ሕዝብን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሽኩቻ እውን ኣለ ?? ሕወሓት ብአዴንን ሰጥ ለጥ ያደርገው ይሆን??
ኢሕዴን ቆየት ብሎም ብአዴን ብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት የፕሮፌሰሩን በመአሕድ ስም መነሳት ተከትሎ ራሱን የአማራው ወኪል ኣድርጎ ቢሾምም ለኣማራ ሕዝብ የፈየደው ኣንዳችን ነገር የለም። ለላኛው ደግሞ ከዱቄት ተሸካሚዎች እነ ከእንጨት ፈላጮች ከነበሩ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦሕዴድ የኦሮሞን ወጣቶች ሲያስፈጅ እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የጥላቻ መዝሙር ከማስጠናት ውጪ ምንም ኣልፈየደለትም። የነዚህ ሁለቱ ፈጠሪ የሆነው ሕወሓት ከሚዲያ ሰበካ ውጪ የክልሎቹን እነ ሕዝቦቹን ኣንጡረ ሃብት በመዝረፍ የኣመራሮቹን ኪስ ሲያደርብ ትርፍራፊዉን ደሞ ነገን በሙስና ስም ሊወነጅላቸው ለሚፈልግ የብኣዴን እነ ኦሕዴድ ኣመራሮች ከነካድሬዎቻቸው ያበላል።
ኢሕዴን ቆየት ብሎም ብአዴን ብሎ ራሱን የሚጠራው ድርጅት የፕሮፌሰሩን በመአሕድ ስም መነሳት ተከትሎ ራሱን የአማራው ወኪል ኣድርጎ ቢሾምም ለኣማራ ሕዝብ የፈየደው ኣንዳችን ነገር የለም። ለላኛው ደግሞ ከዱቄት ተሸካሚዎች እነ ከእንጨት ፈላጮች ከነበሩ ምርኮኞች የተመሰረተው ኦሕዴድ የኦሮሞን ወጣቶች ሲያስፈጅ እንጂ ለኦሮሞ ሕዝብ የጥላቻ መዝሙር ከማስጠናት ውጪ ምንም ኣልፈየደለትም። የነዚህ ሁለቱ ፈጠሪ የሆነው ሕወሓት ከሚዲያ ሰበካ ውጪ የክልሎቹን እነ ሕዝቦቹን ኣንጡረ ሃብት በመዝረፍ የኣመራሮቹን ኪስ ሲያደርብ ትርፍራፊዉን ደሞ ነገን በሙስና ስም ሊወነጅላቸው ለሚፈልግ የብኣዴን እነ ኦሕዴድ ኣመራሮች ከነካድሬዎቻቸው ያበላል።
የጨዋታው ሜዳ ይሁን የኣጥቂዎቹ ሚዛን ያለው እንግዲህ ሕወሓት እጅ ነው።በተነሱ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ምናልባት የኣንዳንድ ኣመራሮች እና የተወሰኑ ካድሬዎች እጅ ሊኖር ይችላል ይህን ኔትወርክ ደሞ ሕወሓት ትቦውን ብሎ ሊዘጋ ኣያዳግተውም፥ሕወሓት በቅጥረኞቹ ኣማካኝነት መጀመሪያ ከሕዝብ ጎን የተሰለፉ ለማስመሰል የክልል ከፍተኛ ባለስልጣናትን ስም ያስጠፋል ሮሮ በካድሬዎቹ ያስነዛባቸዋል።ይህ የሚጠቅመው ደግሞ ከታች ያሉ ትንንሾቹን እና ተከታዮቻቸውን ለማጥመድ ይረዳዋል፥፥ በተቃውሞ ውስጥ የትልልቆቹ እጅ እንዳለበት በፕሮፓጋንዳ የሚታለሉ የከፍተኛ ባለስልጣናት የክልል ካድርዎች ፊታቸውን ወደ ሕዝቡ ኣዙረው ሲያጨበጭቡ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የተቀሰሩ አጆች ትንንሾቹን ለማጥመድ ጊዜ ኣይፈጅባቸውም፥ ይህ ደግሞ ከኦሮሞ ተቃውሞ ላይ በነሙክታር ከድር ኣባዱላ እና ሌሎች ከፍተኛ የኦሕዴድ ባለስልጣናት ላይ የተቀሰሩ እጆች በብዛት ያጠቁት የበታቹን ኣካላት ነው፥ ኣሁንም ሕወሓት ካድርዎቹን በኣማራ ክልል ባለስልጣናት ላይ የቀሰረው የበታቹቹን ለማጥመድ እንዲያመቸው ሲሆን ኣስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ በግምገማ ስም ከፍተኛ ፓለስልጣናት ላይ የስልጣን ፕወዛ ያደርጋል፤በጉዳዩ ዙሪያ በሙስና ስም የሚታሰሩ ቢኖሩ እንኳን በሕወሓት ተመልምለው በጥቅም ተደልለው እንጂ በሕዝብ ተቃውሞ ላይ ተሳትፈው ኣይደለም።
