Thursday, July 7, 2016

ፀረ-ወያኔ የጋራ ብሔራዊ ትግል ጠንቅ ጠባብ ብሄርተኝነት ብቻ አይደለም

ፀረ-ወያኔ የጋራ ብሔራዊ ትግል ጠንቅ ጠባብ ብሄርተኝነት ብቻ አይደለም

ማሳሰቢያ፤ከዚህ በታች የቀረበው ጽሁፍ የተለያዩ አወዛጋቢና አናጋጋሪ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው ከራሳቸው ዕይታ አኳያ የተመለከቷቸውን ጉዳዮች እያነሱ ግምገማዎችን ያቀርባሉ። በጽሁፉ ውስጥ ስለተጠቀሱት ነጥቦች ትክክለኛነትም ሆነ ስህተት ኃላፊነቱ የጸሃፊው መሆኑንን እያጠቆምን እኛ ነጻ የሕዝብ መገናኛ ብዙሃን እንደመሆናችን መጠን ሃሳባቸው ለአንባቢ አድርሰንላቸዋል።
ከዮናስ ተክለማርያም
ማሳሰቤያ- ለአንባቢያን
-ይህ ጽሑፍ ትውልደ ኢትዮጵያ ስለሆኑ ጠባብ ብሄርተኞችና ጠባብ ብሄርተኝነትን አይዳስስም
-ይህ ጽሑፍ በአገር ቤት በቅርጽም ሆነ በይዘት ከዚህ ጽሑፍ ጋር ተዛማጅነት ያላችውን ይሁንታዎችና ትርምሶችን አይዳስስም
-ይህ ጽሑፍ በዲያስፖራው/በውጩ ዓለም በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ያተኮረ ነው
-ፀሃፊው በሚኖርበት የባዕድ አገር ካየውን ፣ ከተከታተለውን ፣ ከቃኘውን፣ ከተገነዘበውን፣ ካሳሰበውን – ከሌሎች ኢትዮጵያውያንም እይታና አስተያየት ተመርኩዞ ነው የጻፈው
– ይህ ጽሑፍ  ሁልእንትናዊ ግድፈቶች እንዳሉት ፀሃፊው ያውቃል ፤ ፀሃፊው ለይዘት እንጂ ለቅርጽ እምብዛም አይጨነቅም ፣ ጓደኛ ወይም ዘመድ ከተወደደ ከነ-ንፍጡ እንደ ሚባለው – የፀሃፊው ዋና ፍላጎት የዚህ ጽሑፍ መልዕክት ከነግድፉ ለሌሎች ማሳወቅ፣ለሌሎች ማጋራ ትና እንዲገነዘቡት ማድረግ ላይ ነው ።
ወያኔ በጠመንጃ ሃይል የደርግ ቁንጮ መንግሥቱን ፈንቅሎ የአዲስ አበባው የገዢዮቻችን ቤት ከተረከበበት 1983 ዓ.ም አንስቶ – ከፋፍሎ ለመግዛት፣ የኢትዮጵያውያን አገራዊና ሕዝባዊ ስነልቦና ለማኮላሸት/ለመበረዝ ፣ አገራዊና ሕዝባዊ ኅልውናችንን ለማዳከምና ለመበጣጠስ ያላሴረው ሴራና ያልነደፈው ስልት የለም ። ከእነዚህም አንዱ የጠባብ ብሄርተኝ  ነት ወይም የጎሰኝነት ፖለቲካ ፖሊሲው ነው ። ከህብረ-ብሄረሰባዊ ኢትዮጵያዊነት ወይም ከዜጋዊ ኢትዮጵያዊነት ይልቅ የጠባብ ብሄርተኝነት ሰሜትና የጠባብብ ሄርተኝነትፖለቲካ መኮትኮቱና ማጠናከሩ ነው ።
የወያኔ የጠባብ ብሄርተኝነት ፖለቲካ በተመለከተ ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት በበርካታ ኢትዮጵያውያን ስለተጻፈ ለአርእስቴ መግቢያ እንዲሆነኝ ጨለፍኩት እንጂ ይህንኑ ለመውቀ  ውቅጥ ወይም እዚሁ ላይ ለመሞዘዝ አይደለም ። የምፈልገውን መልእክት የማስተላለፍበትን ጽሑፌ የሚያተኩረው  በሌሎች ለብሄራዊ ትግላችን እንቅፋት ወይም  ጎጂ ናቸው በምላቸው ነጥቦች ላይ ነው ። እነዚህም (የተለቪዥን ፣ የሬዲዮ ዜናና የኅትመት ስርጭት ድረገጽ አውታሮች ሚዲያ ኢ-ዲሞክራሲያዊነት) ፣ የተቋሚ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች መከፋፈልና አቅመቢስ መሆን ፣ (ጎሰኝነት ፣ጎጠኝነትና ፣ጭፍን ጥላቻ) ፤ የምዕምናን መከፋፈልና የቤተክርስቲያናት መሰነጣጠቅ ፣የኮምኒቲ ዎችና የእስፖርት ተቋማት መከፋፈልና መዳከም ናቸው ። እነዚህ ነጥቦች እንዴት ‘ፀረ-ወያኔ የጋራ ብሄራዊ ትግል’ እንቅፋት እንድሆኑና እንድሚሆኑ ም እየነጠልኩ ለእኔ የሚታየኝን ለአንባቢ ያን ለማስጨበጥ እሞክራለሁ ።
የሳት ቲቪና ሬዲዮ
ለተራቡ ምግብ፣ ለተጠሙ  ወሃ፣ ለታመሙ ኅክምና ወዘተ..ሲሰጣቸው ምን እንደሚሰማቸው ለማውቅ እነሱ ባለፉበት ማለፍ ወይም እነሱ መሆን ነው። የእሳት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ አገልግሎት በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲጀመር -ለዘመናት ስንመኘውና ስንታገልለት የነበረውን ‘ነጻ ሚዲያ’ እውን ሆነልን አልን፤ ፈነጠዝን ፤ ለኢትዮጵያውያን – አዲስ ውጋጋን፣ አዲስ ጮራና አዲስ ተስፋ ፈነጠቀ እያልን በአካልም በስልክም ተነጋገርንበት ፤ተወያየንበት። ነጻና የማን ም ተጽኖ የሌለበት፤ በፀረ ወያኔ ተሰልፈው  ለዲሞክራሲያዊ አስተዳደር፣ ለፍትህና ለእኩልነት ለሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በእኩልነት የሚያገለግል ሚዲያ ነው ተብሎ ተወራ ። የኢትዮ-ዴያስፖራ ኮምኒቲዎች፣ የሲቪክ ፣ የሃይማኖትና የፖለቲካ ድርጅቶች -በአገራችን ብሄራዊ አጀንዳዎች ላይ በተናጥልም ሆነ በጋራ እንዲወያዩ   መድረክ የሚሰጥና የሚያስተናግድ ሚዲያ እንድሚሆንም ታመነበት ።በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን በሚኖሩበት አካባቢዮች ሁሉ- የሳት ማጠናከሬያ ገንዘብ ማዋጣት ተቀጠለ ፤ እኔም ከአንዴም ሁለቴ የገንዘብ አስተዋጾ አድርጌያለሁ።
