ትንሽ ጋር እንደመታገል ምን የሚያደክም ነገር አለ?!!
ለኢትዮጵያውያን አብሮ መስራትና ሥርዓት መስርቶ መሄድ ከጊዜ
ወደጊዜ ምን ያህል ከባድ እየሆነ እንደመጣ ለመረዳት ያለፉት አርባና
ሃምሳ አመታትን ታሪካችንን ምስክር ነው፡፡ አለመተማመንና አምባጓሮ
ሳይፈጥርበት ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ ተቋም ለመፍጠር ምን ያህል
እየተቸገርን እንደሆነ በዓለማዊ ተቋሞቻችን ይቅርና በየሐይማኖት
ድርጅቶቻችን መካከል ያለውን ጥልና ፍጅት ስናይ እርግማን ያለብን
ይመስላል፡፡ ከዚህ በሽታችን በተጨማሪ ይህች ድሃ ሐገር ልትሰጥ
የምትችለው ነገር ሁሉ በእጁ የሆነው ወያኔ/ኢሕአዲግ፣ ለሕልውናዬ
አደጋ ናቸው ያላቸውን ሁሉ “እግር ሲያወጡ እቆርጣቸዋለሁ” በሚለው
መርሑ መሰረት በሕዝብ ሐብት ቅጥረኞችን በማሰማራት የፖለቲካም
ይሁን የሲቪል ተቋማትን እያበጣበጠ ሰላምና ህልውናቸውን ሲያፈርስ
ኖሯል፡፤
በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የተከሰቱ ችግሮችም የእነዚህ ነባራዊ
እውነታዎች ውጤት ናቸው፡፡ አሁን የሚታዩት ችግሮች ለመተንበይ
የከበዱና ለመፍታትም አስቸጋሪዎች አልነበሩም፡፡ ነገር ግን ኋላ ቀር
የሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ በሚፈነጭባት ኢትዮጵያ መቀናናት፣
ምቀኝነት፣ ድንቁርና፣ ሎሌነት እና መሸጦነት የዘመናችን ቁንጮ
መገለጫዎች እየሆኑ መምጣታቸውና፤ እነዚህን ደካማ ጎኖች እያነፈነፈ
የሚጠቀምባቸው ወያኔ/ኢህአዲግ ፍርፋሪ ለቃሚዎችን በመግዛትና
አስርጎ በማስገባት የፓርቲዎችን ሰላም ማደፍረስና ማፍረስ የተለመደ
ሥራው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲም የእነዚህ እኩይ አስተሳሰብ ሰለባ
ከመሆን አላመለጠም፡፡
የገዥው ቡድን የጥፋት ሚና እንዳለ ሆኖ የአስተሳሰብ ድሃ በሆኑ
የፓርቲው አባላት የተፈጠሩ ችግሮችንም ሆነ ችግሩን ስለፈጠሩት ትንንሽ
ሰዎች በየመገናኛ ብዙሃኑ ማውጣት ለውጥና ፍትህ ለጠማው
የኢትዮጵያ ህዝብ የሚፈይድለት ነገር የለም ብዬ ስለማስብ እስካሁን
ምንም ሳልል ቆይቻለሁ፡፡ አሁንም ቢሆን ስለነዚህ ትንንሾች በማውራት
ራሴን እንደእነሱ ማውረድና ማቆሸሽ ፍላጎቴ አልነበረም፡፡ የወያኔ
ቅጥረኛ ከሆኑት ውጭ ያሉት ምን ማድረግ እንደፈለጉ የማያውቁና ዛሬ
በፖለቲካው ሰው ጠፍቶ በማይገባቸው ቦታ የተቀመጡ ድኩማኖችም
የእኔ አጀንዳ ለመሆን አይመጥኑም፤ የእኔም አስተያየት አይገባቸውም
ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህም አቋሜ ምክንያት እስካሁን በፓርቲው ዙሪያ
