Thursday, April 14, 2016

ሳልሳይ ወያነ የሚባል ድብቅ ፓርቲ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ውስጥ ተመስርተዋል። April 14, 2016 – ቆንጅት ስጦታው — Comments ↓ ምርጫ 2012 ሳይደርስ ዓረናን ማፍረስ!

 

ምርጫ 2012 ሳይደርስ ዓረናን ማፍረስ!
እንግድህ ወደድንም ጠላንም ሳልሳይ ወያነ (3rd Weyane)የሚባል ድብቅ ፓርቲ በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ውስጥ ተመስርተዋል። የዚህ ፓርቲ የመጀመሪያው ድብቅ ኣላማው ዓረናን ማፍረስ ሲሆን፣ ሁለተኛ ኣላማው ደግሞ ትግራይ ውስጥ ብቻ የአስተዳደር ለውጥ በማምጣት የህውሃትን እድሜ ማራዘም ነው። ህውሓት ህገመንግስቱን መሰረት ኣድርገው ሲታገሉ ከነበሩ ፓርቲዎች መካከል አንድነትን እና ሰማያዊ ፓርቲን ባቀደው መሰረት ኣፈራርሶ የቀሩትን የተቃዋሚ ፓርቲዎች ለማፍረስ ቆርጦ ተነስተዋል። ኣሁን በህውሓት ኣጀንዳ ውስጥ መፍረስ ኣለበት የተባለ ፓርቲ ዓረና ነው!
.
ለመሆኑ ሳልሳይ ወያኔን ማን መሰረተው? የዚህ ፓርቲ መስራች ኣቶ ስብሃት ነጋ ሲሆኑ፣ ኣባላቶቹ ደግሞ ህውሃትን ሲቃወሙ የነበሩ እና ያሉ የትግራይ ልጆች ናቸው። ከነዚህ መካከል በቅርቡ በየሚድያው፣በፌይስቡክ እና በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ህውሓትን ሲቃወሙ የነበሩ ናቸው። እነዚህ ወጣቶች ህውሃት ከስልጣን እንድትወርድ የማይፈልጉ፣ነገር ግን ህውሓት የተወሰነ ለውጥ ኣምጥታ ስልጣን ላይ እንድትኖር የሚፈልጉ ናቸው። ፍራቻቸው ደግሞ ህውሃት ስልጣን ከለቀቀች “ኣማራ” ይገዛናል የሚል ፈሊጥ ነው።
.
ኣሁን ትግራይ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ያገኘው ዓረና እንዴት እና በምን መልኩ ማፍረስ እንዳለባቸው ከአቶ ስብሃት ነጋ ተልእኮ ተሰጥቶዋቸው በመፈጸም ላይ ይገኛሉ። የመጀመሪያው ተልእኮ የወልቃይትን ጉዳይ ማራገብ ነው። የሳልሳይ ወያኔ ኣባላት ወልቃይት የትግራይ ትልቅ ኣጀንዳ በማድረግ ቀን ከለሊት ስለወልቃይት መጻፍ እና መከራከር ዋነኛው ስራቸው ሲሆን፣ ተቀጥላው ስራቸው ደግሞ፣ ዓረና ትግራይ በወልቃይት ላይ ያለው አቋም የተሳሳተ በማስመሰል(ዓረና ወልቃይት የአማራ ነው የሚለው”ኣማራ እንዲገዛን ነው የሚፈልጉት”)በማለት ከትግራይ ህዝብ ጋር ለማጋጨት መሞከር እና ዓረና በትግራይ ህዝብ ያገኘው ተቀባይነት ማኮላሸት ነው።
.
