የኢትዮጵያን የባሕልና ስፖርት ፌዴሬሽንን (ESNFA) በአላሙዲ ገንዘብ ለወያኔ ለመሸጥ የሸረቡት ሴራ በአገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን መና የቀረባቸው ጥቂት ሆዳሞች “ኤሳ ዋን” የሚባል የማወናበጃ ተቋም አዘጋጅተው ለማደናገር ካለፉት 5 ዓመታት አንስተው የተለያየ ዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደቆዩ ይታወቃል። ሆኖም ሕዝብ ኃይል ነውና “ውሾን የነካ ውሾ” ብሎ ወያኔን የነካ ወያኔ ነውና ህዝብ ጠልቶና ንቆ ጢቅ ስላለባቸው ባዶ የት/ ቤት መጫወቻ ሜዳ ታቅፈው ቀርተዋል። ከአምስት ዓመታት በፊት በፍርድ ቤት ከተሸነፉ በኋላ በተንተራሱት ከኢትዮጵያ የተዘረፈ ገንዘብ ተማምነው በዲሲ ከተማ ውስጥ በሚገኘው 45,000 በላይ ተመልካች በሚያስተናግደው RFK ስታዲዮም ውስጥ ውር ውር ብለው በስቴዲዮሙ ታሪክ እጅግ አነስተኛውን የተመልካች ቁጥር አስመዝግበው አልፈዋል። እስቴዲዮም ውስጥ ማዘጋጀቱ በተመልካች ድርቅ መመታታቸውን ስላሳበቀባቸው በትንንሽ የት/ቤቶች የልጆች መጫወቻ ሜዳ ቢያደርጉም በዚህም ብቅ የሚል ተመልካች ስለጠፋ ኢትዮጵያዊ ያልሆነውን በማስገባት ነጻ የሙዚቃ ትርዒት ከነጻ ምግብና መጠጥም ጋር ግብር በማስገባት ቦታዎችን ሙሉ አድርገው ለማሳየት ያደርጉት ሙከራም በሚያሳፍር ሁኔታ መክኖባቸዋል። ዘንድሮም “የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ” እንደሚባለው ያዘጋጁት ድግስ መብከቱን የሚያሳይ ECADF የለቀቀውን ቪዲዮ ለመመልከት አዚህ ላይ ይጫኑ።
No comments:
Post a Comment