Saturday, July 16, 2016

ጭካኔ የተሞላበት ግፍ የወለደውን ሕዝባዊ አመጽ፣ ተመሳሳይ ጭካኔና ግፍ አያቆመውም! ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት


ጭካኔ የተሞላበት ግፍ የወለደውን ሕዝባዊ አመጽ፣ ተመሳሳይ ጭካኔና ግፍ አያቆመውም!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት
ጭካኔ የተሞላበት ግፍ የወለደውን ሕዝባዊ አመጽ፣ ተመሳሳይ ጭካኔና ግፍ አያቆመውም!
የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና አርምጭሆ ወረዳ ነዋሪ የዐማራ ነገድ ሕዝብ ፣በዘረኛው የትግሬ ወያኔ ከ1972 ዓም እስከ ዛሬ ድረስ የማያባራ ፣አሰቃቂ፣ ሰቅጣጭና አሳዛኝ ግፍ ፈጽሞበታል። እየፈጸመበትም ይገኛል። በሽዎች የሚቆጠሩትን በአሰቃቂ ሁኔታ አሥሮና አሰቃይቶ ገድሏል። አያሌዎች ዐማራ በመሆናቸውና በኢትዮጵያ አንድነት ማመናቸው እንደወንጀል ተቆጥሮባቸው በግፍ በመሬት ውስጥ እስር ቤቶች ያለፀሐይ ብርሃን ለዘመናት ታስረው ተሰቃይተዋል። በርካታ የወልቃይት፣ ጠገዴ እና ጠለምት ነዋሪ አዛውንቶች ንብረታቸውን በወያኔ ተወርሰው ለድህነት ተዳርገዋል። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩት በትውልድ አገራቸው ሠርቶ ለመኖር ባለመቻላቸው ለስደት ተዳርገዋል። በርካታ ልጃገረዶችና የአባወራ ሚስቶች በወያኔ አፋኝ ቡድን ተደፍረዋል። ጥንተ የወረዳዎቹ ነዋሪ የዐማራ ነገድ ተወላጆች አጽመ ርሳታቸውን ተነጥቀው ለትግሬ ሠፋሪ ተሰጥቷል።
የትግሬ ወያኔ በወልቃይ ጠገዴ ተወላጆች፣ ከሁሉም በላይ በዐማራው ነገድ ላይ አንግቦት የተነሳው ፈጽሞ የማጥፋት ዓላማ ፣ዐማራውን በመግደል፣ በማሰር፣ ንብረቱን በመቀማት፣ ከርስቱ በማፈናቀልና በማሰደድ የልቡ አልደርስ በማለቱ፣ የዐማራውን ማንነት ለማስለውጥ የተቀነባበረ ሤራ በመሥራት ላይ ነው። በዚህም መሠረት፣ የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምትን የዐማራ ሕዝብ ማንነት ለማስለወጥ በርካታ የዕመቃ ሥራዎችን በመሥራት ላይ ነው። የማንነታቸው ልዩ መታወቂያ በሆነው የአማርኛ ቋንቋ እንዳይግባቡ እገዳ ጥሏል። ዐማራዊ የሆነ ማናቸውንም ባህላቸውን እናዳይከተሉ ታግደዋል። በአማርኛ መዝፈን፣ ማልቀስ፣ መግጠም፣ መነጋገር እንደከፍተኛ ወንጀል ተቆጥሮ፣ በእነዚህ ሀሳቡን ፣ ምኞቱን፣ ሕልሙን፣ ብሶቱን፣ ደስታውን ለመግለጽ የሞከረ ሰው ይታሰራል። ይገረፋል። የዚህ ሁሉ ድርጊት ግብ፣ ዐማራዊ ማንነቱን በፍርሃት አውልቆ ጥሎ፣ ትግራዊ ማንነትን ቀስ በቀስ ይላበሳል፣ ያን ጊዜ የዐማራ ማንነት በራሱ ጊዜ ይከስማል ከሚል እሳቤ ተነስተው የሚፈጽሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ግልጽ ነው።