ሲያናፍሷቸው በነበሩ መሰረተ ቢስ የጥፋት መልዕክቶች ላይ አስተያየት
ከመስጠት ተቆጥቤ ቆይቻለሁ፡፡ነገር ግን፣ አሁን ነገሮችን በደንብ
ሳጤናቸው በፓርቲው ላይ የሚደረጉ አፍራሽ ተግባራት ከእነዚህ ትንንሽ
ደንቆሮዎች አቅም በላይ እያለፈ በገዢው ቡድን እጅ መሽከርከር
መጀመሩ ግልፅ እየሆነ መጥቷል፡፡ በተለይም ሰሞኑን እኔና ጓደኞቼ
ከሰማያዊ ፓርቲ መባረራችንን እና የተወሰኑት ደግሞ መታገዳቸውን
የሰሙ በገጠሪቱ ኢትዮጵያ ሳይቀር በተለያዩ የዓለም ክፍል የሚገኙ
ኢትዮጵያውያን በነገሩ ተገርመውና ተደናግጠው በስልክ፣ በአካል፣
በማህበራዊ ሚዲያና በኢ-ሜይል ስለሆነው ነገር ማብራሪያ
እንድሰጣቸው ስለወተወቱኝ ለጠያቂዎቼ መረጃ ለመስጠትና ወያኔም
የስልጣን ጥመኞችንና ቅጥረኞችን በመጠቀም የሚፈፅመውን ደባ
ለማጋለጥ ትንሽ ነገር ማለት እንዳለብኝ ስላመንኩ ይህችን ፅሑፍ
አውጥቻለሁ፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ የተፈጠረው ችግር የርዕዮተ ዓለም ልዩነት
አይደለም፤ልዩነቱ እንዲህ ዓይነት የእምነትና የአስተሳሰብ መጋጨት
ቢሆን ኖሮ በሃሳብ የተለያዩ ሰዎችም ይከባበራሉ፤ ችግሩንም
በውይይትና በክርክር መፍታት ይቻል ነበረ፡፡ አሁን ያለው ችግር ግን
የተለያዩ ፍላጎቶች የሚንጸባቁበትና አባላቱም በሚያመሳስላቸው
አስተሳሰብ ውስጥ የሚሳተፉባቸው አራት ቡድኖች መካከል የሚደረግ
ፍልሚያ ነው፡፡ እነዚህም 1ኛ. ፓርቲው እንዲፈርስ ወይም እንዲዳከም
በሚሰሩ የወያኔ ቅጥረኞች 2ኛ. የስልጣንና ዝና ጥመኞች 3ኛ.
የሚያደርጉት ነገር ምን እንደሚያመጣ በማያዉቁ ደናቁርቶችና 4ኛ.
እነዚህን ሶስቱንም አጥፊዎች በሚከላከሉ እውነተኛ የፓርቲው አባላት
መካከል ነው፡፡ ዓላማና ፍላጎታቸው የተለያዩ ቢሆኑም መጀመሪያ
የጠቀስኳቸው ሦስቱ ቡድኖች “ስራቸሁ ትክክል አይደለም” ብለው
የሚከራከሯቸውን የፓርቲውን እውነተኛ ኣባላት ስለማይወዱ የጋራ
ግንባር ፈጥረው አንድ ስለሆኑ አሁን ያለው ጠብና ክርክር በሁለት
ቡድኖች መካከል ሆኗል ማለት ይቻላል፡፡
የሚሰሩት ነገር ምን እንደሚያስከትል መገመት እንኳን የማይችሉ ሰዎች
የሚያደርጉት ነገር ምን እንዲያመጣላቸው ፈልገው እንደሆነም
አያውቁም፡፡ እነዚህ ሰዎች በሚሰማቸው የዝቅተኝነትና የጥላቻ ስሜት
ከመነዳትና ለሌሎች ሴረኞች መጠቀሚያ ከመሆን ውጭ አንድ
ሊያሳኩት የሚፈለጉት የታወቀ ነገር ስለሌላቸው ለማያውቁት መድረሻ
የሚታወቅ ስልት ሊቀይሱም አይችሉም፡፡ የወያኔ ቅጥረኞችና ሰርጎ
ገቦች ከጀርባ ተደብቀው በጥፋታቸው እንዲገፉበት አስፈላጊውን ሁሉ
