Monday, July 25, 2016

በምእራብ አርሲ – ዶዶላ – ሃራሮ – አዳባ – ተቃውሞው በአዲስ መልክ ተቀጣጥሏል::


 : በምእራብ አርሲ – ዶዶላ – ሃራሮ – አዳባ – ተቃውሞው በአዲስ መልክ ተቀጣጥሏል::
በምእራብ አርሲ በዶዶላ ወረዳ በኢዶ ከተማ ከፍተኛ ተቃውሞ እየተደረገ ይገኛል ።ወደ ከተማዋ የሚያስገባ እና የሚያስወጣን መንገድ በመዝጋት እና የኦሮሞን ባንዲራ በመኪናቸው ላይ በማውለብለብ ትግሉን በቁርጠኝነት እያፋፋሙት ይገኛሉ።በአሁኑ ሳአት የተኩስ ድምፅ ከተማዋን እያናወጣት ነው 3 መኪና አድማ በተኝ ፖሊስ ወደ ከተማው ገብቶዋል ።
ወደ ፊንፊኔ የሚወስደው መንገድ ተዘግቶዋል ።ህዝቡ የተለያየ መፈክሮችን እያሰማ ይገኛል በወያኔ መተዳደር አንፈልግም ኦሮሚያ የኦሮሞ ናት ኦሮሞን እየገደሉ ያሉ ለፍርድ ይቀረቡ ኦሮሚያ ደሜን የማፈሰው ላንቺ ነው በማለት እየዘመሩ ከተማውን እየዞሩ ይገኛሉ።

No comments:

Post a Comment