሎት ስፋትና ጥራት የተንቀሳቃሽ ስልኮች ስርጭትና ኔትወርክ የማግኘት አቅም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ብዛትን ለኢንተርኔት የደረሱ ዜጎች ቁጥርን ግምት ውስጥ ያስገባ እንደነረ ሲታወቅ በውጤቱ በሰንስጠረዥ መጨርሻ 167 ኛ ያወጣቸው ቻድ ስትሆን 166ኛ የሻዕቢያዋ ኤርትራ 165 ኛ ደግሞ ወያኔ በዘረኛንት የሚገዛት ኢትዮጵያ ሆናለች በጥናቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጆ ለዜጎቻቸው በአስተማማኝ መንገድ ብቻ ሳይሆን በጥራት በማቅረብ ኮሪያ ቀዳም ስትሆን ዴንማርክና አይስላንድ አንደ ቅደም ተከተላችው ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነዋል። በጥፋቱ ሰንጠረዥ ትናንት ነጻነት አገኘሁ ያለችው ደቡብ ሱዳን ከኢትዮጵያ በልጣና ተሽላ መገኘቷዘረኛዎቹ ወያኔዎች በኢትዮጵያ ላይ የሚሸርቡን ደባ ሸርና በግልጽ አሳይቷል
Øበተያያዘ ዜና የወያኔ ቡድን ባለስልጣኖች በከፊል ኢትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ በደቡብ አካባቢ ለሚገኘው ተጠቃሚ የትዊተር የዋትስ አብፕ ና የሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ከአንድ ወር በላይ ለሆነ ጊዜ ዘግቶ የነበረ መሆኑ ብሉመርግ የተባለ የዜና ወኪል አጋልጧል። የወያኔ አገልጋይ የሆነው የኢትዮጵያ የቴሌኮሙኒከሽን መስሪያ ቤት የአገሪቷን የኢንተርኔት አገልግሎት በሞኖፖል የያዘ ሲሆን ተቀጣጥሎ ከተያያዘው ሕዝባዊ አመጽ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የኢንተርኔት አገግልጎትን በተለይም የሞባይል አገልግሎት ለመግዛት ማቀደቀዱ ቀደም ብሎ የተዘገበ መሆኑ ይታወቃል። የወያኔ ባለስልጣኖች የኢንተርኔት አገልግሎት ደካማ መሆን ነው እንጅ ሆን ተብሎ የተወሰደ የመንግስት እርምጃ አይደለም ብለው በማለት መግለጫ ለመስጠት ቢሞክሩም አፈናው እንቅስቃሴውን ለማዳከም የተጠቀሙበት እርምጃ መሆኑ የተረጋገጠ መሆኑና ብሶት የገፋፋው የሕዝብ አመጽ በማናቸውም ዓይነት አፈና ሊዳከም እንደማይችል ብዙዎች ይናገራሉ፡፡
Ø የወያኔ አገዛዝ ትውልድ ገዳይ የሆነ የትምህርት ፖሊስ ቀርጾ አንድ ዘርን ብቻ በዕውቀትና በሞራል ኮትኩቶ በማሳደግ ሌላውን ኢትዮጵያ ከንቱና ገልቱ ትውልድ ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ ሱስና በጎጂ ባህል የታሰረ በማድረግ ተተኪ ትውልድ ለማሳጣት ጠንከሮ እየሰራ መሆኑ ታውቋል። በትግራይ ውስጥ በትምህርት ቤት አካባቢ መጠጥ መሸጥ ጫት መነገድ በት/ቤት ግቢ ስጋራ ማጤስ የከለከለው የወያኔ የትምህርት ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ በትምህርት ቤቱ ግቢ አጥር ተጠግቶ ወይም ተሸንቆ በተሰራ የንግድ ቤት አልኮል መጠጥና ሲጋራ እንዲሸጥ ማድረግ ይፈቅዳል። ለትምህርት ቤቱ ልዩ ገቢ ያስገኛል ተብለው የተከፈቱት የንግድ ሱቆች ከልዩ ልዩ ገቢ ጀምሮ የአልኮል መጠጦችን የሚሸጡ ሲሆን ተማሪዎችና መምህራን በእረፍት ጊዜያቸው ወደ ሱቆቹ ጎራ ማለታቸው እየተዘወተረና በትምህርት ሰዓትም መጠጥ የሚጠጡና ሲጋራ የሚያጨሱ መበርከታቸው ታውቋል። በአዲስ አባባ በደጃጅ ገነሜ አንደኛና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይህ ሁኔታ በግልጽ የሚታይ ሲሆን ወላጆችችና ኅብረተሰብ አንድ ካላሉ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ገበታ መሆናቸው ቀርቶ የሱስ መሸመቻ ይሆናል በማለት የሚያስጠነቅቁ ዜጎች ብዙ ናቸው።
Ø በወያኔ ጦር ውስጥ በሚካሄዱት ስብሰባና ግምገማ ላይ ሕዝባዊና አገራዊ ጥያቄ ያነሱ ወይንም ሃሳባቸውን በነጻነት የገለጹትን ማስርና ደብዛ ማጥፋት የተለመደ ተግባር ሲሆን ሰሙኑንም በምስራቅ ዕዝ ውስጥ የተካሄደውን ስብሰባና ግምገማ ተከትሎ ቁጥራቸው ሃያ ሰባት የሚደርስ የበታች መኮንኖችና ወታደሮች ተይዘው መታስራቸው ታውቋል። ወታደሮቹና የበታች መኮንኖቹ የታሰሩት ጦሩን ልታሳምጹ ነው በማለት ሲሆን በወታደር ፖሊስ ተይዘው ለቀናት በሐረር ጦር አካዳሚ ከታስሩ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በድሬደዋ አየር ኃይል ግቢ ውስጥ ታስረው ድብደባና ስቃይ እየተፈጸመባቸው መሆኑ ታውቋል። የወታደሮቹና የበታች መኮንኖች እስር አሁንም ድረስ ለምስራቅ ዕዝ ጦር አባላት ሚስጥር ተደርጎ መቀመጡ ታውቋል። ወታደራዊ ተመልካቾች የወያኔ መሪዎች ለሥልጣን ማራዘሚያና ለህልውናቸው በየጦሩ ውስጥ የራሳቸውን ዘርና ፓርቲ አባላትን በአዛዥነት በመሾም ጦሩን ለመቆጣጠር መቻላቸውን በመግለጽ የወያኔ መሪዎች ያስሯቸውን የሕዝብና የሀገር ልጆች ለማስፋፋት የወያኔ የጦር አለቆችን ማገትና መያዝ ከአዛዥነት ማባረርና ለፍርድ ማቅረብ ሊታሰብበትና የሚገባ እርምጃ ነው ይላሉ።
Ø ቦኮ ሃራም የተባለው አሸባሪ ቡድን በአጥፍቶ ጠፊነት የሚጠቅማባቸው ህጻናት ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ። በአሁኑ ወቅት በአጥፍቶ ጠፊነት ቦምብ ከሚያፈነዱ ሰዎች መካከል ከአምስት አንድ የሚሆኑት አዕምሯቸው በአደንዛዥ ዕጽ የተበከለ ህጻናት መሆናቸው ታውቋል። የዛሬ ሁለት ዓመት ቦኮ ሃራም በአጥፍቶ ጠፊነት ራሳቸውን እንዲገድሉ ያደረጋቸው ህጻናት 11 ሲሆኑ ባለፉት ሶስት ወር ብቻ 44 ህጻናትን ቦምብ በማፈንዳት ተጠቅሞባቸዋል። አደንዛዥ ዕጽን በመጠቀም ህጻናትን በዚህ ተግባር ላይ ማሰማራቱ ቡድኑ መዳከሙን ያሳያል የሚሉ ወገኖች ከካሜሩን ከቻድ ካናይጄሪያና ከናይጀር ጠልፎ የወሰዳቸውን ወደ 1.3 ሚሊዮን የሚደርሱ ሕጻናት በመጠቀም ብዙ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።