የሚያደርጉላቸው በስልጣን ጥም የሰከሩ ድኩማኖች ግን፣ በባለፈው
ጉባኤ ተመኝተውት ያጡትን ስልጣን ለማሳካት ሁለት ስልቶችን
ነድፈዋል፡፡ እነዚህም አንደኛ የፓርውን እንቅስቃሴ በማዳከም ፓርቲው
ላይ ለሚደርሰው ጥፋትም አሁን ያለውን አመራር ተጠያቂ ማድረግ
ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ የአመራሮችን ስም በማጉደፍ በሚቀጥለው
ጠቅላላ ጉባኤ ስልጣን ላይ ለመውጣት እንደ ዋና ስትራቴጅ ነድፈው
ጠንክረው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡
በመጀመሪያው ስልት መሰረት፣ ፓርቲው ሥራውን በአግባቡ እንዳይሰራ
ለማድረግ በተቻለ መጠን የፓርቲውን የተለያዩ ተቋማት በራሳቸው
ደጋፊዎች መቆጣጠርና አሁን በአመራር ላይ ያሉትን ይደግፋሉ
ያሏቸውን አባላት ደግሞ በፓርቲው ውስጥ ምንም ሚና እንዳይኖራቸው
ወይም እንዲባረሩ ማድረግ እንደ ቁልፍ ስልት ተይዟል፡፡ ፓርቲው
የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ሁሉ ለማስተጓጎል የመጀመሪያው እርምጃ
የወሬና አሉባልታ ዋና ምንጭ የሆነው አቶ እንደሻው እምሻውን ከህግ
ውጭ በፅህፈት ቤት ኃላፊነት ማስቀመጥ ነበር፡፡ (በነገራችን ላይ
በፓርቲው ውስጥ ለተፈጠረው ችግር ቁልፍ ምክንያት ይህ በሕገ
ወጥነት በፅ/ቤት ኃላፊነት የተቀመጠው ሰው ሲሆን ለዚህም ኦዲትና
ምርመራ ኮሚሽን እና የምክር ቤት ሰብሳቢ የሆነው አቶ ይድነቃቸው
ከበደ ኃላፊነነቱን ይወስዳሉ፡፡ እንደሻው አሁን እንዴት ከፓርቲው ደንብ
ውጭ በፅ/ቤት ኃላፊውነት እደተቀመጠ መዘርዘሩ የዚህ ፅሁፌ ዋና
ኣላማ ባይሆንም በጠቅላላ ጉባኤ ለምክር ቤት አባልነት የተመረጠና
ስሙም ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በምክር ቤት አባልነት የተላለፈ ሰው፣
በምክር ቤት ብዙ ስብሰባዎች በመሳተፍ የፖለቲካ ውሳኔዎች ላይ
ድምፅ የሰጠ ሰው በፅ/ቤት ሃላፊነት ሲቀጥል እንዴት ህገ ወጥ
እንደሚሆን የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ በማገናዘብ መረዳት
ይቻላል)፡፡ አቶ እንደሻው እና በቦታው ካልተቀመጠ ሞተን እንገኛለን
ያሉት አቶ ይድነቃቸው ከበደ የፅ/ቤት ኃላፊነትን መልቀቅ የሞት ሽረት
ጉዳይ እንደሆነባቸው ያረጋገጥነው ሰሞኑን የወጣ መረጃ አቶ እንደሻው
የፓርቲውን ማህተም በመጠቀም በሚሰራቸው ህገወጥ ተግባራት የገቢ
ምንጭ እንዳደረገው የሚያመላክት ሲሆን ትንቅንቁም ይህንን ጥቅም
ላለማጣት እንደሆነ ግልፅ ሆኗል፡፡ ሌላው የፓርቲውን እንቅስቃሴ
ማዳከሚያ ስልት ደግሞ ሊቀመንበሩ በሥራ አስፈፃሚ አባልነት