ግፍ ግፍን፣ ኃይል ኃይልን ይወልዳል እንጂ፣ ሰላምን አለመውለዱ ይታወቃል። በመሆኑም፣ የትግሬ ወያኔ በጥቅሉ በዐማራው ነገድ ላይ፣ በተናጠል ደግሞ በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለው የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ፣የወንጀሉ ሰላባ የሆነው ሕዝብ ድምፅም ሆነ አመጽ ፈጽሞ ማስቆምና ማፈን አላስቻለውም። ይህም በመሆኑ፣የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ከግድያ፣ ከሀብት ነጠቃ፣ ከእስራትና ከማሰደድ አልፎ፣ ማንነትክን ቀይር የሚለው ሲጨመርበት፣ «ሲበዛ ማር ይመራል! ይኸስ በዛ!» በማለት በሕጋዊ መንገድ ማንነቱን ለማስከበር ከመካከሉ ጉዳዩን የሚከታተሉ ወኪሎቹን መርጦ የማንነት ጥያቄው ሕገመንግሥታችን ነው ባሉት መሠረት መልስ እንዲያገኙ ለሚመለከታቸው አካሎች ሁሉ ጥያቄአቸውን ማቅረባቸው ይታወቃል።
ሕዝቡ ላቀረበው የማንነት ጥያቄ ሕጋችን ነው ባሉት መሠረት መልስ በመስጠት ፋንታ፣ የማንነት ጥያቄ አቅራቢው ሕዝብ ወኪል የሆኑንትን ሰዎች በኃይል አሳዶ በማሰር የማንነቱን ጥያቄ ለማዳፈን ወያኔ በመጣር ላይ ይገኛል። በዚህ ጥረቱም ሰሞኑን የሕዝብ ተወካይ የሆኑትን አንደኛ አቶ አታላይ ዛፌ፣ ሁለተኛ አቶ ጌታቸው አደመ፣ ሦስተኛ አቶ መብራቱ ጌታሁን፣ አራተኛ አቶ አለነ ሻማ የተባሉትን በአቶ ዐባይ ወልዱ የሚመራው የትግሬ አፋኝ ቡድን ከክልሉ አስተዳደር እውቅናና ፈቃድ ውጭ በማን አለብኝነት መታፈናቸው ታውቋል። በሌላ በኩል ይኸው አፋኝ ቡድን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የተባሉትን የሕዝብ ልጅ አፍኖ ለመውሰድ ያደረገው ጥረት ለጊዜው በሰውየው ቆራጥ እርምጃና በሕዝቡ ድጋፍ አለመሳካቱ ታውቋል። የወልቃይት ጠገዴና ጠለምትን ሕዝብ የማንነት ጥያቄ፣ የወያኔ ጭካኔ የተሞላበት ግፍ የወለደው ሕዝባዊ አመጽ በመሆኑ፣ ተማሳሳይ ጭካኔና ግፍ የተቀጣጠለውን ሕዝባዊ ንቅናቄ በፍጹም ሊያቆመው እንደማይችል፣ የጎንደር ከተማና የአካባቢው ከተሞችና ገጠሮች ነዋሪ ሕዝብ እያደረገ ያለው ግፍን የመቃወም እንቅስቃሴ ሕያው ማሳያ ነው። ወያኔ የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላቀረበው የማንነት ጥያቄ መልሱ ኃይል ከሆነ፣ ሕዝቡ ኃይልን በኃይል መክቶ ማንነቱን እንደሚያስከብር ለቅንጣት ታክል መጠራጠር አይቻልም። የሕዝቡ ጉዞና የእንቅስቃሴው መቀጣጠል የሚያመራውም ወደዚያ ነው።
ይህ እንቅስቃሴ በሕዝቡ አሸናፊነት እንዲደመደም፣ መስዋዕትነቱን ቀንሶ፣ ጊዜውን አሳጥሮ፣ ድሉን በተፋጠነ መንገድ ለመቀዳጀት የዐማራው ነገድ በያለበት ይህን እንቅስቃሴ በሞራል፣ በገንዘብ፣ በመረጃ ልውውጥ፣ በሀሳብ ወዘተ ያልተቆጠበ ድጋፉን ሊሰጥ ግድ ያላል። መስዋዕትነት የጥቂቶች፣ ድል ግን የሁሉም ወይም የብዙዎች መሆኑ ቢታወቅም፣ የድሉ ተጠቃሚ የሆነው የዐማራው ወገን ለመስዋዕትነት የተዘጋጁትን ወንድም እህቶቻችን የመሰዋት ዕጣ የመቀነስና የትግሉን ጉዞ ማሳጠር ይጠበቅብናል። ከሁሉም በላይ በብአዴን ውስጥ ያላችሁ የዐማራ ልጆች፣ የትግሬ ወያኔ ፍላጎት ማስፈጸሚያ ከመሆን መቆጠብና የትግሉ አካል የምትሆኑበትን መንገድ መሻት ልታልፉት ከማያስችላችሁ ወቅት ላይ አለመሆናችሁን አውቃችሁ፣ ከሕዝቡ ጎን እንድት ቆሙ ትጠየቃላችሁ። ይህን ሳታደርጉ ቀርታችሁ፣ ለወያኔ ዓላማ ማስፈጸሚያ እጀታ መሆናችሁን ከቀጠላችሁ፣ ከወያኔም ከወገናችሁም ሳትሆኑ፣ የባሕር ላይ ኩበት የመሆን እጣችሁ የሠፋ ሊሆን እንደሚችል ልብ ልትሉት ይገባል። በፖሊስና በመከላከያ፣ እንዲሁም በስለላው መዋቅር ውስጥ ያላችሁ የዐማራ ነገድ ልጆች፣ «ከባዕድ ቆርሰህ፣ ወደ ወገንህ ዙረህ ጉረስ» ነውና፣ ይህ ወቅት፣ ዕውነተኛ ማንነታችሁ የሚፈተንበት መሆኑን አውቃችሁ፣ የወገናችሁ መቁረጫና መፍለጫ ከመሆን ትቆጠቡ ዘንድ ትጠየቃላችሁ። እንደተለመደው የእጀታነት ተግባራችሁን የምትፈጽሙ ከሆነ፣ በራሳችሁ ብቻ ሳይሆን፣ በትውልዳችሁ ላይ ምንጊዜም የማይረሳና ይቅርታ የሌለው ስሕተት የፈጸማችሁ እንደሆነ እንድትገነዘቡ እንሻለን።
የትግሉ ባለቤት የሆንከው የወልቃይት፣ ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ፣ «ደም ተቀብቶ፣ ዝንብ አይፈሩም» ነውና ከእንግዲህ ወደፊት እንጂ፣ ወደኋላ የለም። ገጥመናልና ጊዜው ይርዘም ወይም ይጠር፣ የምንከፍለው መስዋዕትነት ይክበድም ይቅለል ድሉ የናንተ እንደሚሆን ጥርጥር የለንም። እናንት የነጣሰው ጎበዜ፣ የራስ ወልደሩፋኤል፣ የነራስ ገብሬ፣ የነደጃዝ ኃይለማርያም ፣የደጃች ውቤ፣ የነቢትወደድ አዳነ፣ የነደጃዝማች ብሬ ዘገየ፣ የፊታውራሪ ሽፈራው ጌታሁን(አባከንትር)፣የነራስ አሞራው ውብነህ፣ ከሁሉም በላይ የቴዎድሮስ ልጆች የሆናችሁ ጀግና የጀግና ልጆች የአባቶቻችን ልጆች ሆኖ ለመገኘት፣ ይህን የተቀጣጠለውን ትግል በድል ለመወጣት ከምንጊዜውም በበለጠ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ፣ የዘረኛውን ትግሬ አገዛዝ ገፍትሮ ለመጣል በኅብረት እንነሳ።
ወያኔ እንደሚለው ዐማራው የተከፋፈለና የማይተባበር አይደለም። ዐማራው ለራሱ ኅልውና ቀርቶ ለሌሎች ነፃነትና ደኅንነት ሕይዎቱን የሚሰጥ መሆኑ ታሪኩ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። በመሆኑም የአባቶችህን ወኔ ተላብሰህ፣ አባቶቻችን ለማስተዳደር ሲሉ በከለሉት አስተዳደራዊ ክልል ራስክን ሳትገድብ፣ የዐማራው አንገት አንድ ነውና በሸዋ፣ በጎጃም፣ በወሎ፣ በሐረር፣ በአዲስ አበባ፣በደቡብ፤ በምዕራብ እና በዓለም ዙሪያ ያለህ የዐማራ ነገድ ልጅ፣ የተፋፋውን የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ ተገቢ ምላሹን እንዲያገኝ የምትችለውን ሁሉ ለማድረግ ኅሊናህን ከማዘጋጀት አልፈህ በተግባር እንድትንቀሳቀስ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት በወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄ አቅራቢ ሕዝብ ስም ጥሪውን ያቀርባል። ከሁሉም በላይ ለኢትዮጵያ አንድነት፤ ለሕዝቡ ሉዐላዊነት እና ለአገሪቱ ብሔራዊ ጥቅም መከበር በተለያየ መልክ ተደራጅታችሁ የምትታገሉ ወገኖች ከወልቃይት ጠገዴ የምንነት ጥያቄ አቅራቢ የዐማራ ልጆች ጎን እንድትቆሙ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ጥሪውን ያቀርባል።
የሕዝቡ ትግል ያሸነፋል!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

No comments:

Post a Comment