Monday, July 18, 2016

የዐማራን ሕዝብ ትግል ለመገንዘብ የሚከተሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎች መገንዘብ ያስፈልጋል፤


የዐማራን ሕዝብ ትግል ለመገንዘብ የሚከተሉትን ወቅታዊ ሁኔታዎች መገንዘብ ያስፈልጋል፤
1. በዐማራ ክልል እና በፌደራል መንግሥት (የትግራ መንግሥት) መካከል ግልጽ ልዩነቶች ታይተዋል፡፡ ጨዋታው የሚዲያ ሆኗል፡፡ ለምሳሌ አቶ ንጉሡ ጥላሁን (የዐማራ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ) እና የትግራዩ የጸረ ሽብር ግብረ ኃይል መግለጫ ፍጹም ተቃራኒ ናቸው፡፡
አቶ ንጉሡ ይህ ሁሉ ሕዝብ ችግር ከሌለበት በስተቀር አሸባሪ ሆኖ አይወጣም ሲል በግልጽ ተናግሯል፤ እንዲሁም ይህ ሕዝባዊ ተቃውሞ እንጅ የብሔር ግጭትም አይደለም ሲል እንክት አድርጎ ገልጧል፡፡ የፌደራል መንግሥት ሁለት በፍትሕ መታየት ያለባቸውን ጉዳዮች አስቀድሞ ፈርዷል፡፡ አንደኛው በስልክ በተቀነባበረ ድራማ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ወልቃይት የትግሬ ነው ሲል በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች አስነግሯል፡፡ በትግራይ ሕዝብ ላይ የተቃጣ መአት እንደሆነ እየለፈለፈ ነው፡፡
2. ኮሎኔል ደመቀን ብአዴኖች ለመስጠት እንደተስማሙ ዛሬ የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፤ ኮሎኔል ደመቀንና ሌሎች በትግል የታሠሩ ዐማሮችን ወሕኒ አውርዶ እንደተለመደው በቶርቸር ብዛት ቃላቸውን እንዲሰጡ አገዛዙ እቅድ እንዳለው ግልጽ ነው፡፡
መላው የዐማራ ሕዝብ ደግሞ እንኴን ኮሎኔል ደመቀን ሊሰጥ ቀርቶ የታሰሩትን ካላስፈታ አይመለስም፡፡ ትናንት በየዳ ላይ የአገዛዙን ገመድ በጥሰዋል፤ የሥርዓቱ መገልገያዎች ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ወድመዋል፡፡ ይህ በደባርቅ፣ በበየዳና በጎንደር ብቻ ተወስኖ የሚቀር አይደለም፡፡ ገና ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን መላ አፍሪካን የሚያርድ ተጋድሎ ዐማራው ይጀምራል፤ ይህ ትንቢት ሳይሆን አሁን እጀመረ ያለ ነው፡፡
እነዚህን ነባራዊ እሙኖች ተንተርሰን የዐማራው ሕዝብ ትግል ወደ የት ነው የሚሔደው የሚለውን እናያለን፡፡ ወያኔ በጣም ብዙ ወጣቶችን ለማሰር እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ እናውቃለን፤ መታሰር ለዐማራ ልጅ አዲስ አይደለም፡፡ የዐማራ ሕዝብ እኮ ለሃያ አምስት ዓመታት በጅምላ ታስሯል፤ ተገድሏል፤ ምስጋና ለእኛ ሲሉ ለተሰቃዩ ታጋዮች! እነርሱ ታግለው እኛ አንገታችን ቀና እንድናደርግ አስችለውናል፡፡