የሚያቀርባቸውን እጩዎች በምክር ቤቱ እንዳይፀድቅ በማድረግና
ፓርቲው ሥራ እንዳይሰራ በማዳከም በሂደትም ለሚጠራው ጠቅላላ
ጉባዔ “የአመራር ችግር በመኖሩ ሥራ አልተሰራም” በማለት ይልቃልን
አውርደው ለመመረጥ መስራት ነው፡፡ ይህ እኩይ አስተሳሰብ ብዙዎቹ
የዚህ ስልት ደጋፊዎች የማያውቁት ድብቅ ዓላማም አለው፡፡ በቅርብ
በተደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ሳይፈልጉት በድጋሜ በሊቀመንበርነት
የተመረጠባቸው ኢንጅነር ይልቃል በችሎታቸውም ሆነ ከዚህ በፊት
በነበራቸው የሥራ ግንኙነት ምክንያት ለድጋሜ እጩ የስራ አስፈፃሚነት
እንደማያቀርባቸው የገመቱት አቶ ሰለሞን ተሰማ፣ አቶ ይድነቃቸው ከበደ
እና አቶ ጌታነህ ባልቻ የእነሱ ብቻ ከሥራ አስፈፃሚነት መቅረት
የሚያደርስባቸውን የስሜት መጎዳት ቢያንስ ሌሎችም ተመልሰው
እንዳይመረጡ በማድረግ በአቻነት ለማካካስ የጠነሰሱት የድብቅ ፍላጎት
ማስፈፀሚያ ስልት ነው፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ለሥራ
አስፈፃሚነት ይልቃል በእጩነት ይዟቸው ይቀርባል ብለው የገመቱንን
በተለይ የእኔን፣ የእያስጴድንና የስለሺን ስም በማጉደፍ የእኛ የሥራ
አስፈፃሚ አባልነት በምክር ቤቱ እንዳይፀድቅ ብዙ አስፀያፊ የስም
ማጥፋት ዘመቻ አካሂደዋል፡፡ ከቀድሞ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት
በብቸኝነት በሁለተኛው ዙር በሥራ አስፈፃሚነት የተካተተው ዮናታን
ተስፋዬንም እንዳይመረጥ ያደረጉት የስም ማጥፋት ባይሳካላቸውም አቶ
ሰለሞን፣ አቶ ጌታነህና አቶ ይድነቃቸው ከበደ ዮናታን ላይ የተቃውም
ድምፅ በመስጠት እንዳይመረጥ መፈለጋቸውን አስመስክረዋል፡፡
የዮናታን ጉዳይ በዚህ ያልታሳካላቸው የቅናት ምርኮኞች በሌላ መንገድ
ገለል እንዲልላቸው በድንቁርናና በቅጥረኝነት በተሞላው የዲስፕሊን
ኮሚቴ በኩል ከፍተኛ ሻጥር በመስራት ከፓርቲው ደንብና አሰራር ውጭ
እንዲባረር አስወሰወነዋል፡፡ በተጓደሉ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት
ምትክ ሊቀመንበሩ ሌሎች እጩዎችን አቅርቦ ለማስፀደቅ ያደረጋቸውን
ተደጋጋሚ ሙከራዎች፣ ስብሰባን በመበጥበጥና አጀንዳን በማሳደር፣
በዚህ በኩል የያዙትን ፓርቲን የማዳከም ተልዕኮአቸውን ለማስፈፀም
ብዙ ርቀት ተጉዘዋል፡፡
ምንም እንኳን ከመጀመሪያው ስልት ብዙ የራቀ ባይሆንም፣ ሁለተኛው
ስልት ደግሞ ስም ማጥፋት፣ አሉባልታ መንዛት እና አባላትና ደጋፊዎች
በፓርቲው እምነት እንዲያጡ ማድረግ ነው፡፡ በመሰረቱ ይህ የስም
