የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ኣገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ የመሰከረበት ሰልፍ
ፖለቲከኞችን ያሳፈረው ሕዝብን ያነገሰው ዛሬ በጎንደር የተካሄደው ሰልፍ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ሂደት ውስጥ ራሱን የቻለ ጫና እንዳለው ያረጋግጣል።ሕዝብ በራሱ ያሰናዳውና የተሳካ ታላቅ ሰልፍ በጎንደር ደሞቆ ውሏል።ሕዝባዊ ኣንድነት ጎልቶ የታየበት የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ኣገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ የመሰከረበት ሰልፍ ነበር፤የሕወሓት ኣገዛዝ በቃኽን የተባለበትም ሰልፍ ነው፥ ሚሊዮኖች ኣደባባይ ወጥተው ወያኔን ልክ እንደሚያስገቡት ነግረውታል።
ሕዝብን በሃይማኖት ለመከፋፈል ሞከሩ ኣልተሳካም። ሕዝቡ ሃይማኖታችንን እንደያዘን የሌላውን ኣክብረን ቤታችን በታቸው ሆኖ የኣንዱ ደስታና ሃዘን የኣንዳችን ሆኖ በተሳሰረ የኢትዮጵያዊነት ሰንሰለት ላይፈታ ታስሯል ብሎ በተደጋጋሚ እያረጋገጠ ነው። የብሄረሰብ መብት ሽፋን በሚል ኣንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ ኣድርጎ ለማቅረብ ቢሞክርም ሰሚ ጆሮ ኣላገኘም ወያኔከኦሮሞ ሕዝብ ጎን መቆሙን ኣማራው በተግባር በሚሊዮኖች ድምጹ ኣረጋግጧል፤ በሕዝብ ዘንድ ጥላቻና ዘረኝነት እንዳሌለ የጎንደሩ ሰልፍ ለገዢዎች ኣሳይቷል። ችግሩ ወያኔና ፖለቲከኞቹ እንደሆኑ እንጂ በሕዝቦች መካከል ችግር እንደሌለ ኢትዮጵያዊነት እንዳስተሳሰረ በተግባር ከመመስከሩም በላይ የወያኔን ባንድራ ተቀባይነት እንዳሌለው ታይቷል በጎንደሩ ሰልፍ።
No comments:
Post a Comment