Thursday, April 14, 2016

ሕወሓት በኦሮሚያ ከ800 በላይ አመራሮች ላይ እርምጃ ወሰደ * 121 ባለስልጣናት ሊታሰሩ ነው




(ዘ-ሐበሻ) በመላው የኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ቁጣ ተከትሎ ከሕዝቡ ጎን ወግነዋል አልያም ደግሞ የሕወሓትን እርምጃ ላለማስፈጸም ለግመዋል የተባሉ ከ800 በላይ የኦህዴድ ባለስልጣናት ላይ እርምጃ ወሰደ:: አብዛኞቹ ባለስልጣናት ከነበሩበት የስልጣን እርከን ወርደው ታች እንዲሰሩ የተፈረደባቸው ሲሆን 121 አመራሮችን ደግሞ ለማሰር መዘጋጀቱን ዛሬ የመንግስት ሚዲያዎች ባሰራጩት መረጃ ላይ ተገልጿል::
በነዚህ “ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ” ለሚፐወዙት ባለስልጣናት የተሰጠው ምክንያት በየመሬትና መሬት ነክ፣ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመንገድ፣ የውሀ፣ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎትና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ለግመዋል አልያም ደግሞ አልታዘዝ ብለዋል በሚል ምክንያት ይሁን እንጂ የውስጥ ምንጮች እንደሚሉት ግን ከሕዝቡ ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ነው ይላሉ::
የኦሮሚያ ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ባወጣው መግለጫው 708 ከፍተኛና መካከለኛ ባለስልጣናት ከስልጣናቸው እንዳነሳ እንዲሁም 121 የዞን እና የከተማ የወረዳ ሃላፊዎችን ዝቅ ብለው እንዲሰሩ አድርጓል:: ከ708ቱ ውስጥ ደግሞ 121ዱ በሕግ እንደሚጠየቁ የወጣው መግለጫ ያሳያል::
በኦሮሚያ ጋብ ያለ የሚመስለው ሕዝባዊ ቁጣ አልፎ አልፎ በየከተማው ይታያል:: በዚህ ሳምንት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ቀጥሎ ነበር:: በተለይም ከትናንት በስቲያ በአምቦ ዩኒቨርሲቲ አዋሮ ካምፓስ ተማሪዎች ሕዝባዊ ቁጣቸውን በስር ዓቱ ላይ ሲያሰሙ ነበር:

No comments:

Post a Comment