ማጥፋት ዘመቻ አዲስ የተፈጠረ ስልት ሳይሆን በባለፈው ጠቅላላ
ጉባኤ ዝግጅት ጀምሮ በሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ ገንዘብ መባከንና
መመዝበር ዋና አጀንዳ ሆኖ የይልቃልን ስም በማጉደፍና በአባላት
እምነት እንዲያጣ በማድረግ በጠቅላላ ጉባዔው የሊቀመንበርነት
ቦታውን ለመያዝ ዋና ስትራቴጂም የነበረ ነው፡፡ ይህንንም ለማሳካት
በተለይ ሰለሞን ተሰማ በምክር ቤት ስብሰባዎች በተደጋጋሚ ያለምንም
ማስረጃ ስማችንን ሲያጎድፍ ከመቆየቱም በተጨማሪ ይህንኑ የስም
ማጥፋት ስራውን ለጠቅላላ ጉባኤውም በትልቅ ዲስኩርነት አቅርቦ
ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች ስልጣን ላይ ለመውጣት በነበራቸው ምኞት
አሉባልታቸውን በበራሪ ወረቀት ጭምር አዘጋጅተው ለጠቅላላ ጉባኤው
ተሳታፊዎች በማሰራጨት ተሳታፊዎችን በማሳሳት ለመመረጥ
ቢያልሙም በዕለቱ ያጋጠማቸው ተቃውሞ ግን እንኳን ለመመረጥ
አይደለም እጩ ሆነው ለመቅረብ ድፍረት አጥተው ራሳቸውንና
ምኞታቸውን ክደው ተደብቀዋል፡፡ ነገር ግን እነዚህ ቁስለኞች፣ አሁን
ያልተሳካላቸውን ምኞት በአመቱ በሚጠራው ጠቅላላ ጉባኤ ለማሳካት
የሃሜትና ስም የማጥፋት ስራቸውን ለመቀጠል የወሰኑት ከጉባዔው
ማግስት ጀምሮ ነው፡፡
የዚህ ስልት ውጤት ለወያኔ ቅጥረኞች ፓርቲውን ለማደከም ቁልፍ ነገር
በመሆኑ ለምን ይህን አደረጉ ተብሎ ሊጠየቅ አይችልም፡፡ በችሎታና
በውድድር ወደ ስልጣን መውጣት ዳገት የሆነባቸው የሥልጣንና የዝና
ጥማታሞችም፣ የፓርቲው ስም መርከስ አያሳስባቸውም፡፡ እነሱ፣
ለምኞታቸው መሳካት እንቅፋት ይሆንብናል ብለው የፈረጁትን ሰው
ወይም ቡድን፣ ስም ማርከስ የእነሱን ወደ ስልጣን እርካብ የመውጣት
ዕድል እንደሚያሳካላቸው ከማሰብ ውጭ ሌላ የሚታያቸው ጉዳት
የለም፡፡
ከጉባኤው በኋላም የሰውን ቀልብ ለመግዛት ቀላል የሆነችውን የገንዘብ
መጥፋትና መባከንን በተደጋጋሚ በማንሳት በፓርቲው ውስጥ በነበረን
ኃላፊነት ምክንያት ከገንዘብ አወጣጥ ጋር ቅርበት የነበረንን ሰዎች
ስማችንን ማጉደፍ ትልቅ ሥራ አድርገው ቀጠሉበት፡፡ በተጨበጠ ነገር፣
ስላጠፋነው ገንዘብ በማስረጃ አቅርቦ ከሚከሰን ይልቅ አሉባልታ
በማውራትና የሰዎችን ስም በማርከስ የአእምሮ ክስረቱን የሚያረካው
የድኩማን ብዛት ጉድ የሚያሰኝ ነው፡፡ ማን፣ ስንት ገንዘብ፣ መቸና እንዴት
እንዳጠፋ ሳይገለፅ ዝም ብሎ “ገንዘብ ተመዘበረ” የሚለው የደንቆሮ
ውንጀላ ማቆሚያ ስለጠፋለት እውነቱ እንዲረጋገጥ በመጀመሪያም
በኦዲት በኩል ይጣራና ይፋ ይደረግ እያልን፣ ከጉባኤው በፊት ጀምሮ
