የጎንደር ህዝብ ቃሉን ጠብቆ አደባባይ ወጥቷል። (የጎንደር ዘገባ)
የጎንደር ከተማ በሰላማዊ ሰልፈኞች ተጥለቅልቃለች ሕዝቡ ወደ መስቀል ኣደባባይ መጓዙን ይዟል ። የሕወሓት ወታደሮችና ፖሊሶች በግርምት ኣፍጥጠው እያዩ መንገድ እየዘጉ ሰልፈኛውን ለመቁረጥ ጥረት እያደረጉ ነው። ፤በፍርሃት እንዳይወጣ እያደረጉት ያለው ሕዝብ በልበሙሉነት ኣደባባዩ በሚሊዮኖች እየሞላ ነው፤የኢንተርኔት ኣገልግሎት ኣይሰራም።
የወልቃይት ጉዳይ የኣማራና የኣማራነት ማረጋገጫ እንደሆነ በተግባር እየታየ ነው። አትነሳም ወይ አትነሳም ወይ ይሄ ባንዲራ ያንተ አይደለም ወይ በሚለው ከፍተኛ ጩሀት ያሰማል የክልሉ ፓሊስ ከህዝብ ጋር ሙሉ ለሙሉ ተቀላቀለ አንድነት ሀይል ነው ህዝብ ሀይል ነው።ሁለም አቅጣጫ በተለይም በፒያሣ አካባቢ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሠልፋ ታዳሚ በመፈክሮችና በቀሥቃሽ ሙዚቃዎች ታጅቦ ወደ መሥቀል አደባባይ እየተመመ እንደሚገኝ የሠልፋ ተሣታፊ ከሥፍራው ነግሮኛል።ከኦሮሞ ሕዝብ ጎን መቆሙን ኣማራው በተግባር በሚሊዮኖች ድምጹ ኣረጋግጧል፤ በሕዝብ ዘንድ ጥላቻና ዘረኝነት እንዳሌለ የጎንደሩ ሰልፍ ለገዢዎች ኣሳይቷል። ችግሩ ወያኔና ፖለቲከኞቹ እንደሆኑ እንጂ በሕዝቦች መካከል ችግር እንደሌለ ኢትዮጵያዊነት እንዳስተሳሰረ በተግባር ከመመስከሩም በላይ የወያኔን ባንድራ ተቀባይነት እንዳሌለው ታይቷል በጎንደሩ ሰልፍ።
የአማራ ክልል ልዩ ሀይል ከሥፍራው እንደሌሉ እና አጋዚ ግን ከትናንት ጀምሮ ቢኖርም ህዝቡ ፍጹም ጨዋነት በተሞላበት ሠላማዊ መንገድ የሠልፉን ግብ ልማሣካት እርብርብ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ችያለሁ።
ሰልፋን እየመሩት የሚገኙት የሀይማኖት አባቶች(የክርስትያኑ እና የሙስሊሙ) ሲሆኑ ምንም የሌለው የኢትዬጽያ ባንዲራ እየተውለበለበ ይገኛል፡፡ በዚ ሰዓት አንድም ፌደራል አይታይም፡፡ አሁን የሚሰማኝ ስሜት ልክ አባቶቻችን ጣልያንን ሲያሸንፉ፤ ልክ እንደ አድዋ ድል በማለት ደስታውን ገልፆልኛል፡፡ በቦታው ኮረኔል ደመቀ የላከው መልክት ሊነበብ እንደሆነም ገልፆልኛል፡፡
በአደራ የሰጠናችሁን ልጃችን ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን መልሱልን!
በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ
በአደራ የሰጠናችሁን ልጃችን ኮለኔል ደመቀ ዘውዱን መልሱልን!
በግፍ የታሰሩ የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ይፈቱ
No comments:
Post a Comment