Thursday, July 28, 2016

እኛ ያልተሳተፍንበት እኛ ያላቁላላነው ድግስ ሁሉ የጸረ ትግሬ ደናቁርት ነው።(ሕወሓቶች) By ምንሊክ ሳልሳዊ


እኛ ያልተሳተፍንበት እኛ ያላቁላላነው ድግስ ሁሉ የጸረ ትግሬ ደናቁርት ነው።(ሕወሓቶች)
ምንሊክ ሳልሳዊ ሁሉንም ነገር እነሱ ካልተጠሩ ወደ ጥላቻ ይመነዝሩታል .የሕወሓት ኣባላት እና ደጋፊዎቻቸው ስለ ሕዝብ ኣንድነት ስለሕዝብ ነጻነት እና ስለ ሕዝብ ፍቅር ሲሰበክ ያማቸዋል፤ ይብልጡኑ ደግሞ የፈጠራ ታሪካቸውና የጎሳ ፖለቲካቸውን የሚያደፈርስ ሕዝብን የሚያነቃ ሰው ከመጣ ኣለቀለት ይወርዱበታል፥ የሕዝቦች ኣንድነትና ፍቅር ለወያኔ ስልጣን አደጋ ነው። ስለ ኣንድነት ስለ ፍቅር ስለ ነጻነት ስለ ጋራ እድገት ከዘመርክ አንተ የቀድሞ ስርዓቶች ናፋቂና አሽባሪ ጸረ ሕዝብ ነህ በሕወሓቶችና ደጋፊዎቻቸው መንደር፡ማንኛውንም ነገር እነሱ ካልተሳተፉበት መላው ኢትዮጵያ ቢያጨበጭብ መላው ሕዝብ ሆ ቢል ወደ ዘረኝነት ኣጠጋግተው ያጦዙታል።እነሱ ካልተጠሩ ወደ ጥላቻ ይመነዝሩታል
ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ እማ ብሶባቸው ስለ ሕዝብ በደል የጮኸ ሁሉ ጸረ ትግሬ እና ኣሸባሪ ይባላል።ይህን የሚሉት ሕወሓቶች ብቻ እንዳይመስሉህ ሕወሓትን እንቃወማለን የሚሉ የስርዓቱ እድም ማስረዘሚያዎችም ጭምር ናቸው ።ኣንዳንደ የትግራይ ተወላጆችም ዝም ኣላሉም ይህ የሕወሓትና የተጠቃሚዎቹ የዘረኝነት መርዝ ለሃገር በተለይ ለትግራይ ኣደጋ እንደሆነ እየተናገሩ ነው።
በማናቸውም ጉዳዮች ላይ የትግራይ ተወላጆችን ኣሊያም የትግራይ ስም ብሎም የሕወሓት ስም ካልተነሳና የኣገዛዙ ታምቡር ካልጮኸ በጉዳዮች ዙሪያ ስድቡ ዘለፋው የዘረኝነት መርዙ ወዘተ ጋጋታው ከሕወሓት መንደር ለጉድ ነው፥ፕ\ር ፍቅሬ ቶሎሳ ኣማራና ኦሮሞ ከኣንድ ምንጭ ተቀዱ ስላለ ተብሎ የዘረኝነት ከበሮ እየተደለቀ ያለው በሕወሓት ኣባላት ደጋፊዎች እና በጽንፈኛ ኦሮሞዎች መሆኑ ምን ያህል ሕወሓቶችና ፍጥረቶቻቸው በበታችነትና በድንጋጤ እየደነበሩ እንደሚኖሩ ያሳያል።ልብ ያለው ልብ ብሎ ከታዘበ እውነታውን ሳይረፍድ ሊያውቅ ግድ ይላል፤ሕዝቦች በጋራ እንዳይነሩ እርስ በርሳቸው እየተባሉ እንዲያልቁ የተረፉት ደግሞ በሕወሓት ጉያ እንዲወሸቁ ሕወሓት እየሰራ ያለው የክፋት ድርጊት ጦሱ ነገ ከባድ መሆኑ ሊያውቀው ይገባል፤ምልክቶችም እየታዩ ነው። ይህንን መጥፎ የጎሳ ፖለቲካ ኣካል የሆነውን የሕወሓት የዘረኝነት ኣባዜ ተረባርበት በማለዳው ልንቀጨው ይገባል። #

No comments:

Post a Comment