Wednesday, July 27, 2016

አቶ በረከት የመሩት ስብሰባ እንደተለመደው በታቃውሞ ፣ በምሬትና በማስጠንቀቂያ ተጠናቀቀ


አቶ በረከት ስምዖን የመሩት ስብሰባ እንደተለመደው በታቃውሞ ፣ በምሬት እና በማስጠነቀቂያ ተጠናቀቀ።የጎንደር አማሮች ዛሬም አቶ በረከትን ቁጭ አድርገው ያለፍርሃት በልበ ሙሉነት ብሶታቸውን ተናግረዋል። ተሰብሳቢው አንድ በአንድ እዬተነሳ የተቃውሞ ውርጅብኝ ሲያዘንብባቸው አቶ በረከት ትንፋሻቸውን ዋጥ አድርገው ሲያዳምጡና ማስታወሻ ላይ ሲቸከችኩ ውለዋል።
የህወሓት የበላይነት እስከ መቼ? ከአሁን በኋላ ኢህአዴግ አብቅቶለታል ፣ ኢህአዴግ የጎንደር እናቶችን ደም እምባ ያስነባውን የመላኩ ተፈራን ስራ በሕወሓት አማካኝነት በጎንደር አማሮች ላይ ደጋግሞ እያደረገው ነው ፣ የጎንደር ወጣት 15 ሁኖ ተደራጅቶ ብድር ሲጠይቅ በስንት ልመና 15ሺ ብር ይሰጠዋል ። የትግራይ 5 ወጣቶቸ ግን 500ሺ ብር ወዲያው ይፈቀድላቸዋል። በተበደሩት ብር ጎንደር ላይ መጠው ይነግዱበታል፣ ወንድሞቻችን ከወልቃይት ገፍታችሁ አባራችሁ ጎንደር መጠው ቢጠጉ ህዝብን ንቃችሁ አፍናችሁ ወስዳችሁ ፣ ህወሓት የጎንደር አማራን በደንብ ታውቀዋለች እንግዲህ ይለይልናል ፣ አቶ በረከት እውን ይህን ሁሉ የምንነግርዎትን ለህወሃት ጓደኞችዎ ወስደው ያደርሱልን ይሆን?               አማራ ለኢትዮጵያ የከፈለውን ብድር እንዲህ ነው የምትመልሱለት? የእናንተ ነገር በቅቶናል ፣ ትግላችን በጀመርነው መንገድ እኛው ራሳችን እንወጣዋለን ፣ የታፈኑ ወገኖቻችን በአስቸኳይ ልቀቁ ኋላ በራሳችሁ ላይ ጉድ ሳታመጡ… እና ሌሎች መአት የአማራ ብሶቶችና ቁጭቶችን አቶ በረከት ሲጋቱ ውለዋል።
እንዴት ጌታቸው ረዳ የተባለ ጅል የአማራን ህዝብ ሲሰድብ ዝም አላችሁ? እንዴት ብትንቁን ነው ይህን ትንሽ ሰው ሚኒስትር አድርጋችሁ የሾማችሁብን? …በጌታቸው ረዳ ላይ ከቀረቡት አቤቱታዎች ውስጥ እነዚህ ይገኙበታል።አቶ በረከት መጨረሻ ላይ እንዲህ ብለዋል… “አንድ ደብተር ሙሉ ጥያቂያችሁን ፅፌ ይዤያለሁ ፣ ለሚመለከተው አካል ወስጄ አንድም ሳልቀንስ አቀርብና እንወያይበታለን። ከዛ መልሱን ይዤ ወደ እናንተ ተመልሼ እመጣለሁ”። በዚህ ሁኔታ ስብሰባው ተበትኗል ። ሌሎች የቀሩ ነገሮች ካሉ ይዘን እንቀርባለን ።

No comments:

Post a Comment