ስንጠይቅ ቆይተናል፡፡ ኦዲትም፣ እንዲያጣራ አስፈላጊውን ትብብር ሁሉ
አደረግን፡፡ ነገር ግን ለምክር ቤቱም ሆነ፣ ለጠቅላላ ጉባዔው የፓርቲው
ገቢና ወጭ ተመሳክሮ ይህንን ያህል ገንዘብ ጠፍቷል ወይም እከሌ
የሚባል ሰው ይህንን ያህል ገንዘብ አባክኗል የሚል መረጃም ሪፖርትም
ሳያቀርብ ቀረ፡፡ ስም ማጥፋት ግን ከጉባኤው በኋላም ቀጠለ፡፡
“በምክር ቤቱ በኩል አጣሪ ኮሚቴ ይሰየምና አጣርቶ ያቅርብ” በማለት
እኛ ስማችን የሚጠፋ ሰዎች ሃሳብ አቀረብን፡፡ ምክር ቤቱም፣ በአጣሪ
ኮሚቴ መቋቋም ስለተስማማ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ የእኛን ስም
የሚያጠፉትን ሰዎች የአጣሪ ኮሚቴ አባላት ሆነው እንዲሰሩ ምክር ቤቱ
እንዲያፀድቅለት ይዞ ቀረበ፡፡ ነገሩ የሚያስቅ ቢሆንም፣ አጣሪ ኮሚቴ
ሆነው እንዲሰሩ የተፈለጉት ያለምንም ማስረጃ የእኛን ስም ሲያጠፉ
የነበሩት ሰዎች ከሆኑ በዚህ በኩል ዋናው ስም አጥፊ የነበረው አቶ
ስሜነህ ፀሐይ በአጣሪ ኮሚቴ አባልነት እንዲጨመር ሃሳብ አቅርቤ
እንደነበር፣ በስብሰባው ላይ የነበሩ ሁሉ የሚያስታውሱት ሀቅ ነው፡፡ ነገር
ግን፣ ያቀረብኩት ጥቆማም ተቀባይነት ሳያገኝ፤ አቶ ስሜነህም
በኮሚቴው ሳይካተት ቀረ፡፡ አጣሪ ኮሚቴውም፣ ያጓተተውን ያህል ጊዜ
አጓቶ አሁንም፤ የተጨበጠ ነገር ከማምጣት ይልቅ ሌላ ሃሜት ለቃቅሞ
ጥላቻንና ድንቁርናን በደንብ ደርቶ ይዞ ቀረበ፡፡ በአጣሪ ኮሚቴው የቀረቡ
በጣም ብዙ አስቂኝ ትንተናዎች እንዳሉ ይቀመጡና፣ በግሌ በጣም
ያሳዘነኝና ልቤን የሰበረኝ የራሴ የትግል ጓዶች ናቸው ብዬ ከማስባቸው
ሰዎች የማልጠብቀው “ገንዘቡን ወያኔ ቢበላው ይሻለን ነበር” የሚል
አስተያየት ተካቶበት ቀርቧል፡፡ (በነገራችን ላይ ይህ ነገር በድምፅ
ተቀርፆ ተቀመጧል!)፡፡
ከላይ እንደጠቀስኩት የአጣሪ ኮሚቴ አባላት የነበሩት አቶ ሰኢድ
ኢብራሂም፣ አቶ ተገኔ ታደሰ እና አቶ ተስፋኣለም ታደሰ ገለልተኛ
እንዳልነበሩ ባውቅም፤ ነገር ግን እውነትና ፍትህ አጥተናል ብለው
በተቃዋሚ ጎራ የተሰለፉ ሰዎች በእነደዚህ ዓይነት ጭፍን ጥላቻና
የቡድንተኝነት አሳፋሪ ተግባር ውሥጥ ይዘፈቃሉ ብዬ አስቤ አላውቅም
ነበር፡፡ የአጣሪ ኮሚቴው ሪፖርትም፣ ማሰሪያው ምን እንደሆነ
የማይታወቅ፣ ምክር ቤቱ ሪፖርቱን ሰምቶ ምን እንዲያደርግለት
እንደሚፈልግ የውሳኔ ሃሳብ እንኳ የሌለው፣ ፍሬ ቢስ ሆኖ ቀረ፡፡ እኛ
ስማችን በሚጠፋው በኩል ያለን ሰዎች፣ እውነት እንዲወጣ
ስለምንፈልግ የሥነ ስርዓት ክስ ይመስረትብንና እከሌ ይህንን ያህል ብር
በዚህ ጊዜ በግል ወይም በጋራ አጥፈተሃል የሚል በሰውና በሰነድ
