Tuesday, July 19, 2016

ትግራይ ክልልና የአማራ ነዋሪዎቿ (?) = የሕወሓት መሰሪ ተግባራት

ትግራይ ክልልና የአማራ ነዋሪዎቿ (?) = የሕወሓት መሰሪ ተግባራት
 አንዳንድ ሰዎች በየዋሕነት በትግራይ ክልል የአማራ ሕዝብና ሌሎች ብሄሮች የሚኖር ይመስላቸዋል:: ይህ ትልቅ ስህተት ነው::በዚህ አጋጣሚ ለመናገር ያህል ጠንካራና እና ገፍቶ የሚሄድ የተደረጀ ሃይል ጠፍቶ ነው እንጂ እንደ ሕወሓት ባዶ ልፍስልስና ፈሪ ድርጅት የለም::ከስነልቦና ምናምን የሚለውን ሃተታ ትተን የሕወሓት አስተዳደራዊ ትስስር በትግራይ ክልል እንኳን እናጠፋዋለን ብለው የተነሱት አማራው ይቅርና ሌሎች ብሄሮች አይኖሩም:: አንዳንድ ነጥቦች ለመጥቀስ ያህል:-
1- በ1983 ዓ/ም ሻእቢያ አስመራን ሲቆጣጠር ያባረራቸው የትግራይ ተወላጆች እንዲሰፍሩ የተደረገው በቀጥታ አዲስ አበባ በእርሻ ሰብል መጋዘን ነበር ለምን ይህ ሆነ ለምትሉ ተፈናቃይ የትግራይ ልጆች ከአማራው ከኦሮሞው እና ከሌላው ብሄር ከሆኑ የደርግ ወታደሮች ስለተዋለደ ስለተጋባ እና ግንኙነት ስላለው ብቻ ነው::በመቀሌ እንዲሰፍሩ የተደረጉት የሕወሓት ሰዎች የነበሩና ለሕወሓት ትግል ድጎማ
በአስመራ ስራ ላይ የነበሩ ናቸው:: ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ሁሉ አማራ ብሎ የሚፈርጀው ሕወሓት ለሌሎች ያለውን ከባድ ጥላቻ ነው::
2- በተለያዩ የስራ ምክንያቶች ትግራይ ውስጥ የሚመደቡ የሌሎች ብሄር ተወላጆች የበጎ አድራጎትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅት ሰራተኞች በትግራይ ረዥም ቆይታ እንዲኖራቸው እይፈለግም ሕወሓት በሙያው የሰለጠኑ የትግራይ ተወላጆች ስላሉ በሚል ሰበብ ድርጅቶቹን በማስገደድ ለስራ የላኳቸውን ኢትዮጵያውያን በትግራይ ተወላጆች እንዲቀየሩ ያደርጋሉ::
3- የሕዝብ እና ቤት ቆጠራ ስታስቲክ እንደሚያመለክተው ከ1984 ዓ/ም በፊት በትግራይ የሚኖሩ የሌሎች ብሄር ተወላጆች 35% የነበረ ሲሆን በሶስት አመት በፊት በተካሄደው ጥናት እንደሚያመለክተው ምንም አይነት የሌሎች ብሄር ተወላጆች እንዳሌሉ ሲሆን ለትምህርት ትግራይ ያሉ 3% ሲሆኑ ለስራ ደግሞ 15% መሆናቸውን ስታስቲክ ባለስልጣን እጅ ያለው መረጃ ይጠቁማል:: ከሕወሓት ጫና በተጓዳኝ የትግራይ ክልል ለመኖር ለማረስ ለንግድም ይሁን ለሰው ልጆች ፍላጎት ስለማይመች አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ፊቱን ወድ ክልሉ አያዞርም::
4- በሕወሓት መመሪያ መሰረት ማንኛውም የትግራይ ተወላጅ የሆነ ሰው በተለይ በክልሉ የሚኖር ከሆነ በአጋጣሚ ክልሉ ላይ ከሚመጡ ከሌሎች ብሄር ተወላጆች ጋር እንዳይቀላቀል እንዳይጋባ በንግድ ይሁን በሌላ ግንኙነቶች እንዳይሻረክ ይመከራል::የትግራይ ሕዝብ በደርግ ስለጠጨፈጨፈ ይህንን የጠፋ ትውልድ ለመተካት ከልላ ዘር ጋር እንዳይቀላቀሉ በሕወሓት በተዋረድ ለእያንዳንዱ ይነገረዋል::
