Monday, July 18, 2016

የሕዝብ ዝምታ ግፈኞችን የሚያደለብ ምግብ ነው – ግርማ ካሳ


Girma G. Kassa's photo.
አክብረናቸው ደብዳቤ ስንጽፍላቸው፣ “ወገኖቻችን ናቸው፣ ለሕግ፣ ለሰብአና ቦታ ይሰጣሉ” ብለን ስንቀርባቸው፣ እነርሱ ግን አዉሬ ሆኑብን። ቤቶቻችንና እና እርሻዎቻችንን ለጥቃምቸው ከፈለጉ ለልማት ይፈለጋል ብለው ወስደው መንገድ ላይ ይጥሉናል።። የመብትና የፍትህ ጥያቄ ስናነሳ ፣ ስንጦምር፣ “ሽብርተኞች” ይሉናል። ሕጉን ተከትለን የማንነት ጥያቄ ስናቀርብ የሻእቢያ ተላላኪዎች እንባላለን።
በጎንደር ኮሎኔል ደመቀን ሕወሃቶች አፍነው ወደ መቀሌና ወይም ማእከላዊ ለመዉሰድ እስከአሁን አልቻሉም። ይኸው አምስት ቀናት አለፉ። ህዝቡ በመነሳቱ።
ይሄ ማለት ግን ነገ አይወስዱትም ማለት አይደለም። የሕዝቡ ሁኔታ ይወሰነዋል። ህዝብ ከተዘናጋ፣ ነቅቶ ካልጠበቀ፣ ይህን የሕዝብ ጥያቄ አንስቶ ሲንቀሳቀስ የነበረን ሰው ማእከላዊ ወስደው፣ ጥፍሩን በፒንሳ ይነቅሉታል፤ ትኩስ ዘይት ያፈሱበታል። ይገድሉታል። እኛም በዝምታችን አስገደልነው ማለት ነው።
Girma G. Kassa's photo.
ህዝብ ጉልበት አለው። በአዲስ አበባ ሌላ የሕዝብ ጀግና፣ ሃብታሙ አያሌውም ሕክምና ነፍገዉት በቂም በቀል ወያኔዎች በአሁኑ ሰዓት እያሰቃዩት ነው። ህዝብ ይሄንን መፍቀድ የለበትም። ሕዝብ ወደ አበባባይ መዉጣት አለበት። በሃብታሙ ላይ እየደረሰ ያለው ሰቃይ በሕዝብ ላይ ላለፉት 25 አመታት ሲደርስ የነበረው ስቃይ አመላካች እንደመሆኑ ጨካኝና አረመኔ እንዲሁም ዘረኛ ገዢዎች በቃችሁ ሊባሉ ይገባል። ህዝብ ሃይል አለው።

No comments:

Post a Comment