ማስረጃ የተደገፈ የሚጨበጥ ነገር እንዲቀርብና ጥፋተኛነታችን ወይም
ንፅሕናችን እንዲታወቅልን አጥብቀን ጠየቅን፡፡ ክስ እንዲመሰረትብን
የውሳኔ ሃሳብ ከማቅረባችንም በላይ፣ ውሳኔውን በድምፅ ከደገፉት
መካከል እኛው ተከሳሾቹ ነበርን፡፡ ተከሳሾች ምን አጥፍተን ምን ዳኝነት
እንደሚጠበቅ የማይለይ፣ አንድ የህግ መሰረታዊ እውቀት ካለው ሰው
በማይጠበቅ፣ የፅሁፍ ክስ ተመሰረተብን፡፡ የሥነ ስርዓት ክስ ሂደቱ ገና
ከጅምሩ፣ ያንኑ ስምን የማጉደፍ ዓላማ ማስፈፀሚያ ከመሆን አላለፈም፡፡
አኛው ተከሳሾቹ ለምነን ያስመሰረትነውን ክስ፣ አንድ የተደበቀ ልዩ ነገር
የተገኘ ለማስመሰል “የሰማያዊ አመራሮች በገንዘብ ምዝበራ ተከሰሱ”
በማለት ለወያኔ ቅርበት ባላቸው ጋዜጦች እንዲወጣ ተደርጓል፡፡ ክስ
የመስማት ሂደቱ በጣም አስቂኝ ነበር፡፡ ከሳሽ ያልጠራብንን ምስክሮች
የዲስፕሊን ኮሚቴው (ወ/ሮ ሃና) በራሷ ፍላጎት ብቻ ምስክሮች
እየፈጠረች ተከሳሾች በሌለንበት እንዲመሰክሩ ታደርጋለች፡፡ ምስክሮች
በሚሰሙበት ጊዜ እኛም ተገኝተን መስቀለኛ ጥያቄ እንጠይቅ ስንል ወ/
ሮ ሰብሳቢዋ “ሞቸ እገኛለሁ እናንተን አይመለከታችሁም” ትለናለች፡፡
ተከሳሾችን ለመደብደብ ሲጋበዝና ሲገላገል የነበረው አቶ ሐሰን ቡሴር
“ፀብ ስላለን ከዳኝነቱ ይነሳልን” በማለት የወያኔ ፍርድ ቤት እንኳን
የማይከለክለውን ቅሬታ የማቅረብ መብታችንን ጠቅሰን ለኮሚቴው
በፅሁፍ ያቀረብነው አቤቱታ የት እንደደረሰ ሳይታወቅ ቀረ፡፡ በመጨረሻም
ከሰባቱ በህጋዊነት ከተሰየሙ የሥነ ስርዓት ኮሚቴ አባላት መካከል
ሦስቱ ብቻ በተገኙበትና፣ ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አባል መሆናቸውን
የማናውቃቸው ሁለት ሰዎች ለምልዓተ ጉባኤ ማሟያነት ተገኝተው
“ዘረፉ” የተባልነው ገንዘብ አሁንም በምንም ማስረጃ ሳየረጋገጥና
ኮሚቴው ራሱ ምን ያህል እነደሆነ ሳያውቀው “ኦዲት እንደገና አጣርቶ”
እንዲያስከፍለን ትዕዛዝ ተሰጥቶት “ጥፋተኛ” ተብለን የአንዳችን ጥፋት
ከሌላችን በምን እንደሚያንስ ወይም እንደሚበልጥ ሳይታወቅ የተወሰንን
ከፓርቲው እንድንባረር፣ የተወሰኑ ደግሞ እንዲታገዱ፣ ተወስኖብን
የዲስፕሊን ኮሚቴውም ስራ ተጠናቀቀ፡፡ የልጆች ጨዋታ ማለት ይሔ
ነው፡፡ በአንድ በኩል ከሳሻችን የሆነው ይድነቃቸው ከበደ የዲስፕሊን
ኮሚቴው ያሳለፈው ውሳኔ እኔ ባልከሰስኩትና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ
በመሆኑ ተቀባይነት የለውም፤ ውሳኔውንም ሆነ ሂደቱን እቃወማለሁ
ይላል፡፡ ታዲያ ምን ታደርጋለህ ሲባል “ፌስ ቡክ ላይ አወራዋለሁ”
ይላል፡፡ ሌላ የልጆች ጨዋታ!