የትግራይ ህዝብ ለአስራሰባት አመታት ደሙን ኣፍስሶ ኣጥንቱን ከስክሶ በቀን ሶዎስት ጊዜ እንካን መብላት ባልቻለበት ጊዜ ወልቃይት ትልቅ ኣጀንዳ የሚያደርጉት ለምንድነው ስትል መልሱ ሩቅ ሳት ሄድ ታገኘዋለህ። መልሱ ኣጭር እና ግልጽ ነው! የትግራይ ህዝብ በተለይ ወጣቱ ኣሁን ህውሃትን በግልጽ መቃወም በጀመረበት ጊዜ፣ ተቃዎሞውን ለማፍን ብሎም ለማክሰም ነው። ሌላው የወልቃይት ጉዳይ እንደ ትልቅ ኣጀንዳ የሚያነሱት የትግራይ ህዝብን ምክንያታዊ ባልሆነ ስሜት ለመቀስቀስ እና ብሎም “ኣማራ” ድጋሚ መጣልህ ለማለት “ስስ” ምክንያት ስለሆነችባቸው ነው።ከዚህ ቦሃላ ስለወልቃይት ማውራትይ ይቅርባቹ ባልልም ወልቃይት ግን የትግራይ ህዝብ የመጨረሻው ኣጀንዳ እንጂ የመጀመሪያው ኣጀንዳ ኣይደለም። የትግራይ ህዝብ ኣጀንዳዎች ተቆጥረው ስለማያልቁ እዛው ላይ ብታተኩሩ ይሻላል።
.
ኣሁን ዓረናን ለማፍረስ ለምን ተፈለገ? ኣሁን ዓረናን ለማፍረስ የተፈለገው፣ የትግራይ ህዝብ ህውሃት ላይ ጥላቸው ከማንም ጊዜ በላይ ኣፍንቻው ላይ ስለደረሰ እና ለውጥ ስለሚፈልግም ጭምር ነው! ይህም ብቻ ኣይደለም፣ ለሁለት ኣመታት ያክል ያለማስረጃ እና ያለወንጀሉ የታሰረው ኣብርሃ ደስታ ከመፈታቱ በፊት በተቻላቸው መጠን ዓረናን ኣፍርሰው መጠበቅ ስለሚፈልጉ ነው። ኣብርሃ ደስታ መታሰሩን ትግራይ ውስጥ የሚቃወም ሰው በዛ እንጂ ኣላነሰም፣ይህንን ያስፈራቸው ህውሃቶች፣ በነተስፋኪሮስ እና ሴፍ ዓድና በኩል ገብተው ስራቸው ጨርሰው፣ዓረናን ኣፍርሰው፣ ተስፋኪሮስ እና ሰፍ ዓድናን ማሰናበት ኣልያም ስልጣን መስጠት ወይም ገንዘብ መሸለም ነው። የዚህ ሁሉ ወጪ የሚሸፍነው ደግሞ ኢፈርት ነው። ተስፋኪሮስ እና ሰፍ ዓድናን በተዘዋዋሪ ከኢፈርት እንደ ትግራይ ህዝብ ሳይሆን እንደ ስብሃት ነጋ እና ቤተሰቦቹ ድርሻቹ ስለወሰዳቹ እንካን ደስ ኣላቹ።
.
ህውሃት ከዚህ ድብቅ ኣላማ ሶዎስተ ነገር ይጠቀማል። ኣንደኛ ከተሳካለት በስልጣን የሚኖርበት ዕድሜ ማራዘም ሲሆን፣ሁለተኛ ወያኔ ማለት የትግራይ ህዝብ ማለት ነው ለሚሉት ጭፍን ተቃዋሚዎች ማጠናከርያ ሆኑ፣ ተስፋኪሮስም ሆነ ሴፍ ዓድና ዞሮው ዞሮው የህውሃት ተላላኪ መሆናቸውን ግልጽ ማስረጃ ስለሚሆንባቸው ነው። ሶዎስተኛው እስካሁን ድረስ በህውሃት መሰሪ ስራ ያልተበታተነው ዓረናን የመስለ ጸረ ህውሃት ፓርቲ ትግራይ ውስጥ ለመመስረት ኣስቸጋሪ ስለሚሆን ነው። የስም ዝርዝሩ ይቀጥላል በዚህ ኣይቆምም፣ህውሓትን ለሁለት ከፍላቹ ኣሁንም ኣዲስ ኣበባ እና ትግራይ ሳልሳይ ወያኔን መፍጠራቹ ያሳዝናል። ኣሁንም የትግራይ ህዝብ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ጠላት ህውሃት ነው እያልክ ህውሃትን ማፍቀር ኣይቻልም!ለዚህም ነበር ባለፈው ጹሁፌ ህውሃትን ህውሃት ጉያ ውስጥ ሆኑ መቃወም ይቻላል ያልኩት።
Natnael Asmelash.

No comments:

Post a Comment