5- በምስራቅ አፍሪካ በተለይ በኢትዮጵያ የሕወሓት መራሽ የሆነ የትግራይ ብሄርተኝነት ለማረጋገጥ እያንዳንዱ የትግራይ ተወላጅ በገንዘብና በጦር መሳሪያ እንዲጠናከር እና “የትግራይ አይሁድ” አስተዳደር በመዘርጋት ሌላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ እየደቆሱ ለመግዛትና ዝም ለማሰኘት በትግራይ ውስጥ የነደፉትን እቅድ በተግባር የሚተረጉም ቡድን በስፋት በሃገር ውስጥ እና በውጪ አገር እየሰለጠነ ይገኛል::ይህ እቅድ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በትግራይ ክልል እንዳይሰራ ሲያደርገው ከአማራ ክልል በተነጠቁ መሬቶችላይ ከግብርና ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከጎጃምና ከወሎ የሚመጡ ገበሬዎች በርካሽ ዋጋ በመቅጠር ማሰራት የሚሉ ንድፎችን በመያዝ እየተንቀሳቀሱ ይገናሉ::ወደ ክልሉ ለእርሻ ስራ ለመቀጠር የሚመጡትን ሌሎች ብሄሮች እርስ በርሳቸው እንዲባሉ በማድረግ ንብረቶቻቸውን አግቶ ወደ እስር ቤት በመውሰድና ከአከባቢው ካለክፍያ እንዲባረሩ ማድረግ የሕወሓት ተግባር ነው::
6- ልክ እንደ ወልቃይት እና ጠገዴ ጠለምት የመሬት ዘረፋ ሁሉ በወሎ ራያ እንዲሁም በአፋር ክልል ዘልቀው በመግባት ትግራይን ለማስፋት በፈጠራ ታሪክና በጠበንጃ ሃይል በሆዳሞች ቱማታ እየተጣደፉ ይገኛሉ ይህ ብቻ ሳይሆን የሱዳን መሬት ነው በሚል ሰበብ ከወልቃይት በመተማ የምጥራብ ድንበሩን አስታኮ እስከ ወለጋ ድረስ የትግራይን መሬት የመዘርጋት ሃሳባቸውን ለመተግበር እየተጠደፉ ይገኛሉ::
በአጠቃላይ በትግራይ ክልል ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘው ሕወሓት መራሹ ጸረ ኢትዮጵያውያን መርሃ ግብር በተለይ ፀረ አማራ ፕሮግራም በተግባር ላይ ለማዋል ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ::ለዚህም የሚረዳቸው ታማኝ ይሆነናል ያሉትን ሆዳም ከመግዛት ወደ ኋላ አላሉም በተለያየ ክልልም ይህን የሚተገብር ሆዳም ከጀርባእ የሕወሓት ሰው ታዝሎት እየተሽከረከረ ይገኛል::ከተለያዩ ክልሎች ያሉትን አንጡረ ሃብቶች የሃገራ የሕዝብ ንብረቶች በመዝረፍ ወደ ትግራይ ማሸሽ የተለመደ ተግባር ነው::ይህ የተጀመረው ከመጀመሪያው ቢሆንም አሁን ግን ተባብሶ ቀጥሎ ይገኛል::ሕዝቡ በአሁን ወቅት ነቅቷል::ወያኔ እያዘናጋ የሕዝብን ጥያቄ በማድበስበስ የሚፈልገውን የትግራይ አይሁድ ምስረታ ለማፋተን በመስራት ላይ ቢሆንም ከፊቱ ከሕዝብ የጋራ እንቅስቃሴ ከባድ እና አደገኛ ፈተና ውስጥ ገብቷል::ከዚህ ጎን ለጎን ግን የሕወሓትን እኩይ አገዛዝ የሚቃወሙና ሕዝባዊ መሰረት እንዳሌለው የሚናገሩ ጥቂት የትግራይ ተወላጆች መኖራቸውን ልናስታውስ ይገባል::
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment