Sunday, July 17, 2016

የወያኔን አገዛዝ (ፀረ ሕዝብ) ወረራ ለማስቆም በመቻቻል ተባብረን መታገል አለብን::


የወያኔን አገዛዝ (ፀረ ሕዝብ) ወረራ ለማስቆም በመቻቻል ተባብረን መታገል አለብን:: የሕወሓት አገዛዝ ባለፉት 25 አመታት ከፍተና ወንጀሎችን በሕዝብ ላይ ፈጽሟል::ይህ የማይካደዉን ሃቅ በላዩ ላይ የተጫነበት ሕዝብ ዘግይቶም ቢሆን ብሶቱን አደባባይ በመውጣት በተቃውሞ እየገለጽ ይገኛል::ካለምንም የፖለቲካ ድርጅት አደራጅነት ካለምንም ቀስቃሽ እና መሪ ሕዝብ አደባባይ የወጣው ብሶቱ ገንፍሎ መሆኑን የሚታወቅ ጉዳይ ነው::ለዚህ ደግሞ የሕዝብ ትግል አብዮት ትግሉን የሚያቀናጅ እና የሚያስተባብር አንድ የሚያደርግ ጠንካራ የለውጥ ሃይል ያስፈልጋል::
በኦሮሚያ ክልል ከዚያም ተከትሎ በአማራው ክልል የተነሳው የሕዝብ ብሶት የወለደው እምቢተኝነት የሚያመለክተው ነገር ቢኖር ሕዝቡ ሕወሓት መራሹን ዘረኛ አገዛዝ እንደማይፈልግ እና በፖለቲካና በኢኮኖሚ ተደቁሶ መማረሩ ነው::ከኦሮሚያና ከአማራ ሕዝብ ሌላ በጋምቤላ በውስን ትግራይ እንዲሁም በኮንሶ እና በደቡብ ኦሞ ብሎም በደቡብ ምእራብ የሃገሪቱ ክፍሎች የሕዝብ እምቢተኝነቶች የተቀሰቀሱ ሲሆን አሁንም እንዳረገዙ ሲገኙ በኦጋዴን የሕዝቡ ለመብቱና ለነጻነቱ እምቢ ማለቱን የሚያሳዩ የተዳፈኑ ፍሞች መኖራቸው እሙን ነው::
Minilik Salsawi's photo.
ብንተነትነው እጅግ ብዙ የሚሆነውና በአጭሩ ሕዝቡ ለውጥ የሚያስፈልገው መሆኑን እየገለጸበት የሚገኘው ተቃውሞ አንድ የጋራ ሃይል የሆነ አስተባባሪ ይፈልጋል ይህንን አስተባባሪ ሃይል መመስረት መገንባት እና በፈጣን አብዮት ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በመቻቻል ተባብረን መታገል ስንችል ብቻ ነው::በመቻቻል ተባብሮ ማታገል መታገል የማይቻል ከሆነ የሕዝብ ብሶት የወለዳቸው እንቅስቃሴዎች ተዳፍነው ሊጠፉ እደሚችሉ ካለፉት ታሪኮን መማር አለብን::የለውጥ ሃይል ነኝ የሚል ሁሉ በዚህ የጋራ ትግል ማቀናጀት ዙሪያ ሊተባበር እና ጠንካራ የሆነ የጋራ ድርጅት በመመስረት የሕዝብን ታማኝነት ሊያገኝ ይችላል::ለውጥ ማምጣት የምንችለው ራሳችን ተቻችለን እና ተከባብረን በጨዋለት ስልሰራ እንጂ የምእራባውያንን ደጅ ስናጨናንቅ አለመሆኑን ልናውቅ ይገባል::ምእራባውያን ብሄራዊ ጥቅማቸውን ስለሚፈልጉ የሃይል ሚዛን ወዳለበት ስለሚያጋድሉ አስተማማኝ አይደሉም ለትግላችንም ዋስትና ሊሆኑን አይችሉም::ለትግላችን ዋስትና የሚሆነን ሕዝብ መሆኑን ልናውቅ ይገባል::ስለዚህ ለጣንካራ መሰረት እና ለሕዝባዊ ትግል ድል የወያኔን አገዛዝ (ፀረ ሕዝብ) ወረራ ለማስቆም በመቻቻል ተባብረን መታገል አለብን:

No comments:

Post a Comment