በሹመት ስም፣ በሀገር ሰላም ስም፣ በትራንስፎርሜሽን ስም፣ በኢንቬስተሮች ማበረታታት ስም፣ ዘራፊዎችን በማሳደድ ስም፣ በፋይናንስ፣ በገቢ አሰባሰብና የመሬት ቁጥጥር ጉዳይ ስም… የሚካሄዱ ምዝበራዎች ተጧጡፈው ቀጥለዋል::በሥልጣን ብልግናም፣ በመሬት ዘረፋም ፣ በታክስ ማጭበርበርም ፣ በኮንስትራክሽን ግዢም ፣ በሚዲያ ኢንዱስትሪ ሀሳዊ – ስብከትም ፣ የቦርድ አባልነትን ተገን በማድረግም፣ በሙልሙል ቢሮክራት መልክም ኢሕኣዴጋዊ ቅኝቱ ከጅብ ጅማት እንደተሰራ ክራር ልብላው ልብላው ብቻ ነው::
በሀገራችን የሚታየውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ስናይ ኃምሌት ይከሰታል፡-
“…ኋላ ምን ሊታየኝ ኖሯል፣ ጊዜ ከፈተነው ሌላ
ምድር ዕፅዋት ብቻ አታበቅል፣ ያለሾህ ያላሜከላ
ወይንም የተፈጥሮ መልክ፣ ሲካበት ሞልቶ ድርጅቶ ብቻውን አደለም ከቶ
ግን እንደዚሁ እንደ ህንፃ፣ ላዩ በሰም አንፀባርቆ
አካባቢው በጌጥ ደምቆ
መሰረቱ ግን በግድፈት፣ በአገም ጠቀም ተደባብቆ
በመሀንዲስ ጥበብ ጉድለት፣ ወይ ባጉል መራቀቅ ዘፍቆ
ከስህተቱም፣ ከጥራቱም፣ ተቻችሎ፣ አለ ተጣብቆ”
ህንፃው ብቻውን ባዶ ነው፡፡ መሰረቱ የተዛባ ነው፡፡ መሀንዲሱ ስራውን በአገም – ጠቀም ሰርቶ አሳቡን ከወሰደ ቆይቷል፡፡ አካባቢያችን ጌጥ ብቻ ነው! እሾህና አሜከላ ዙሪያችንን ከቦናል፡፡ ይሄ የሀገራችን ሀቅ ነው፡፡የሃሳብ ስብስብ – addisadmassnews.com ድረ ገጽ #ምንሊክሳልሳዊ #AddisAdmass

No comments:
Post a Comment