Tuesday, July 19, 2016

የአማራ ህዝብ ወዴት እንዲሄድ ነዉ የምትፈልጉት ?‪



– ለጊዜዉ በአረብ ዶላር እርዳት እንዲሁም የአረብ አሽከር ሆነዉ:አገር አፍርሰዉ:የአለም አቀፍ ቅጥረኛ ሆነዉ እና የኢትዮጵያ ጠላቶ በጣሉላቸዉ ፍርፋሪ ድጋፍ ስልጣን ስለያዙ እብጠት ሊገላቸዉ ደርሶ አማራን አከርካሪዉን ሰበርንዉ ሲሉ አዋጅ አስነገሩ::ድንቁርና ልክ አለዉ::እነዚህ ወያኔዎች ግን ድንቁርናቸዉ ተሰፍሮም ተለክቶም አያልቅም::
አማራን አከርካሪዉን ሰበርነዉ ብለዉም አልበቃቸዉም::አማራ ላይ የዘር ፍጅት ይደርስበት ዘንድ ልዩ ልዩ የኢትዮጵያ ጎሳዎችን በአማራ ህዝብ ላይ ቀሰቀሱበት::በአማራ ላይ ከፍተኛ የጥላቻ ፕሮፖጋንዳ ሰሩ:: ደጋግመዉ ደጋግመዉም የአማራን አክርካሪ ሰበርነዉ እያሉ ከበሮ ይዘዉ ድለቃ ቀጠሉ::
-ህዝብ እንዴት ይሰበራል? ትዉልድ እንዴት አከርካሪዉ ይመታል? እንኳን እንደ አማራ በብዙ ዉቃያኖስ ዉስጥ ለሽህ እና ሽህ ዘመናት በመከራ ዉስጥ እየቀዘፈ ህልዉናዉን ያስከበረ ዉስብስብ ህዝብ ይቅርና ማንንም ህዝብ እንዲህ አይነት የድንቁርና ንግግር መናገር አይገባም ነበር::እነዚህ ከንቱዎች ግን በአጋጣሚ ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በባንዳነት ተወዳጅተዉ ባገኙት ድል ሰክረዉ ብዙ መርዛማ ንግግር ተናገሩ::የሚያስገርመዉ ዛሬም የሚማር ልብ የላቸዉም::ያንኑ ድንቁርናቸዉን ያላዝናሉ::
-ትናት የአማራን ህዝብ አከርካሪ ሰበርን ሲሉ መርዛቸዉን ረጭተዉ ልባችንን ያደሙት ወያኔዎች ዛሬ ደግሞ ህዝባችንን በጅምላ አሸባሪ ይሉ ይዘዋል:: እንዴት ህዝብ መብቱን ስለጠዬቀ አሸባሪ ይባላል? እንዴት ህዝብ ዲሞክራሲያዊ መብቱን በመጠዬቁ በጠላትነት ይፈረጃል?
– የአማራ ህዝብ ምን እንዲያደርጋችሁ ትፈልጋላችሁ? የአረብ እና የኢትዮጵያ ጠላቶች ቅጥረኛ ሆናችሁ ስልጣን ስትይዙ የአማራን አከርካሪ ሰበርን እያላችሁ በመቶ ሽህ አማሮች ፈጃችሁ አስፈጃችሁ::ይሄ አልበቃ ብሏችሁ በመላ ሀገሪቱ የሚኖረዉን አማራ ከአባቶቹ ሀገር ከኦሮሚያ: ከደቡብ: ከቤኒሻንጉል: ከጋምቤላ : ከአፋር እና ከሶማሌ እንዲባረር: እንዲፈናቀል: ንብረቱ እንዲወድምበት ብሎም አማራ እንዲታረድ ሁሉን ደባ እና ተንኮል ሰራችሁበት::ለይስሙላ የጻፋችሁትን ህገ መንግስት እንኳን በአማራ ህዝብ ላይ እንዲደረመስበት አደረጋችሁ::የራሳችሁን ህገመንግስት እያጣቀስን በፌደረሼን ምክር ቤታችሁ ብንሞግታችሁ ጆሮ ዳባ አላችሁ::
-እሽ የአማራ ህዝብ ወዴት እንዲሄድ ነዉ እቅዳችሁ? ከመላ ሀገሪቱ አባረራችሁት::የዘር ፍጅት ፈጸማችሁበት::ጎንደርን ለሱዳን ሰጣችሁበት::ወልቃት ሀገሬ ነዉ እንዳይል ከእነ ማንነትህ አማራ ሆነህ በወልቃይት አትኖርም::በወልቃይት ለመኖር ከፈለግህ እኛ የምንመርጥልህን ማንነት መልበስ አለብህ አላችሁት:: እሽ ይሄ ህዝብ ወዴት ይሂድ? አሁን ለዚህ ጥያቄ ትከሻችሁን ከፍ ዝቅ እያደረጋችሁ መልስ እንደምትሰጡ ልባችሁ ዉስጥ ያለዉን ክፋት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያዉቀዋል:: የረሳችሁት ወይም አዉቃችሁ የረሳችሁት ግን ህዝብን ማሸነፍ እንደማትችሉ ነዉ::
-ህዝብን ማሸነፍ አትችሉም::ህዝብ እንደ ጥልቅ የዉቃያኖስ ምንጭ ነዉ::የሚያፈልቀዉንም ሀይል ማንም ሊገድበዉ አይችልም:: እናንተ ከእዉቀት የተጣላችሁ ስለሆናችሁ ይሄ አይገባችሁም:: ወይም እንዲገባችሁ አትፈልጉም::ህዝብን አከርካሪዉን መስበር አትችሉም:: ህዝብን አሸባሪ ብላችሁ የመፈረጅ ሞራል የላችሁም::ብትፈርጁትም መጥፊያችሁን ከማቃረብ ዉጭ ዋጋቢስ ነዉ::ህዝብ ህዝብ ነዉ::ጥልቅ ዉቃያኖስ::ትዉልድን መገደብ አትችሉም::የትዉልድ ዥረት የሚያሳነሳዉ ማዕበል ጥርግ አድርጎ ይወስዳችኋል::

No comments:

Post a Comment