Monday, April 4, 2016

በወልቃይት ጸገዴ ተወካዩች ህገ መንግስታዊ ጥያቄ የቀረበለት የፌደሬሽን ምክር ቤት አስገራሚ ምላሽ

ሳተናው) በወልቃይት ጸገዴ ህዝብ ውክልና ተሰጥቷቸው በሁለት የተለያዩ ወቅቶች ለፌደሬሽን ምክር ቤት ጥያቄያቸውን በማቅረብ የህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብት ተከብሮ ለማንነታቸው እውቅና እንዲሰጥ ለጠየቁ ተወካዩች ምክር ቤቱ በሰጠው ምላሽ ‹‹እንዲህ አይነት ጥያቄዎች በመጀመሪያ በክልሉ በሚገኙ የተለያዩ የመስተዳድር እርከኖች ቀርበው መፍትሔ የሚሰጣቸው ሲሆን ቀጥታ ለምክር ቤቱ የማይቀርቡ በመሆናቸው በአቤቱታ አቅራቢዎች የቀረበው የማንነትና ሌሎች ተያያዥ የመብት ጥያቄዎች  በክልሉ መፍትሔ እንዲሰጠው የመለስን መሆኑን እናስታውቃለን››ማለቱን ከምክር ቤቱ የወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
ምክር ቤቱ የተቋቋመው እንዲህ አይነት ህገ መንግስታዊ ጥያቄዎችን በመመርመር አቤቱታዎቹን በመከታተልና የህገ መንግስት ትርጓሜ በመስጠት ጥያቄዎቹ አግባብ ባላቸው ደረጃዎች የሚመረመሩበትንና እልባት የሚያገኙበትን መንገድ ለማመቻቸት ቢሆንም ምክር ቤቱ ጉዳዩን የማንነታችን ተጨፍልቆ የሌሎችን ማንነት እንድንለብስ አድርገውናል በማለት ወደሚከሷቸው መስተዳድሮች ዘንድ ሄዳችሁ ጉዳያችሁን አሳዩ ማለቱ ነገሩን አስገራሚ ያደርገዋል፡፡


No comments:

Post a Comment