የእስራኤሉ ጠ/ሚ ቢኒያሚን ናታኒያሁ ነገ አፍሪካ ይገባሉ!!! 4 የ እስራኤል አየር ሃይል አውሮፕላኖች ለዚህ በይዘቱ ልዮ ለሆነ ጉብኝት ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል። ጉብኝቱ የአፍሪካ አገራትንና የ እስራኤልን ግኑኝነት በብዙ ዘርፉ ያጠናክራል ተብሎ ይታሰባል ለዚህ ጉብኝት እስራኤል ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ወጭ አድርጋለች የሜዳ ላይ ሆስፒታሎች በአደጋ ግዜ የሚከፈቱ ሆስፒታሎችንም ጨምሮ ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ጉብኝቱ በሰላም ከተጠናቀቀ በኋላ እንደ ስጦታ ለአፍሪካ አገራቶች ይለገሳሉ ተብሏል። በዚህ ጉብኝትም ለመጀመሪያ ግዜ በአሸባሪዎች እጅ ተጠልፎ ወደ ኡጋንዳ እንዲያመራ የተደረገውን አውሮፕላን ሙሉ የ እስራኤል ዜጎችን ይዞ አንቴቤ እንዲያርፍ ቢደረግም በጠ/ሚንስትሩ ወንድም ዮኒ ናታኒያሁ መሪነት ኡጋንዳ ኤርፖርት በተደረገ ኦፕሬሽን (operation entebbe) ወንድማቸው ህዝባቸውን ከአሸባሪ እጅ ካስለቀቁ በኋላ በጠና ቆስለው ወደ እስራኤል በበረራ ወቅት በነበሩበት ግዜ ሊያርፉ ችለዋል። ይህን ታሪካዊ ቦታም ከተዋጊ የኮማንዶ ቤተሰቦች ጋር ለመጀመሪያ ግዜ ይጎበኛሉ። በስተመጨረሻም ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ … ለዚህ የጉብኝት ግዜ እጅግ ስልጡን የድህንነት ሰዎች ኢትዮ- እስራኤሎች ትልቅ ሚና እንደሚጫወቱም የውስጥ አዋቂዎች ተናግረዋል።
No comments:
Post a Comment