እሳት ከተመሰረተበት እ.አ.አ ጁላይ 14/2010 ዓ.ም ጀምሮ -የሳት ተወካዮች በዓመት ሦሥቴ ወይም ሁለቴ እኔ ያለሁበት አውስትራሊያ አሁጉር እየመጡ – በያንዳንዱ ጉዞዋቸው ከ $70-100 ሺ የአውስትራሊያ ዶላር ይዘው ይመለሳሉ ። ኢትዮጵያውያን ተበድረውም ቢሆን ለእሳት ገንዘብ የሚያዋጡበት ምክንያት እሳት ለሃቀኛ  ተቃዋሚ ድርጅቶች ሁሉ በእኩልነት የሚያገለለግል እየመሰላቸው ነው ።
በአንድ በማውቃቸው እቁብተኞች እቁብ ቀንና ቦታ ተገኝቼ ስለእሳት አገልግሎት ስናወራ የሳት ባለቤት ግንቦት 7 ነው ይባላልና – እንዴት ታዩታላችሁ ብዬ ስጠይቃቸው ሁሉም በአንድ አፍ- “አይ የሳት ባለቤት ራሱ እሳት ነው አሉኝ፤ በማስከተልም እሳት ማንም ከማን ሳያዳላ የሚሰራ ነጻ ሚዲያ ነው” አሉኝ ። የቀጥታ የግንቦት 7 አባላት እና የእጅ አዙር የግንቦት 7 አባላት ማለት የሳት አባላትም-እሳት የግንቦት 7 እንዳልሆነ ምለውና ተገዝተው ይከራከራሉ ።
እውነትም እሳት ነጻ ሚዲያ ነውን? እሳት የነጻ ሚዲያ መስፈርትና መተክል አለውን ? እሳት ነጻ ሚዲያ ከሆነ ለምን ሁሉንም የተቃዋሚ- የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች በእኩልነት መድረክ ሰጥቶ አያስተናግድም?  እ.አ.አ ከ 26- 27 ማርች 2016 በእሳትና በግንቦት 7 አጋሮች በተዘጋጀው (Ethio-vision) የኢትዮጵያ ራዕይ በተሰኘው  የውይይት መድረክ – የሸንጎ የፖለቲካ አቋም ይዘው የቀረቡትን የአቶ አክሊሉ ወንዳፍራው ን ንግግር ብቻ ነጥሎ -አደባብይ ወጥቶ ሕዝብ እንዳይሰማ – ው እሳት ለምን አፈነው? ወይስ ጥሪው እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው ዓይነ   ት ነበርን? እሳት የግንቦት 7 ካልሆነ ለምን የሳት ጋዜጠኞች እስከ ኤርትራ በረሃ እየሄዱ የግንቦት7 ናቸው የሚባሉትን ሠራዊት ፎቶ አንስተው የሚያስተዋውቁትና የሚቀሰቅሱት ?ለምድነው  የንጉስ ኢሳያስን ቤተመንግሥት ድረስ ገብተው ኢሳያስ   ን ሲያነጋግሩና ቃለመጠየቅ ሲያደርጉ  የተነሱትን ፎቶዎች በእሳት ተሌቪዥን ለኢትዮጵያውያን የሚያሻሽጡት ? ለምንድ ነው የእሳት ጋዜጠኞች ግንቦት7 በሻቢያ እርዳታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊያመጣ ይችላል ባዮችን ደግመው ደጋግመው ሲያወያዩ የሚታዩት? ከእነህም አንዱ የፋሽቱ መንግሥቱ አጎትና የሥልጣኑ ቀኝ እጅ የነበረት ዶ/ ካሳ ከበደ ነው ። ለምንድ ነው የሳት ጋዜጠኞች በየቦታው የግንቦት7 ሰብሰባዎችና መድረኮች የሚያመቻቹትና የሚዘግቡት? በዚህ አንቀጽ ያሰፈርኳቸው ጥያቄዎች – የግንቦት7 እና የሳት አባላት ውሸታምና አጭበርባሪ መሆናቸውን ለመንገርና የፖለቲካ የዋህ ኢትዮጵያውያንን ለማስገንዘብ እንጂ የፖለቲካ  በሳሎችማ -ገና ከጅምሩ እሳት የግንቦት7 የፕሮፓጋን ዳ መሳሬያ/ማሽን መሆኑን ቢረዱም እንደዚህ ኢ-ዲሞክራሲያዊና መድሎአዊ ይሆናል ብልው አላሰቡም ነበር ፤ ሰለሆነም እርዳታቸውን ለገሱ ።
እ.አ.አ 7 feb 2016 “On media jamming and mass uprising in Ethiopia” “የሚዲያ አፈናና ሕዝባዊ አመጽ” በሚል አርእስት አሜሪካ ውስጥ በተደረገው የውይይት መድረክ ፤ ፕሮ/ጌታቸው በጋሻው የሳት ነጻ ሚዲያነትና አገልግሎት አድንቀው ‘እሳት ባይኖር ኖሮ’ የሚል ግጥም እንደተጻፈም ጠቅሰዋል ። ያ ማለት እሳት ባይኖር ኢትዮጵያው ን ስለአገራቸው ወሬ የሚያሰማ ሚዲያ አይኖርም ነበር ለማለት ይሆን?እሳት ለኢትዮ ጵያውያን ብቸኛ የዜና መሳርያ ነው ለማለት ይሆን? እሳት በመኖሩ የኢትዮጵያ  የፖለቲካ ሁኔታ ተቀይረዋል ለማለት ይሆን? እሳት ለኢትዮጵያውያን ሁሉ -ጆሮ፣ ዓይንና አንደበት ነው ለማለት ይሆን? ወዘተ..