አሁን መላው የዐማራ ሕዝብ የትግል ማዕከሉን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱንና የወልቃይት ጠገዴን ጉዳይ አድርጎ ይዟል፡፡ የጎንደር ከተማ ከንቲቫና የዐማራ ፖሊስ ኮሎኔሉን አንሰጥም፤ ከፈለጋችሁ ወደ ሕዝቡ ይቀላቀልና እናንተ ያዙት የሚል አቋም ይዞ መሰንበቱ የሚታወቅ ነው፡፡ ሆኖም ዛሬ ላይ ባሉት መረጃዎች መሠረት በጫና ብዛት አሳልፈው እንዲሰጡት ተስማምተዋል፡፡ ዛሬ፣ ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ሊፈጽሙት ይሞክራሉ፡፡
ያ ቀን ነው ጉዱ! በዚያ ቀን በመላው የዐማራ ሕዝብ የሚፈጠረውን ስሜት መገመት አይከብድም፡፡ ወያኔዎች የሚያስከፍላቸውን ዋጋ አላወቁም፡፡ ልክ ከመቀሌ ሰተት ብለው መጥተው እንወስደዋለን ብለው እንዳሰቡት ሁሉ አሁንም መካሪ አጥተዋል፡፡ የዐማራ ሕዝብ በማንነቱ ለሚመጣበት ባእድ አካል ምንኛ መሬ እንደሆነ አላወቁትም፡፡ በዚያ ዕለት ጀግኖች ወንድሞቻችን የሚያሳዩትን ተጋድሎ ለወያኔ ሥርዓት አጠቃላይ ውድቀት ነው፡፡ ይህ ትንቢት አይደለም፤ ለማየትም ረጅም ጊዜ አያስፈልግም፡፡ ቀናት ብቻ ይቀራሉ፡፡
ያኔ ታዲያ ምን ይሆናል? ያኔ የተከዜና አንገረብ ወንዞች በደም ሲቀሉ ይታየኛል፡፡ የሥርዓቱ አገልጋዮች የትኛውንም ያክል ቢታጠቁ፣ የትኛውንም ያክል ቢደበቁ የትም አያመልጡም፡፡ ያኔ መሬት ጠባብ ነች፡፡ መሬት በዋጠችኝ የሚሉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
በሌላ በኩል ሥርዓቱ ይህ እንዳይሆን ሁሉ በእጁ ነው፡፡ ሁልጊዜ ከሽንፈት መማር ባሕሪው ስለሆነ ነው እንጅ ኮሎኔል ደመቀን ጨምሮ የታሠሩ ዐማሮችን ሙሉ በሙሉ ከእስር ለቆ የወልቃይትን ጥያቄ በሰለማዊ መንገድ በሕጉ መሠረት እንዲሔድ ማድረግ ይችላል፡፡ እስካሁን የሞቱት ሰዎች ይበቃሉ፡፡ ስለዚህ ምርጫው ሁለት ነው፤ እሳት ወይም ውኃ፡፡ ለብ ያለ ነገር ብሎ የለም፡፡
በትግራይ መከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ ውስጥ ያሉ የዐማራ ልጆች በወገኖቻቸው ላይ ዐይናቸው እያየ አይተኩሱም፡፡ እርግጥ ነው የሌላ ጎሳ አባለትን ብቻ ሊያሰልፉ እንደሚችሉ ይጠበቃል፡፡ ግን ደግሞ የዐማራ ልዩ ኃይልና ሲቪል ፖሊስ ዝም ብለው አይመለከቱም፡፡ ምክንያቱም እነርሱም እንደኔ ዐማራ ናቸውና፡፡
ዐማሮች ከየጀ ደላንታ እስከ ግሸን አምባ፣ ምንጃር ሸንኮራ እስከ መርሀቤቴ፣ ከደጀን እስከ ይስማላ፣ ከጋይንት እስከ ኹመራ ድረስ ይሰባሰባሉ፡፡ ለትግሬው መንግሥትም የመጫሚያ ቦታ እንኳን አይኖረውም፡፡
ስለዚህ በየትኛውም በኩል በሚደረገው ትግል የዐማራ ሕዝብ አሸናፊ ይሆናል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ለሰላም ቅድሚያ እድል ሰጥቷል፡፡ ቀጥሎ ያለው የትግሬው አገዛዝ ብቻ የሚወስነው ይሆናል፡፡
እንደማስገንዘቢያ፡
የዐማራ ሕዝብ ተጋድሎ የበቀል አይደለም፤ ማንኛውም ሕዝብ ላይ ዐማራ በበቀል አይነሳም፡፡ ነገር ግን ከአገዛዙ ጋር ሕብረት ያደረጉ ወገኖች ጉዳት ቢደርስባቸው በዘራቸው ሳይሆን በሚሠሩት ተንኮል ነው፡፡

No comments:

Post a Comment