ወደ ብአዴን መለስ ስንልም ጉዳዩ እንዲሁ ከኦሕዴድ ጋር የተቆራኘ ነው፤ባለፈው የኦሮሞ ፕሮቴስት ሕወሓት በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ለመምታት ብ አዴንን በመያዝ ሌሎችን ኣጋሮቹን እንደተጠቀመ ሁሉ ኣሁንም ኦሕዴድን እና ኣጋሮቹን በመያዝ በኣማራ ክልል የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ለመምታት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፥ ሕወሓት በኢሕ አደግ ውስጥ ያሉን ድርጅቶች ኣንዱን ከኣንዱ በ አይነ ቁራኛ እንዲተያዩ ኣድርጎ በደንብ ስለቀረጻቸው መተማመን እንዳይፈጠር ኣድርጓል ይህም የፖለቲካ ሽኩቻዎች እነ የሕዝብ ተቃውሞዎች በተነሱ ቁጥር ሕወሓት በየወገኑ ከጎኑ ለማሰለፍ እየተጠቀመባቸው ይገኛል።
ኣሁን እንግዲህ ከላይ በኣጭሩ የተቀመጠውን ተከትሎ በኢሕ አዴግ ውስጥ ሕዝብን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ሽኩቻ እውን ኣለ ሕወሓት ብአዴንን ሰጥ ለጥ ያደርገው ይሆን ለኔ የማይመስል ነገር ነው በወያኔ ውስጥ የፖለቲካ ሽኩቻ በቀላሉ ማምከን የሚቻልበት ሕወሓታዊ ኣሰራር ኣለ ይህ ኣሰራር ከፍተኛና መካከለኛ ባለስልጣናትን በጥቅም ከመደለልና ከማስፈራራት ኣንስቶ አንከ ፖለቲካ ጥፊ ይከተላል ይህም ሕወሓት በኢሕ አዴግ ውስጥ በዘረጋው የጥላቻ ድርጅትዊ ኣሰራር ከፍተኛ የፖለቲካ የበላይነት አንዲቀዳጅ ስላደረገው የሚከሰቱ ችግሮች ሁሉ ጊዜያዊ ኣጀንዳ ከመሆን ኣያልፉም፥ ሕወሓት ከኢሕ አዴግ ድርጅቶች ውስጥ የሚፈራው ቢኖር የኣማራውን ሲስተም ብቻ ነው ይህ ሲስተም የደቡብ ኣጋር የተባሉ ድርጅቶችን ሊያሳድፍብኝ ኣሊያን እንዲሸራተቱ ሊያደርግ ይችላል የሚል ፍራቻ ስላለው በኣማራው ክልል የፖለቲካ እነ የኢኮኖሚ እድገት ልንዲኖር ኣይፈልግም፤ኣማራው በደህንነት እነ መከላከያ ተቋም ውስጥ ያለው ሚና ከተራ ጉዳዮች እንዲዘል ፍቃደኛ ኣይሆንም፤ ለምሳሌ ከሌላው ብሄር ኣባላት ይልቅ በወታደሩ ክፍል በእዝ ጣቢያዎች ከኣማራ ክልል የሚሄዱ ወታደሮች መረጃ እንዳያገኙ ራዲዮ እንዳይሰሙ ጫና ሲደረግ ግንባር ላይ በፊት መስመር ለፈንጂ ማምከኛና ለጣላት ጥይው ሲያይ የሚሆኑት እነሱ ናቸው፤ኣማሮች።
ወደ ወቅታዊው ሁነታዎች ስንመለስ የኣማራ ተቃውሞ ተከትሎ የሕወሓት ጡንቻ ያረፈው መጅመሪያ በሚዲያዎች ላይ ነው ልክ እንደ ኦሮሞ ተቃውሞ በጋዜተኞች ላይ እርምጃ እንደተወሰደው ኣሁም የኣማራውን ሚዲያ ማሽመድመድ ነው የኣማራ ጋዜጠኞችን እንዳያስር መዘዙ ሌላ እንደሆነ የደረሰበት ሕወሓት ለማስፈራራትና ዝም ለማሰኘት እንዲረዳው ሚዲያውን መምታት ከዚህ በመቀጠል ወደ ግምገማ ይዞራል የኣማራ ክልል ተቃውሞ እንደ ኦሮሚያ ክልል ተቃውሞ ሁሉ ሕዝባዊ ነው፥ የኣማራው ሕዝብ ከወልቃይት ማንነት ጀምሮ ብዙ ጥያቄዎችን ያነገበ ነው ብ አዴን ይህን የሕዝብ ጥያቄ ተከትሎ ከሕወሓት እንዳያፈነግጥ በጣም ያስፈራል የሚሉ እደምታዎች ኣሉኝ።ሆኖም ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ይቀናጅ ይሆናል ድብልቅ ኣመጽን በሕወሓት ላይ ይፈጥር ይሆናል የሚለው የማይታሰብ ነው።ቀጣዩ የሕወሓት እርምጃ መካከለኛና ዝቅተኛ የብ አዴን ባለስልጣናትን ከነካድሬዎቻቸው መምታት ሲሆን እንደ ኦሕዴድ ባንዴ ሳይሆን በሂደት ይፈጽመዋል፤ በደህንነትና መከላከያ ተቋማት ውስጥ የሚውተረተሩ ኣማሮች ተፈናቅለው ወደ ሲቪል የመንግስት ሰራተኝነት ይዞራሉ፤ከፍተኛ ባለስልጣናትም በሂደት ይፐወዛሉ ኣስፈላጊ ናቸው የተባሉ ደግሞ ግምገማን ተከትሎ በሙስና ይወነጀላሉ የሚወነጀል ካሌለ በገንዘብ የተወሰኑ ካድሬዎች ይገዙናበፊት በር እስር ቤት ገብተው በጀርባ ይወጣሉ። ይህ ነው ያለው ውነት።
No comments:
Post a Comment