የኢሳት- ቲቪና ሬዲዮ አውንታዊ ሥራዎች
የአንድን ማኅበራዊ/ሕዝባዊ አገልግሎት የሚሰጥ ሞያተኛ -ግለሰብ፣ ቡድን፣ ድርጀት ወዘተ..ሥራ <የሚለካው> ሌሎች ተመሳሳይ አገልግሎት ከሚሰጥ/ጡት ሞያተኛ/ኞች ጋር ነው ። ስለሆነም እሳት-በቅድመ እሳት ከነበሩት- በዓለም ዙሪያ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአማርኛችን የሬዲዮ ዜና ሥርጭት አገልግሎት ይሰጡ ከነበሩትና ከሚሰጡት -ቪኦኤ/VOA ፣ ዶችቬሌ/ DW ፣ (ኤስቪስ/ SBS እና አዲስ ድምጽ/ADDIS DIMS) ሲነጻሰር የሳት አውንታዊ ወይም ከእነዚህ ሚዛን የደፋ  የሚዲ አገልግሎቱ/ሥራው ላይ ነው የማተኩረው ። ይኸውም እሳት ወያኔ የሚፈ–ጽማቸውን-ግፍች፣ በአገር ቤት በየጊዜው የሚነሱትን ፀረ-ወያኔ / ሕዝባዊ አመጾች ፣ በተለያዩ የአገራችን ምድር በረሃብ የተጠቁትን ወገኖቻችን፣ በድርቅ ምክንያት ስለሚሞቱቱ የቤት እንሣት፣ በዓልም ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሚደርጉትን ፀረ-ወያኔ ሰላማዊ ሰልፎች ፣ የኢትዮጵያውያን ሥደተኞች ገጠመኞችን ፣ ከመሬታቸው  ስለተፈናቀሉትን ኢትዮጵያውያን፣ የሳት እርዳታ ማሰባሰቤያ መድረኮች ወዘ..ምስል/ ፎቶግራፍ እያስደገፈ ለኢትዮጵያውያን ይፋ አድርጓል፤ እያደረግም ነው ። የመለስ ዜናዊ ሞት ተከታትሎ ይፋ አድርጎዋል ፣ በወያኔ ሠራዊት መካከል ያለው የሥልጣ ን/የማዕረግ ተዋረድ ጎሳዊና አድሎአዊ መሆኑን በጭብጥ አጋልጧል ፣በኢትዮጵያ እስር ቤቶች በዕሥረኞች ላይ የሚፈጸመውን ሰቆቃ እና አልፎ አልፎ ወያኔ በሰብሰ  ባ የተወያየባቸውን ሚስጥሮች አጋልጧል ። እሳት ከሚያስተናግዳቸው ሎሎች ፕሮ  ግራሞች በትምህርት ሰጪነቱ ፋይዳ ያለው ‘የትምህርት ብልጭታ’ ሲሆን በአዝናኝ ነቱ ‘ዋዛና ቁም ነገር’ ነው – የቀረ ካለ አንባቢ ይሙላበት ።
የሳት-ቲቪና ሬዲዮ አሉታዊ ገጽታዎች
ሁላችንም  እንድምናውቀው  ሚዲያ ኃይል ነው ፤ ሚዲያ የጥፋትም የልማትም መሳርያ ነው ። ስለሆነም ይህ የሳይበር ሚዲያ (እሳት) ቀደምትና አበይት ሥራው መሆን የነበረበት – ለረዥም ዓመታት የትግል ልምድ ያላቸውን ፣የሀገራችንን ተጨባጭ-ፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወዘተ..ሁኔታዎችን ለማስተማር -ልምድ፣ በቃትና ችሎታ ያላቸውን ፣ ሕዝባቸውና አገራችወን ለሚወዱ ፣ ለእውነተ ኛና ለሃቀኛ ተቃዋሚዮችን- ሰፊ መድረክ  ሰጥቶ በአገራችን ብሄራዊ አጀንዳዎች ላይ በተናጥልም ሆነ በጋራ የሚወያዩበት፣ የተራራቁትን የሚቀራረቡበት ፣ የተጣሉ ትን ፣የሚታረቁበት መድረክ መሆን ነበረበት ። የእሳት አስተዳዳሪና የእሳትጋዜጠኞ ች ያንን ሚና መጫወት ነበረባቸው ።
ነገርግን እሳት ትኩረትና ቅድሜያ የሰጠው ከዚህ በተቃራኒ ለተሰለፉትን የፖለቲካ ድርጅቶች ነው ።ይኸውም እሳት ተመስርቶ ሥራ ላይ ከዋለበት ሰዓት አንስቶ፤ ከኢትዮጵያ ጋር በጉርብትና እንጂ አብረን አንኖርም ፣ ኢትዮጵያዊ ሥነል-ቦና የለንም ፣የኢትዮጵያ ሃገራዊ አንድነት አንቀበልም ፣እኛ የኢትዮጵያ ቅኝ ተገዢዎ ች ነን ወዘተ..ባዮችን ከየተደበቁበትን- ጫካ፣ መንድር ፣ ጉራንጉር ወዘተ.. በባትሪ በመፈለግ  ኢትዮጵያዊ ማስክ አልብሶ ወደ አደባባይ በማውጣት ሥራ ላይ ተሰማ ሩ።  ሰፊ መድረክ ሰጥቶ አስተዋወቋቸው ፣ አሻሸጧቸው/ፕሮሞት አደረጋቸው፤ ጎላ ብለው እንዲታዩ ይህ ቀረ የማይባል ጥረት አደረጉላቸው ። የሳምንቱ እንግዳ በተሰውኘው መረሃግብሩ/ፕሮግራሙ  ሲያሳትፋቸው ከሚታዩት አብዛኞቹ የደርግ ና የፋሽስቱ መንግሥቱ ጽረ-ሕዝብ ባለስልጣንና ካድሬ የነበሩ ናቸው ።ለምንይሆን? በ 1983 ዓ.ም በለደን የተደረገውን ዓይነት የሥልጣን ድርድር -በአሜሪካና በአውሮ ፓ ማኅበር (E.U) ግፊት ከተደረገ -ግንቦት 7 እነዚህን ሃይሎች በዙርያው አሰልፎ  ና ሁለተኛ ኢህኣድግ (EPRDF) ፈጥሮ ሥልጣን ላይ ለመውጣት ከማሰብ ይሆን? ወያኔ መጣል የሚቻለው  ከጠባብ ብሄርተኞች ጋር በመሰለፍ ነው ከማለት ይሆን? ለተገንጣይነት የሚታገሉት ላቅ ያለ የፖለቲካ  -ብስለት ፣ ብቃት ፣ስልት ፣እስትራ ተጂ ወዘተ..አላቸው ከማለት ይሆን?
ሌሎች የሬዲዮ ዜና ስርጭት አውታሮችና የኅትመት ሥርጭት ድረገጽዎች በተመለከተ
እነዚህ በባዕዳን አገራት ለሚኖሩት ኢትዮጵያውያን የሚያገለግሉ ሬዲዮኖችና ድረገጽዎች ቁጥር በጣም ብዙ ስለሆኑ – እያንዳንዳቸውን -ተግባር፣ አውንታዊና አሉታዊ አገልግሎት ምን እንድሚመስል ለመመስከር አልሞክርም። ነገርግን ከራሴ ገጠመኝን፣ ካስተዋ ልኩትና ከሌሎ ች ከሰማኋቸውን አስተያየቶች ተመርኩዤ የእነዚህ መዲያ-አድሎአዊ ነት፣ ኢ-ዲሞክራሲያዊነ  ትና ሙስናዊነት – ጠቅለል ጠቅለል ባለመልክ ለማሳየት እሞክራለሁ ። አብዛኞቹ በሚዲያ ሥራ ላይ ያላቸው አስተሳሰብ /ማይንድ ሴት እና አሠራር ተመሳሳይ ነው ። የሚዲያን መተክሎች/ፕሪንስፕልስ ተከትለው የሚሰሩ  ‘ኢትዮጵያን ያማአከልና ያስቀደመ’ የሚዲያ አገልግሎት የሚሰጡ ኢትዮጵያዊ/ት የሚዲያ ሞያተኞች እጅግ በጣም ጥቂቶች ናቸው ። እጅግ በጣም በርካታዎቹ የሚያስቀድሙት የግል ጥቅም ፣ የድርጅት ታዛዥነት ፣ ተክለሰውነ ት፣ ወዳጅነት ወዘተ..ነው (1 ) አንድ የአገርና የኅዝብ ጉዳይ የሚመለከት/መልዕክት ያለው ጽሁፍ ሲላክላቸው ፤ ጽሑፉን -አንድ የገንዘብ ድጎማ የሚያደርግላቸው  ወይም የተወዳጁትን – የፖለ ቲካ ፣ የሲቪክ ፣ የሃይማኖት ወዘተ..ድርጅት ወይም ድርጅት መሪ የሚነካ ከሆነ ጽሑፉ አደባባይ እንዳይወጣ ያፍኑታል  (2) አንድ ጽሁፍ ሲላክላቸው -ጽሑፉን የሚለኩት- በጽሑፉን ይዘትና መልዕክት ሳይሆን በጸሃፊው ነው ። ጽሁፉ -በፕሮፌሰር ፣ በዶክተር ፣ በፖለቲካና በሕዝባዊ መድረክ  በሚታወቅ ፣ አንድ ትንሽ መጽሃፍ ጽፎ በአንድ ድረገጽ በለጠፈ ሰው ወዘተ.. የተጻፈ ከሆነ ወዲያውኑ በድረገጻቸው ይለጥፉታል ። በአገር ጉዳይ ላይ ለቃለ መጠየቅም ለውይይትም  የሚጋብዙዋቸው ከሞላ ጎደል እነዚሁ ናቸው (3) በጓደኝነት ፣ በዝምድና ፣ በትው ውቅ ፣በትውልድ አካባቢነት ፣ በአምቻ ጋብቻ  ወዘተ.. የሚላኩ ጽሑፎችም በደምብ ይስተናገዳሉ ።
የተቋሚ የፖለቲካና የሲቭክ ድርጅቶች መከፋፈልና አቅመቢስ መሆን
ከጥር ወር 2008 መጀመርያ ጀምሮ በዋናነት የኦሮሞ ብሄረስብ ወጣቶች በተከታታይ ያደረጉትን ጠመንጃ አልባ አመጾች የፈጠረው ሁኔታ – የፖለቲካና የሲቪክ ተቃዋሚ ድርጅቶች የተጓዙበትን የተናጥል ትግል ውጤቱ (outcome) ምን እንደሚመስል ደግመው ደጋጋመው እንዲያስቡብትና እንዲመረምሩ ያስገደዳ ቸው ይመሰል ነበር ። ለሃያ አራት ዓመታት ለኅብረት ትግል ጥሪ፣ አቤቱታና ውት  ወታ ጆሮ ዳባ በማለት ፤ ከማን አንሼ-ብቻዬን ታግዬ ለሥልጣን እበቃለሁ ባይነት፣ የፖለቲካ የዋኅነት/ናይቪቲ ፣ ባጭር አቋራጭ  ሥልጣን ለመጨበጥ -ሃቀኛ ታጋዮ ችን አግልሎ ከባንዳዎች ጋር መሰለፍ ወዘተ..ለጥፋት እንጂ ለየትኛውም አገርና ሕዝብ አድን ፖለቲካ ግብ እንደማያደርስ ትምህርት ያገኙበት ይመስል ነበር ። አመጹ ቀድሞ ከተደረጉት አንጻራዊ አመጾች ሁሉ ለየት ያለ ስለነበረ የተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዮች በጣም እንዳስደነገጠ -ለተለያዩ ኢትዮ/ድረገጾች ከጻፉዋቸው ጽሁፎች፣ ለተለያዩ ኢትዮ/ዜና አውታሮች ከሰጡትን የቃለመጠይቅ መልሳችውና አስተያይታቸውን መረዳት ችዬአለሁ ። ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ወድቃለች! ኢትዮት- ጵያ አደጋ ላይ ናት! ኢትዮጵያ በመፍረስና ባለመፍረ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛ-ችለ! ኢትዮጵያ እየፈረስች ነው ! ስለሆነም የህብረት ትግል በአስቸኳይ መጅመር አለበት! ወዘተ.. የተሰኙ መፈክሮች አሰሙ ፤ ደሰኮሩ ።
ያንን-ለኢትዮጵያም ፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ፣ ለወያኔም አደጋ ይዞ መጥቷል የተባለው አመጽ እውን ከሆነ እነሆ መንፈቅ ሆኖዋል ፤ ታዲያ የትአለ ህብረቱ ?  ምነው እነዚያ መፈክሮቹ ሁሉ የውሃ ሽታ ሆነው ቀሩ? ከስሜታዊነት ያለፈ ሥራ መስራት አንችልም ማለት ነውን? ለሃያ አራት ዓመታታ ተቃዋሚዮችን አቅመቢስ- (inadequate) ያደረገው የተናጥል ትግል አሁንም ተቀጠለበት፤ ለምን ?
ለድክመታችንና ለውድቀታችን የታገልነው ያህል – ለምን ለጥካሬያችንና ለአሸና ፊነት አንታገልም ? ማለት ለድክመታችንና ለውድቀታችን መሠረታዊና ዋንኛ ምክን ያት ‘በኅብረት’ ያለመታገል መሆኑን -ኅብረት ኃይል መሆኑን፣ ኅብረት ለኢትዮጵያ ሕዝብም አለኝታ መሆኑን ወዘተ..ከታወቀ -ኅብረት ፈጥሮ ለመታገል ምን አስፈራን?
ለመሆኑ ሁሉም ፀረ ወያኔ ኢትዮጵያዊ  ተቃዋሚዮች የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር የጋራ ችግር ነው የሚሉ ናቸውን? በፀረ ወያኔ የተሰለፉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች መሪዮች ሁሉ- ብሄራዊ ስሜትና ሥነልቦና እኩል ነውን?   በፀረ ወያኔ የተሰለፉ ኢትዮጵያዊ ተቃዋሚ ድርጅቶች ሁሉ- ኢትዮጵያና የኢትዮጵ ሕዝብ ያስቀደም ትግል ይታገላሉን ? ሁሉም የኢትዮጵያ ሃገራዊና ሕዝባዊ ሉዓላዊነት አደጋ ላይ መሆኑን የሚያስጨንቃቸው ናቸውን ? ወዘተ..መልሱ  -አው ከሆነ  ‘ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ’ እንደ ሚባለው -ዛሬ ያልተፈጠረ ኅብረት፣ ዛሬ ያልተገኘ አንድነት፣ ለዛሬ ያልሆነ ኢትዮጵያዊ ሥነ-ልቦና ፣ ለዛሬ ያልሆነ የአገርና የሕዝብ ፍቅር ፣ ለዛሬ ያልሆነ ትምህርትና የፖለቲካ እውቀት ወዘተ..ለመቼ ሊሆኑ ነው ? ለሰማይ ቤት ወይስ ለመቃብር ?
ከላይ ያሰፈርኳቸውን ጥያቄዎች በቅርጽ እንጂ በይዘት የማያሟሉ ተቃዋሚ ድርጅቶች አሉ የምንል ከሆነ ፤ የኅብረት ትግል የማይፈሉጉበት፣ የኅብረት ትግል የሚፈሩበትና የሚያሳቡቡበት ምክንያቶች ምንና ምን ይሆኑ?
– የካፒታል ፣ የሚዲያ ተቋም ፣ የደፈጣ ውጊያ ግንባር ወዘተ አለኝ ፣ አሜሪካና የአውሮፓ ኅብረት ከእኔ ጋር ናቸው ፣ ተቃዋሚ ተብዮች ሁሉ በእኔ ሥር ካልተሠ ለፉ ኅብረት አያስፈልገኝም ፤ ብቻዬን ታግዬና ወያኔን ጥዬ ሥልጣን መጨበጥ የሚያስችል አቅም አለኝ የሚል/ሉ የፖለቲካ ድርጅት/ቶች ስላለ/ሉ ። ስለድርጅቴ  አትወያዩ፣ አትተቹ ፣ አትጻፉ ፣  አስተያየት አትስጡ ፣ በድረገጻቹህ አትለጥፉ ወዘተ .. በማለት የኢትዮጵያውያንን ፖለቲካዊ አንደበትና የሚዲያ ነጻነት ለማፈን የሚቃጡ/ጣ  አምባገነን የፖለቲካ ድርጅችት/ቶች ስላለ/ሉ ።እ.አ.አ  በ2015 አጋማሽ አካባቢ የአዲስ ድምጽ ሬዲዮ ባለቤትና አስተናጋጅ አቶ አበበ በለው የግንቦት 7 ወደ ኤርትራ መሄድን አስመልክቶ በአየር/ሳይበር መድረክ/ፎረም ኢትዮጵያኖችን -ስለአወያየ በከረንት አፌርስ በፓልቶክ ሚዲያ የደረስበትን የስድብና የዘለፋ ውርጅብኝ  ፣ ይህንኑ አስመልክቶ -በኢትዮሚዲያና በቪኦኤ ላይ <VOA>  ላይ ተጽኖ ለማድረግ የተደረጉትን ሙከራዎች የፍላጭ ቆራጫዊ አምባገነንነት (አብሶሊት ዲክታቶሪያል) ባህሪ በቂ ማስረጃዎች ናቸው ።
-በሚፈጠረው ኅብረት ውስጥ ከኔ የተሻለ ችሎታ ያላቸው ስዎች ስላሉ -ሊ/መምበ ርነት፣ ዋና ፀሃፊነቴ ፣ ገ/ያዥነቴ ወዘተ..አጣለሁ/እነጠቃለሁ ከሚል ፍርሃት
-ያንን ድርጅት አልወደውም ፣ እነእገሌ ያሉበት ድርጅት እጠላዋለሁ ፣ ከእነሱ ጋር ኅብረት ከመፍጠር ከወያኔ ጋር ህብረት መፍጠር ይሻላል የሚሉ ስላሉ ። እንደ እነ  ዚህ ያሉትን ድርጅት መሪዮች- ሃቀኛ ኢትዮጵያውያን ያሉበትን የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ድርጅቶች አይወዱም ይሆናል ። ከሃቀኛ የተቋሚ ድርጅት/ቶች ጋር ለመሥራት ምቹ ያልሆኑበት የመደብ ፣ የፀረ ህዝብነት ፣ የመጥፎ ባህሪ ወዘተ.. ጀርባ ይኖራቸው ይሆናል ።
-እውነት ይሁን እውሸት ባይታወቅም -ድርጅቴ ለስበዓዊ መብት የቆመ ድርጅት ስለሆነ ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ኅብረት ከፈጠርኩ- ካለሁበት አገር መንግሥት የሚሰጠኝ ን ድርጎ/ፈንድ አጣለሁ ከሚል ሰበብ ። ሌሎችም በርካታ ውሃ ቀጠነ ፀረ-ኅብረት ምክንያቶችና ሰበቦች ይኖራሉ ። እንደ እነዚህ ዓይነት ተቋዋሚ ተቢዮች ‘ትግል’ -ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ያስቀደመ አይደለም ፤ በኅብረት ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከወያኔ መንጋጋ  ከማላቀቅ- የሚያስቀድሙት እየድርጅታቸውና እየራሳቸውን ጥቅም ፣ ፍላጎትና ሥልጣን ነው ፤ ስለሆነም የኅብረት መሰናክል ናቸው ።
ጎጠኝነት
እገሌ ጎጠኛ ነው ሲባል-ያ ስው ጎሠኛ ነው፣ መንድርተኛ ነው ፣ አድሎአዊ ነው ፣ ኢ-ፍትኃዊ ነው ፣ ዘመድተኛ ነው ፣ ጓደኝተኛ ነው ወዘተ..እንድማለት ይመስለኛ ል ።ጎጠኝነት በተለያዩ ሥውርና ይፋ መንገዶች ይንፀባረቃሉ ወይም ይተገበራሉ ።
1) አንድ ሰው በፖለቲካ ፣ በሃይማኖት ፣ በሞያ ፣ በማኅበራዊ ፣ በመንግሥታዊ ወዘተ..ድርጅት/ቶች የያዘውን የበላይነት ወይም ሁነኛ ሥልጣን ተጠቅሞ  የእኔ ናቸው  ፣ ለሥልጣኔ ይጠቅሙኛል የሚላቸውን -ዘመዶቹ ፣ ጎሳዎቹ ፣ ጓደኞቹ ፣ ከትውልድ ሠፈሩ እስከ ትውልድ ክፍለ ሃገሩ የሚያወቃቸውን በይፋም ሆነ በሥውር ከሾመ ወይም ከቀጠረ ፤ ያ ሰው ጎጠኛ ነው ።
2) ልማታዊ ጎጠኝነት፦  መንግሥት ማድረግ ያልቻለውን የትውልድ አካባቢ ለማልማት/ለመገንባት የመሰባሰብ ጎጠኝነት ።ይህንን ዓይነት ጎጠኝነት አውንታዊ ጥቅም እንዳለው አሉታዊም ጎን አለው። ይኸውም ኢትዮጵያዊነትን ያማአከል/ያስ  ቀደመ ሥራ እንዳይሠራ ያደርጋል ፤ በኢትዮጵያዊነት አጀንዳ ላይ እንዳይተኮር ያደርጋል/ እንቅ ፋትይፈጥራል (የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ኅልውና ለመታደ ግ ወይም ለማዳን ከምናደርግው የጋራ ትግል አኳያ ማለቴ ነው) ። ሁሉም ለጎጡ ብቻ እንዲያስብ ፣ ሁሉም ወደ ጎጡ እንዲሄድ ይጋብዛል ። የብሄርተኝነት ጽንሰ ሃሳብ ፣ የብሄርተኝነት ይዘትና ትርጉም /ኮንቴክስት ባይኖረውም – በቅርጽ የብሄር ተኝነት አካሄድ ይጋራል ። በተለይም የአሁኖቹ ገዢዮቻችን ለከፋፍለህ ግዛ ሥራዓ ታቸውን ሊጠቀሙበት ይችላሉ ፤ ለምን ሌሎችን ጠባብ ብሄርተኛ ትላላችሁ  እናንተም  ጎሳዊ ሳይሆን ጎጣአዊ ጠባቦች ናቹሁ ሊሉ ይችላሉ ።
3) ማኅበራዊ ጎጠኝነት፦ በአንድ መንድር/ሠፈር ተወልዶ – ከህጻንነት ዕድሜ አንስቶ አብሮ (በልተው ጠጥተው ፣ተጫውተው ፣ ጨፍረው ፣ ት/ቤት ሄደው ወዘተ..በማደግ) ፣ ቤተሰብ ከቤተሰብ በመተዋወቅ ምክንያቶች ተገናኝቶ አብሮ (መብላት፣ መጠትና መጫወት) ጤናማና ሶሺዮሎጂአዊ ይሁንታ ነው ። ነገር ግን አብሮ በማድግና ቀድሞ በመተዋወቅ ብቻ ሳይሆን – በአንድ  አካባቢ፣ ወረዳ ፣ አውራጃ ፣ ክፍለ ሃገር ወዘተ.. ወተወላጅነት  ብቻ -ጎ.ሜ ፣ወ.ዬ  ፣ ወ..ቴ ወዘተ.. በሚል ሰያሜ በይፋም ሆነ በሥው ር ተሰባሰቦ -የመብላት ፣ የመጠጣት፣ የመጨ ፈር ወዘተ ፣ ለአከባቢ ልማትም ሆነ ለአገራዊ ፖለቲካ ምንም አስተዋጾ  የማያደር ግ/ጉ ጎጠኝነት ። ድግሳችንም ፣ ግብዣችንም ፣ ሠርጋችንም ፣ ጋብቻችንም  ወዘተ.. እኛው በእኛው  የሚል ዝንባሌ የሚታይባቸው -የሌላ አካባቢ ተወላጅ ኢትዮጵያ ውያንን አግላይ ማኅበራዊ ጎጠኝነት-ፋሽን እየሆነ የመጣ ይመስላል ። እንደውም የአንዱ ክ/ሃገር አማራ የሌላውን ክ/ሃገረ አማራ የሚጠላበትና የሚቋሽሽበት ጎጠኝነ ት እየተደመጠና እየተስተወለ ነው ።
የምእምናን መከፋፈልና የቤተክርስቲያናት መሰነጣጠቅ
በክርስትና ሃይማኖት እምነት መሰረት- ቤተክርስቲያን የክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች በስብስብም ሆነ በተናጥል የእግዛብሄር ቃል የሚሰሙበትና የሚጸልዩበ ት የክርስቲያኖችም የእግዚአብሄርም ቤት ነው ። ነገር ግን በአገር ቤትም ሆነ በባ ዕዳን አገሮች የሚገኙት የዘመነ ወያኔ ኢትዮጵያዊ የዕምነት ድርጅቶች በቅርጽ ሃማኖታዊ ይምሰሉ እንጂ በይዘት ፖለቲካዊ ናቸው  ። ስለሆነም -ሃይማኖታዊ ጎሰኝነት ፣ሃይማኖታዊ ጎጠኝነትና ጭፍን ጥላቻ በባዕዳን አገሮች በፀረ-ወያኔ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያናትም ሆነ በእንድገና መወለድ/ቦርን አጌን ቤተክርስቲያና ት -የምእምናን መከፋፈልና የቤተክርስቲያናት መስነጣጠቅ አበይት ምክንያቶች ናቸው ። እንዴት?
<ሃይማኖታዊ ጎሰኝነት> ፡- ለምን ለወያኔ ሰነዶስ አቡን አይፀለይለትም ፣ ስሙ ለምን አይነሳም ያ ካልሆነ ይህ ቤተክርስቲያን አንፈልገውም ብሎ ጥሎ መሄድ ወይም ተገንጥሎ ሌላ ቤተክርስቲያን መመሥረት ።
<ሃይማኖታዊ ጎጠኝነት> ፦ መሠረቱ- ወሎዬ ፣ጎጃሜ ወዘተ.. የሆነ አንድ ቄስ ወይም መነኩሴ በጥፋቱ ከተወቀስ ወይም ከተባረረ ፤ ጥፋቱ ምንድነው ? እንዴት እንፍታው ? ብሎ መጠየቅ ሲገባ ፤ ሁሉም ባይሆኑም በርካታዎቹ የዚያ ክ/ሃገር ተውላጆች ያንን ቤተክርስቲያን ይጠላሉ ፤ከዚያ ይርቃሉ ። የአንድ ቤተክርስቲያን ቄስና ዳቁን የአንድ አካባቢ ሰዎች ከሆኑ -እንበል ጎንደሬ ከሆኑ ፤ አይ ! ጎንደሬዎች የተጠራቀሙበት ቤ/ክርስቲያን ስለሆነ አንሄድም ብሎ መቅረት።
<ጭፍን ጥላቻ> ፦ የአንድ ቤተክርስቲያን የሰበካ ጉባኤ ሊ/መምበር ፣ ጸሃፊ ፣ ገ/ያ ዥ ወዘተ.. ሰው አያከበርም ፣ ገላመጠኝ ፣ ይዋሻል ወዘተ.. ብሎ በመቀስቀስ  ቡድን አዘጋጅቶ ከዚያ ቤተክርቲያን መራቅ ። በአወስትራሊያ ፣ በኢክቶርያ እስተት ፣ በልሜርቦርን ከተማ  በጎሰኝነት፣ በጎጠኝነትና በጭፍን ጥላቻ ምክንያቶች- አንዲት  ፀረ-ወያኔ የኦርቶዶክስ ቤተክ ርስቲያን -እንድ ድመት ወይም እንድ ውሻ ሦስት ግልገል ቤተክርስቲያት ወለድች፤ ከራሷ ጋር አራት አካል ሆነች ። እነዚህ ችግሮች ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ሌሎች ባዕዳን አገሮች ሁሉ እንዳሉም እገምታለሁም ።
አምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክም ለአምሳዎች ግን ጌጥ ነው እንደሚባለው ፤ አንድ ቤተክርስቲያን አይበቃንም ፣ በተለያዩ መላእክት ስም -በዚህና በዚያ ሰፈር ተጨ ማሪ ቤተክር ስቲያን ያስፈልገናል ተባብሎ ፣ ተመካክሮና ተፈቃቅዶ ቢሆን ኖሮ – ባህላችንና ልማዳችን የሚፈቅዱልንና የሚያስከብረን ሥራ ነበር ። በአገር ቤትም ሆነ በባዕዳን አገሮች የሚኖሩትን  ኢትዮጵያውያን አብሮ እንዳይኖሩ – ወያኔ በቀየሰው  -የጎሰኝነት ሰሜት ምክንያት መከፋፈልና መራራቅ የለመድነው  ቢሆንም ‘የጎጠኝነትና የጭፍ ን ጥላቻን’ ሥራ ሲተገብሩ የሚታዩት ፤ ወያኔ በዋና ጠላትነት ፈርጆ -ከሚገላቸው ፣ ከሚያስራቸው ፣ ከቄያቸው ከሚያፈናቅላችው ፣ ከሚያሳድ  ዳቸው ወዘተ.. ከአማራው ብሄርስብ ናቸው ። የአናሳ ብሄረሰቦች አባላት የዚህ ዓይነት ጽንፈኛ ሥራ ሲሰሩ አይታይም  ።