በሌላ በኩል በፓርቲው ደንብ መሰረት፣ የዲስፕሊን ኮሚቴውን
የሚያቋቁመው ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን “የዲስፕሊን ኮሚቴ የሚሰራው
ህገ ወጥ ስራ ነው ውሳኔውም ተቀባይነት የለውም” በማለት፣ እስካሁን
በዲስፕሊን ኮሚቴው የተሰጡ ውሳኔዎችን በተደጋጋሚ ውድቅ ሲያደርግ
ቆይቷል፡፡ ነገር ግን እነዚህን፣ ለወያኔ በቅጥረኝነት የሚሰሩ የዲስፕሊን
ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደው፣ ምንም ዓይነት እርምጃ የለም፡፡ ነገሩ
ፓርቲን የሚያፈርስና፣ የተጨማለቀ ስራ እንዲሰሩ የፓርቲ አባል
መሆናቸው የማይታወቁ ሰዎችን በዲስፕሊን ኮሚቴ አባልነት ከህግ
ውጭ የኮሚቴው አባል እንዲሆኑ የሚያደርግ ተቋም፣ “የዲስፕሊን
ኮሚቴ የሰራው ከህግ ውጭ ነው” እያለ መግለጫ የሚሰጠውና
ውሳኔአቸውንም የሚያግደው፣ ከአባላትና ከህዝብ የሚደርስበትን
ተቃውሞ ለማብረድ እንጅ፣ ፓርቲውን በማፍረስ ሥራ ላይ የተጠመዱት
ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ውስጥ ያሉ ሰዎች መሆናቸውን አጥተነው
አይደለም፡፡ በነገራችን ላይ፣ በኦዲትና ምርመራ ኮሚሽንም ሆነ በሥነ
ስርዓት ኮሚቴው ውስጥ ፓርቲውን በሚያፈርሱና በሚጎዱ ተግባራት
የተጠመዱት አብዛኛዎቹ፣ በትምህርታቸውም ሆነ በሥራ ልምዳቸው
የህግ እውቀት የሌላቸው ሲሆኑ፣ በአንፃሩ ስለህግ በደንብ የሚያውቁና
የጥብቅና ፈቃድ ድረስ ያላቸው ሰዎች የሚሰራው ነገር ሁሉ ህግን
ያከበረ እንዲሆን የሚያቀርቡትን ሃሳብ እንኳ የሚያዳምጣቸው በማጣቱ፣
ሥራዎች ሁሉ ያላዋቂዎችና የቅጥረኞች መፈንጫ መሆናቸውን
እንባቢያን ቢረዱት እወዳለሁ፡፡
እነዚህ ትንንሾች ሁለት ነገር ተሳክቶላቸዋል፡፡ አንደኛ ለወያኔ ቅጥረኞች
መንሸራሸሪያ በመሆን ፓርቲው እንዲዳከምና ስሙ እንዲጠፋ
አድርገዋል፡፡ ሁለተኛው ለኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነትና የፍትህ ጥማት ብዙ
በምናበረክትበት ሰዓት፣ ስለትንንሾች በማውራት እኛም አብረን
እንድንረክስ ምክንያት ሆነዋል፡፡ መቸም፣ ይህን ሁሉ ዝባዝንኬ
በትዕግስት ያነበበን ሁሉ አደንቃለሁ፡፡ ይህንን በመፃፍ ያጠፋሁት ጊዜዬ
ያሳዝነኛል፡፡
ትግሉ ይቀጥላል!!!!

No comments:
Post a Comment