Wednesday, July 13, 2016

የጎንደር ህዝብ ቁጣ አልበረደም፤ ህዝባዊ አመጹ ለሁለተኛ ቀን ቀጥሏል


Colonel Demeke Zewdu
ትናንት እስከ ምሽቱ አራት ሰአት በተደረገው የተኩስ ልውውጥ በርካታ የህወሃት ታጣቂዎች ተገድለዋል። ጥቃቱን የፈጸሙት የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢዎችን ለመታደግ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ጎንደር ከተማ የገቡ ነዋሪዎች ናቸው። በተኩሱ ልውውጥ መሃል ከወልቃይት ጠገዴ ጥያቄ አቅራቢዎች መካከል አቶ ሲሳይ ታከለ፣ አቶ ሰጠኝ፣ አቶ አለቃ እስበሶም እና ሌሎች ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎችም ሲገደሉ፣ በፌደራል ፖሊስና በህወሃት ደህንነት አባላት በኩል ደግሞ በርካታ ወታደሮች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። በርካታ ወጣቶች እንደተገደሉም መረጃዎች እየወጡ ነው።
ተቃውሞው ዛሬም የቀጠለ ሲሆን አንድ የህወሃት የንግድ ድርጅትና አንድ የፌደራል ፖሊስ መኪና መቃጠላቸው ታውቋል።በተጣቂዎች ተከበው የነበሩት ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ እርሳቸውን ሊረዱ በመጡ ሰዎች ታግዘው እየተኮሱ ማምለጣቸውን እየተነገረ ነው። ከጎንደር ከተማ ወደ አጎራባች ከተሞች ተዛምቱዋል። አዘዞ ተቃውሞው በርትቱዋል።
መንገዶች አሁንም እንደተዘጉ ናቸው። የጥይት ድምጽ እዚህም እዚያም ይደመጣል። የአዘዞ ነዋሪ እንደነገረኝ በመንግስት ጸጥታ ኃይሎች በጥይት ዘመዶቻቸው የተገደሉባቸው ወጣቶች ተቃውሞዎችን በማስተባበር ላይ ናቸው። የህዝብ ቁጣው ቶሎ የሚበርድ አይመስልም ይላሉ የአካባቢው ምንጮች።

No comments:

Post a Comment