ኮምኒቲዎችና የኮምኒቲ እስፖርት ተቋማት መከፋፈልና መዳከም
-ከእናት አገራችን በብዙ ማይልስ እርቀን በምንገኝባቸው ባዕዳን አገሮች ወፍዘራሽና ባይተዋር እንዳንሆን
-ደስታችንም ሆነ ሃዘናችን ባህላችን በተከተለ በጋራ ተሳትፎ ለማስተናገድ
-የማንነት ቀወስ እንዳይደርስብን-ባህላችን ፣ ታሪካችን ፣ ቋንቋችን ፣ ወጋችን ወዘተ ተንከባክበን ለማቆየትና ለልጆቻን ለማስተላለፍ
-ከምንኖርባቸው ባዕዳን አገሮች ሕዝብ ባህልና ሥርዓት ተመሳስለን እንዳንኖር የሚገጥሙንን ችግሮች በጋራ ለመፍታት
– ብሄራዊ በዓሎቻችንና አውደ ዓመቶቻችን በጋራ ለማክበር
-ለአካል እንቅስቃሴ ብቻ ሳይሆን በሁሉም  የእድሜ ደረጃ ያሉትን ኢትዮጵያውያን  – እንዲገናኙ ፣ እንዲተዋወቁ ፣እንዲወያዩና በጋራ እንዲዝናኑ     ወዘተ..በማሰብና በማቀድ  -በቅድመ ወያኔ በአንድ ኢትዮጵያዊነት ጥላ ሥር የተቆረ  ቆሩትን /የተመሰረቱትን ማኅበሮች (ኮሚኒቲዮች) እና በኮምኒቲ ሥር የተዋቀሩትን የእስፖርት ተቋማት- ወያኔ የሥልጣን ኮርቻ ላይ ከወጣ ጅምሮ – ‘በጎሰኝነት ፣ በቡድንተኝነትና  በጭን ጥላቻ’ ምክንያቶች ሲከፋፈሉና ሲዳከሙ ይታያሉ ።
አንድ ኢትዮጵያዊነትን ያማአከለ/ያስቀደመ ኮሚኒቲና የዚያ ማኅበረሰብ ማኅበረ የጋራ አንጡራ የእስፖርት ተቋም ቅርስ (the common or the collective good) ነጥቆ ወደ ቡድን ንብረትነት በማዛወር – የቡድን መጠቀሜያ ለማድረግ  የሚጥሩ ፣ ሃቀኛና ኢትዮጵያዊነትን እምብርት ያደረጉ ኮምኒቲዮችን የሚከፋፍሉና የሚያዳክ      ሙ ፣ ‘በጭፍን ጥላቻም ሆነ በጠላት ተልዕኮ’ – ሃቀኛ የኮምኒቲ መሪዮችን በመጥላ ት፣ በማስጠላትና በመከፋፍል ሥራ ላይ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን – በእኔ አካባብ   ቢ እንዳሉ ሁሉ በተለያዩ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው ባዕዳን አገሮችም እንደሚንሩ እገምታለሁሉ ።
ማጠቃለያ
የኢትዮ -ዴስፖራ የሚዲያ ምያተኞች፦ (1) የሞያ ነጻነት ባለበት ፣ በሞያቸው ምክንያት መታሰር ፣ መገረፍና መገደል በሌለበት ፣ የአካልና የአእምሮ ጉዳት ይደርስብኛል በማይባልበት (2) በሞያቸውም ባይሆን በማንኛወም የሥራ መስክ ሠርተው ራሳቸውና ቤተሰባቸውን ማስተዳደር በሚችሉበት አገሮች እየኖሩ ፤
  • ኢትዮጵያ አገሬ ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ህዝቤ በለው የሚታገሉትን ሃቀኛና እውነተኛ የፖለቲካና የሲቭክ ድርጅቶች አግልልው – የኢትዮጵያ አገራዊ ና ሕዝባዊ ሉዓላዊነትን ፣ የኢትዮጵዊነት- ታሪክ ፣ ቋንቋ ፣ ባህል ፣ሥነል ቦና ወዘተ.. የማይቀበ ሉትን ወይም የእኔ ናቸው የማይሉትን  የፖለቲካ ድርጅቶች- ማደራጀት ፣ ማስተገድና ማስተዋወቅ/ፕሮሞት ማድረግ የመረጡና የሚመርጡ የሚዲያ ተቋማትና ጋዜጠኞች እንዳሉ በዚህ ጽሁፍ ከላይ ጦቁሜያለሁ ። ከዚህ ዓይነት የሚዲያ ድርጅት/ተቋም  የሚሠሩ ጋዜጠኞች  – ለገንዘብ ፣ ለጥቅማ ጥቅም ፣ ለሽሞት  ወዘተ.. ብዬ ሞያዬን የሚያጎድፍ ፣ የአገሬና የሕዝቤን ኅልውና የሚጻረር ፣በታሪክ የምወቀስበት ወዘተ..ሥራ አልሰራም ለማለት ለምን አልደፈሩም ? እስካሁን ያጠፉትን ጥፋት ባለመገንዘብና ባለመንቃት ከሆነም ከአሁን ጀምሮ ራሳቸውን ከዚህ ዓይነት የሚዲያ ተቋም ማግለል ይጠበቅባቸዋል (የሳት ጋዜጠኞችን ይመለከታል) ።
(2) በቅንነት ፣ በዲሞክራሲያዊ መተክል ፣ ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ  ጉዳዮችን ያማአከለና ያስቀደመ የጋዜጠኝነት ሞያ አገልግሎት ከመሥጠት ይልቅ የአንድ  የፖለቲካ ድርጅት ፣ የአንድ  የሲቪክ ድርጅት ፣ የዶክተር ፣የፕሮፌሰር  ፣ የደራሲ ፣ የወዳጅ ፣ የአካባቢ ልጅ ፣ የአምቻ ጋብቻ  ወዘተ.. የፖለቲካ ፍላጎ  ትች ማስተናገድና ማሻሻጥ – ለምን ይመርጣሉ ? ለምን ቅድሜያ ይሰጣሉ ?
ከግል ጥቅም ፣ ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት ፣ከዶክተር ፣ ከፕሮፌስር  ከወዳጅ  ወዘተ.. ጥቅምና ፍላጎት – አገርና ሕዝብ አይቀድሙምን ? ለእነዚህ ተገዢ መሆን አጎብዳጅና አድርባይ መሆን አይደለምን ? የጋዜጠኝነት ሞያ ንቃተኅሊ የሚፈታተን አይሆንምን? ለተያያዝነው  ብሄራዊ ትግል አሉታዊ አስተዋጾ  አይኖረውምን ? ( በዲያስፖራ ለሚኖሩ የኢትዮጵዮ -ሚዲያ ሞያተኞችን ሁሉ ይመለከታል)
አምባ-ገነንነት ፦ በባዕዳን አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያ የሚዲያ ሞያተኞችን -የመናገር ፣የመጻፍ ፣ ኢትዮጵያውያንን የማወያየት ፣በድረገጻቸው  አንድን ድረጅት የሚተች ጽሁፍ የመለጠፍ ወዘተ.. ነጻነት ለማፈን የሚሞክሩ እንደ <ግንቦት 7> ዓይነት አምባገነን የፖለቲካ ድርጅቶች – በአገር ቤትሥልጣን ቢዙ (1) ተቃዋሚዮቻቸውን እንዴት እንደሚመቱ (2) ሕዝቡን እንዴት እንደሚያስተዳድሩት ከወዲሁ መገመት ይቻላል ።
ማኅበራዊ ጎጠኝነት ፦ በአንድ አካባቢ ተወላጅነት ተሰባስቦ -መብላት ፣ መጠጣት  መጨፈር ወዘተ..እንድ ሃይል ተደርጎ ይወሰዳል ፤ምቾትና ደስታ የሚያጎናጽፍ ይመ ስላል ፤ ከአብሮነት ልዩነት ይመርጣል ፣ ማለት እነሱ ከተወለዱበት-(አካባቢ ፣ወረ ዳ ፣ አውራጃ ፣ ክ/ሃገር) ያልሆነ/ነች አይፈለጉም ።ይህ ዶምስቲክ ወይም የውስጥ ዜኔፎቢያ  እንድ ማለት ነው ። “pond is the only world for frogs” “እንቁራ ቶች ከሚኖሩበት ጨፌ ሌላ ዓለም የላቸውም” እንድሚባ ለው -አስተሳሰባቸው  ከወፍ ጎጆ የጠበበ ፣ንቃተ-ኅሊናቸው እንቡጥ የሆነ ማኅበራ ዊ ጎጠኞች እያቆጠቆ ነው ።
ሃይማኖታዊ ጎጠኝነት ፦ ክእኔ አካባቢ የመጣ ቄስ ወይም ዳቁን በጥፋቱ ከተወቀስ ፣ ከተቀጣ ፣ከተባረረ ወዘተ..ቤተክርስቲያኑን ጥዬ እሄዳሉሁ የሚሉ ፣ እኔ ከተወለ ድኩበት አካባቢ ባልመጡ ቄሶችና ዳቁኖች አልገለገልም  ፤ ሁሉም የቤተክርስቲያኑ ምዕም ናን በራሳቸው አካባቢ ቄስ ወይም ዳቁን መገልገል አለባቸው የሚሉ፤ ለምሳ ሌ የአንድ ቤተክርስቲያን ምዕምናን-የጎንደር ፣የወሎ ፣ የጎጃም ፣የሸዋ ፣የጅማ- ተወ ላጆች ከሆኑ በቤተክርስቲያኑ ከአምስቱ ክ/ሃገራት የመጡ ቄሶችና ዳቁኖች መኖር አለባቸው  ዓይነት ግራየተጋባ ወይም አስተሳሰብ ያላቸው ወይም በጠላት ተልዕኮ የተቃኘ ‘ሃይማኖታዊ ጎጠኝነት’ – ከላይ እንደገለጽኩት የምዕምናንና የቤተክርስቲ ያናት አንድነት እያናጋና እያተራመሰ ነው ።
ጭፍን ጥላቻና የጠላት ሉዕኳን ፦ በጭፍን ጥላቻና በጠላት ሉዕኳን የሚሴርባ ቸው እነማናቸው ? ለምን ? የጭፍን ጥላቻና የጠላት ሉዕኳን ሰለባዎች – ሃቀኛ የኮሚኒ ቲ ፣ የቤተክርስቲያን ፣ የፖለቲካና የሲቪክ ድርጅቶች መሪዮችና አባሎች ናቸው ። ለምን? ለ(አገራቸው ፣ታሪካቸው ፣ ባህላቸው ፣ ቋንቋቸው አንድነታቸው ፣ ማንነታቸው  ፣ ጥንታዊ  ሃይማኖታቸው ፣ ኢትዮጵዊነታቸው  ፣ ኢትዮጵያዊነት ሥነ-ልቦና ፣ኮሚኒቲያቸው  ወዘተ..) ስለሚታገሉ ፣የእነዚህን ሕልውና ስለሚንከባከቡ ፣ ለእነዚህ ሉዓላዊነት ስለሚከላከሉና ስለሚፋለሙ ።
ይህንን ጽሁፍ በመጻፍ ላይ እያለሁ -አንድ ለረዥም ዓመታት የማውቀው ኢትዮጵያዊ የተወሰኑ የአሜሪካ ግዛቶች ወይም እስቴትስ ጎብኝቶ ሲመለስ -<ወያኔ ሃያ አምስት ዓመታት ስለገዛን ለምን እንቆጫለን  -የወያኔ ወኪል ሆነን የምናገለግ እንመስላልን> አለኝ ። እኔም በአውንታ እንዴት እይታችን ተገጣጠመ አልኩት !
በዚህ ጽሁፍ ንኡስ አርስቶች ሥር የጻፍኳቸው  ድርጊቶች/ ይሁንታዎች ሁሉ ምክንያቶች ምንና ምን ይሆኑ ? የወያኔ እጅ ? ድንቁርና ? የንቃተ-ኅሊና ዝቅተ ኝነት ? የግልና የቡድን ፍላጎት ከአገርና ከሕዝብ ፍላጎት ማስቀደም ? እንድ እኔ እይታ ከላይ በዚህ ጽሁፍ ከገለጽኳቸው  ድርጊቶች ሁሉ በስተጅርባ  – ወያኔ ፣ድንቁ ርና ፣ የንቃተኅሊና-ዝቅተኝነት ፣ የግልና የቡድን ፍላጎቶች አሉበት ።
ይኸውም  በወያኔ ጥቅማ ጥቅም በመታለል ፣በድንቁርና ተጽኖ፣ ከንቃተ-ኅሊና ማነስ እንዲሁም ከአገርና ከሕዝብ ፍላጎት የግልና የቡድን ፍላጎት በማስቀደም   የሚከወኑ ተግባሮች ናቸው እላለሁ ፣ የእነዚህ ውጤቶች ናቸው ፣ ሌላ ሊሆን አይችልም ። በመሆኑም – በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ራሳችንን በማጥፋት ላይ እየዘመት ነው ፤ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወያኔ ዕድሜ የሚያራዝም ሥራ እየሠራን ነው ። ስለሆነም ለሕዝባዊ አንድነታችን ፣ ለአገራዊ ሉዓላዊነታችን እና ዲሞክራሲያዊ የአስተዳደር ሥራዓት ለማምጣት ለምናደርገው  ‘ፀረ -ወያኔ የጋራ ብሄራዊ ትግል’ ጠንቅ ጠባብ ብሄርተኝነት ብቻ አይደለም ። በዚህ ጽሁፍ በንኡስ  አርእስት ያሰፈርኳቸው ዘርፈ ብዙ ችግሮች – ለተያያዝነው  ፀረ-ወያኔ ብሄራዊ ትግል ጎታች ፣ እንቅፋትና ሳንካ ናቸው  የሚል እምነት አለኝ ። ለመፍትሄው በጣም ሊታሰብበት ይገባል እላለሁ ። ከመፍትሄዎቹ አንዱ -የሰከነና ጥራት ያለው (ኦርጋኒክ) ውይይት ማድረግና ማንቃት ይሆናል ።
ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተነሱብንን የኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላቶች በሃቀኛ የኢትዮጵያ ልጆች የተባበረ ክንድ ይወድማሉ ! በቅርጽ ለኢትዮጵያዊነት የቆሙ የሚመስሉ ፤ በይዘት ግን በፀረ-ኢትዮጵያዊነት የተሰለፉ ሃይሎች ይጋለጣሉ !
ይህ ጽሑፍ አደባባይ እንዲወጣ በድረገጻችሁ የምትለጥፉልኝ የሚዲ ሞያተኞች ፤የኢትዮጵያ አድባር ይጠብቃችሁ ፤ ተፈጥሮ ይመርቃችሁ -ማለት ዕድሜያችሁ ይርዘም  ።

No comments:

Post a Comment