Ø ሰኞ ሚያዚያ 03 ቀን 2008 ዓም. ሩዪጊ በሚባለው የብሩንዲ ምስራቃዊ ግዛት ማንነታቸው ያልታወቀ ታጣቂዎች በገበያ ቦታ ላይ በተኩሱት የእሩምታ ተኩስ ቢያንስ አምስት ሰዎችን የገድሉ መሆናቸውና ሌሎች ሰባት ሰዎች የመቁሰል ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል። የእሩምታውን ተኩስ በመተኮስ ጉ በዜጎች ላይ ጉዳት ያደረሱት ታጣቂዎች ቁጥር ሶስት ሲሆን ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ ሳያዙ ያመለጡ መሆናቸው የአይን እማኞች ገልጸዋል። በብሩንዲ የፖሊቲካ ውጥረት ከተፈጠረ ጀምሮ በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት የጠፋ ሲሆን ከ250 ሺ ሰዎች በላይ መሰደዳቸው ይታወቃል።
Ø የደቡብ ሱዳን አማጽያን ቡድን ቃል አቀባይ ሰኞ ሚያዚያ 3 ቀን በሰጠው መግለጫ የደቡብ ሱዳን መንግስት የጸጥታ ኃይሎች 16 የሚሆኑ የደቡብ ሱዳን አማጽያን አባላትን አስረው ደብድባ ፈጽመውባችዋል ብሎ ከሷል። የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪ በሚቀጥለው ሚያዚያ 10 ቀን በዋናዋ ከተማ ጁባ ይገባሉ እየተባለ በሚጠበቅበት ጊዜና የጸጥታውንም ሁኔታ ለመጠበቅ የተወሰኑ የአማጽያኑ ወታደሮች ጁባ በገቡበት ሁኔታ በሰዎቹ ላይ የተፈጸመው እስርና ድብደባ የሰላሙን ሁኔታ ሊያበላሽ ይችላል የሚል ፍርሃት ፈጥሯል። በተጨማሪም ባህር ዔል ገዛል በተባለው ሰሜናዊ ግዛት የመንግስት ኃይሎች በአማጽያኑ ላይ ያካሄዱትን አዲስ ወታደራዊ ጥቃት በማውገዘ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሚያዚያ 10 ቀን መግለጫ ሰጥቷል። መስሪያ ቤቱ የደቡብ ሱዳን ኃይሎች ያከሄዱት ጥቃት የተኩስ አቁሙን ስምምነት የሚጥስ መሆኑን ገልጾ የተጀመረውን የሰላም ሂደት ያደፈርሳል ብሏል።
Ø የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ጀንቲሎኒ ለሊቢያ የአንድነት መንግስት የፖሊቲካና የዲፕሎማሲያዊ እርዳታ ለማድረግ ማክሰኞ ሚያዚያ 4 ቀን 2008 ዓም ትሪፖሊ መግባታቸው ተነገረ። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግፊትና አስተባባሪነት የተቋቋመው የአንድነት መንግስት በባህር በኩል ትሪፖሊ ከተማ ከገባ ጀምሮ አንድ የአውሮፓ ባለስልጣን በሊቢያ ጉብኝት ሲያደርግ ጀንቲሎኒ የመጀመሪያ መሆናቸው ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአንድነት መንግስቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚስተር ፋየዝ ሴራጅ ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ በሰጡት መግለጫ የአውሮፓ አገሮች አዲሱን መንግስት ለመርዳት እና ለማጠናከር ሙሉ በሙሉ የቆረጡ መሆናቸውን ገልጸው ከእሳችው በኋላ በርካታ ባለስልጣኖች ወደሊቢያ በመምጣት የስራ ጉብኝት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ዋናው ቁልፉ አይሲስ እንዳይጠናከርና እንዲወገድ ማድረግ ነው ካሉ በኋላ በርካታ የአውሮፓ አገሮች ኢምባሲዎቻቸውን በትሪፖሊ ሊከፍቱ የሚችሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።
Share0 72 0
No comments:
Post a Comment