Monday, July 18, 2016

ወደ ጎንደር ሲሰማሩ ከሻእቢያ ጋር ለመዋጋት ነው ተብለው የተገደሉ የፌዴራል ፖሊሶች ፎቶዎች


እነዚሁ ሰሞኑን በጎንደር የተገደሉ የፌዴራል ፖሊሶች ናቸው።
ወደ ጎንደር ሲሰማሩ አብዛኞቹ ከሻእቢያ ጋር ለመዋጋት ነው ተብለው ነው የመጡት። እዉነቱ፣ ሚሽናቸው ሳይነገራቸው። ተዋሽተው። በቦታው ሲደርሱ ግን አድርጉ የተባሉት ሕዝባቸው ላይ እንዲተኩሱ ነው። ያሳዝናል። ይሄ ሁሉ መሆን አለነበረበትም። ወደዚህ ደረጃ መደረስ አለነበረብት። ህወሃቶች እንጥፍጣፊ የሰላምና የ እርቅ መንፈስ ቢኖራቸው፣ ትንሽ እንኳን ከጥጋባቸው በረድ ቢሉ፣ ያሉ ችግሮችን በሰላም፣ በዉይይት መፍታት ይቻል ነበር።
ግን ሰዎቹ አጋንንት የሰፈረባቸው ጥቅማቸውንና ስልጣናቸው ይጠበቅ እንጂ ለማንም ደንታ የሌላቸው ጭራቆች በመሆናቸው አገር ትታመሳለች።
እነርሱ ለጆቻቸው ጋር እረፍት ዱባይና ፓሪስ ይሄዳሉ፤ የነዚህ ፖሊሶች ልጆች ግን ከዚህ በኋላ ያለ አባት ያድጋሉ። ያሳዝናል። ልብን ያደማል።

No comments:

Post a Comment