Monday, July 18, 2016

በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ይቀርብ የነበረው አልሚ ምግብ የውሃ አቅርቦት ተቋረጠ ::


በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ይቀርብ የነበረው አልሚ ምግብ ከተቋረጠ 3 ወር መሆኑን ቦታው ድረስ ተገኝተው ተጎጂዎቹን የጎበኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ተወካዮች ተናግረዋል ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በሶማሌ ክልል ስጢ ወረዳ ሰዴቶ ቀበሌ ድረስ በአካል ተገኝተው ተጎጂዎትን ያነጋገሩት የበጎ አድራጎት ድርጅት ተወካዮች  እንደተናገሩት ተጎጂዎች አሁንም የውሃ አቅርቦት ችግር አለባቸው ሌላም አለብን ያሉትን ችግርም ነግውናል ብለዋል፡፡
የጉብኝቱ አላማም ተጎጂዎቹ ምን ችግር እንዳለባቸ ለማየትና የበጎ አድራጐት ድርጅቶችስ ምን ማድረግ ይጠበቅባቸዋል የሚለውን ለመለየት እንደሆነ ከተወካዮች ሰምተናል፡፡በስጢ ወረዳ ብቻ በድርቅ የተጐጁ የሶማሌ ክልል ነዋሪዎች ቁጥር 475 ሺህ ይደርሳል፡፡ በአካባቢው በጎርፍ የተጐዱ ደግሞ 34 ሺህ አባወራዎች ናቸው ተብሏል፡፡በድርቁም በጎርፉም የተጐዱት በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሚኖሩት ከመንግሥት ከሚሰጣቸው የምግብ እርዳታ ነው፡፡ከእርዳታ እህል በተጨማሪ የአልሚ ምግብ የሚሰጣቸው ህፃናት፣ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች ሲሆኑ ቁጥራቸውም 55 ሺህ እንደሚሆን ሰምተናል፡፡

No comments:

Post a Comment