- የተኩስ ልውውጥ መኖሩን እንጅ ተኩሱ በማንና በማን መሆኑን ማወቅ አልቻሉም። ሌሎች መሥመር ማግኘት የምትችሉ ወይም እዚያው ጎንደር ያላችሁ ልጆች እየተከታተላችሁ ንገሩን።
- ኮረኔሉን ለመውሰድ በሚደረግ ትንቅንቅ ጎንደር ።በወያኔ አስከ ፊጦርነት በአጋዚ ሊከፍት ተዘጋጂቷል።ደም እንደጠማቸው ያስታውቃል ሁሉንም ሰው ለመግደል የፈለጉ ናቸው ይላል መልእክት የላከልኝ ታጋይ። ጎንደር ላይ ስለ አንዣበበው እሳት እንፀልይ።
- ትላንት ማምሻውን ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ ወደ አዲሱ ማረሚያ ወርዷል።በጉዳዮ ላይ ለመምከር ደመቀ መኮንን፣ካሳ ተ.ብርሃን፣በረከት ስሞን፣ገዱ አንዳርጋቸው፣አለምነው መኮንን ጎንደር ከተማ ይገኛሉ።”ህዝቡ የሰጠንን አደራ አንበላም”በሚል የከተማው ከንቲባ ተቀባ ተባባልና የዞኑ የጸረ ሽብር ግብረ ኃይል ቡድን መሪ ኮማንደር ዋኛው ከብአዴን አመራሮች ጋር ሙግት ውስጥ ገብተዋል።
- ባለስልጣናቱ የህዝቡን ትርታና የአካባቢውን ሁኔታ ቢገመግሙም ለውሳኔ የተቸገሩ ይመስለኛል።የከንቲባ ጽህፈት ቤት ምንጮቼ እንዳረጋገጡልኝ።የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት የህዝብ ፍላጎት ይከበር እያሉ ይገኛል።የዞኑ ካቢኔ አባላት ከከተማው ባለሥልጣናት ፍላጎት ጋር ባይቃረኑም የላይኞቹን የብአዴን ባለሥልጣናት የልብ ትርታ ማድመጡ ምርጫቸው መሆኑን ምንጮቼ አረጋግጠውልኛል።
- የሆነው ሆኖ አሁን በከተማዋ ውስጥ ከሲቪል ባለሥልጣናቱ በላይ የፖሊስና ልዮ ኃይል መኮንኖች ተሰሚነት አላቸው።ከዚህ ጠቋሚ መረጃ ተነስተን የዞኑ የጸረ ሽብር ግብረ ኅይል ቡድን መሪው ኮማንደር ዋኛውና ጓዶቹ በአቋማቸው መጽናት ከቻሉ ኮለኔሉ ወደ ሰፊው ህዝብ መልሶ የመቀላቀል እድል ይኖረዋል።ይህ ማለት ግን ትግሉ ይቆማል ማለት አይደለም።ምን ግዜም ቢሆን የትግሉን አቅጣጫ የሚወስነው ጨቋኙ ነው።እናም ትጉሉ ህዝባዊ መሰረቱን በማጽናት ወደ ፊት ይቀጥላል።
- በአሁኑ ሠዓት የንግድ ድርጅቶች ሁሉ ተዘግተዋል።ወታደሮች ከነፍስ ወከፍ መሳሪያ በተጨማሪ የቡድን የጦር መሳሪያ (መትረየስ)ይዘው ይታያሉ።በተለይም አራዳ፣ቅዳሜ ገበያ፣ፒያሳ፣ብልኮ፣ስላሴ፣ቁስቋም መስመር፣ልደታ፣18 ማዞሪያ፣ጎንደር ዮኒቨርስቲ፣ዳሽን ቢራ፣አስተዳደር፣ከንቲባ ጽ.ቤት ፣ ሁሉም የግልና የመንግስት ባንኮች በክፍተኛ ጥበቃ ላይ ናቸው።ህዝቡም የሚሆነውን በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።አስፈሪው ነገር ከ”ፍርድ ቤት” ወጣ በተባለ ማደኛ ብዙዎችን ለማፈስ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ነው።ማደኛው ከፌደራል ፍርድ ቤት እንደወጣ ተረጋግጧል።
- ህወሃት በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ለደረሰበት የተዳከመ ቁመና መሪዎቹ በየአደባባዩ የደሰኮሩት እብሪታዊና ህዝብን የሚንቁ ንግግሮች ትልቅ ድርሻ አላቸው።ከአመት በፊት አባይ ጸሃዬ ንቀት በተሞላበት አነጋገር “ልክ እናስገባለን” አለ። የጥቂት አሸባሪዎች ጥያቄ ነው ብሎ አናንቆ ህዝብ ላይ ዘመቱ። ከዛ በኋላ የሆነውን የምናውቀው ነው። ሞክሼው አባይ ወልዱ ከጥቂት ወራት በፊት “በወልቃይት ኮሚቴ ላይ የማያዳግም እርምጃ እንወስዳለን” ብሎ ዛተ። እሱም እንደወዲ ጸሃዬ የጥቂት አሸባሪዎች ጥያቄ ነው ብሎ አናናቀ።
- ከቀናት በፊት ያን ለማስፈጸም በማናለብኝነት የክልሉን ባለስልጣናት እንኳን ሳያማክር ጦር ልኮ የቻለውን ማፈን ቢችልም ሌላ ያልታሰበ እሳት ቀሰቀሰ።እብሪቱም ለጊዜው ተነፈሰ። ዛሬ ህወሃትና ደጋፊዎቹ የእብሪትና የጥላቻ ዛራቸው ተነስቶባቸው ቀን ለሊት የአማራን ህዝብ እየተሳደቡ እያጓሩ ነው። እብሪታቸውና ጥላቻቸው ገደብ አጣ።
Saturday, July 16, 2016
ሰበር ዜና፤ በአሁኑ ሰዓት ጎንደር ውስጥ ፒያሳና አራዳ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ እንደሆነ አሁን በስልክ መረጃ አግኝተናል
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment