ከባለፈው ስህተት ተምረን የሞተውን ወያኔን ቀብሩን እናፋጥን!!
አሚናት ኢብራሂም ከኖርዌ
ህወሃት ወያኔ ኢትዮጵያን ከመቆጣጠሩ በፊትና ስልጣንም ይዞ በቆየበት ዘመን እስከ 1990 ዓ ም ድረስ ከኤርትራ
መንግስት ሻዕቢያ ጋር እጅና ጏንት እንደሆኑ በአንደበታቸው ሳይቀር እየተኩራሩ ሲናገሩ ተደምጠዋል። ግን እነርሱ
እንዳወሩት ሳይሆን በተለያዩ ጊዜያት ወደ ተለያዩ ግጭቶች በመግባት ሰላማዊውን ዜጋ ባልሆነ ተልካሻ ምክንያት
ሲያስጨርሱት ከርመዋል። በኤርትራም ይሁን በኢትዮጵያ በኩል ያሉ ህዝቦች እውነተኛ የሆነውን የግጭት መንስኤ
አያውቁም። በተለመደ መልኩ በሁለቱም በኩል ያሉት አምባገነን መሪዎች ተመሳሳይ የሆኑ ምክንያቶችን በማቅረብ
ህዝብን ሲያደናግሩ ይስተዋላሉ። ወያኔ ካስፈለገው ድንገተኛ ወረራ በሻዕቢያ እንደደረሰበት አድርጎ ያቀርባል። ሻዕቢያም
በተራው ወያኔ ጥቃት ሰንዝራብኛለች በማለት ሲከስና ሲካሰሱ ይደመጣሉ።
እነዚህ ሁለት አምባገነን ገዢዎች በሀገራቸው ውስጥ በዜጎች የሚነሱ ማንኛውንም አይነት ጥያቄዎችን የሚመልሱት
ጠያቂውን ክፍል የሚገደለውን ገለው የሚታሰረውን አስረው በቃ ለነሱ የህዝብ ጥያቄ የሚመለሰው እንደዚህ ነው።
በሁለንተና ባህሪያቸው አንድ ከሚያደርጋቸው ነገር ህዝብን በልተው ሳይጨርሱ መወገድ አለባቸው። ስልጣናቸው
ጣኦት የሆነባቸው እነሱ ከተቀመጡበት ወንበር ላለመነሳት ሲሉ የሁለት ሀገር ህዝቦችን በስደት በርሀብ በጦርነት እርስ
በርስ በማጋጨት ዛሬም ድረስ እየገዙ አሉ።
ወያኔ አሁን በሀገር ውስጥ ያለውን ትግል እንዳስፈራው የሚያሳየው ከየአቅጣጫው የሚወስደው እርምጃ ትግሉን
መጠናከሩን እንጂ ወደሗላ መመለሱን አያሳይም ለዚህም ነው ወያኔ ትግሉ አስፈርቶት በሁሉ ስፍራ አውሬነቱን እያሳየ
ያለው ኢትዮጵያዊውም በዚህ ሰአት በሁሉ አቅጣጫ ትግሉን እያፋፋመው መስዋእት እየከፈለ የወያኔን ግብአተ መሬት
መድረሱን ተረድቶ እየታገለ ይገኛል ።
እንዲያውም ትግሉ ውጤት ማምጣት ስለጀመረ የሚከፈለውም የመስዋእትነት ዋጋ ይበልጥ እየጨመረ ሄዱዋል።
ወያኔም በተጋለጠ ቁጥር ትግሉም በተሻለ ልምድ ባላቸው የትግል ተሞክሮዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ሊጠቅም በሚችል
በሳል አመራሮች ሲመራ ውጤቱ ያማረ ይሆናል። ታዲያ ከእስከዛሬው በተሻለ ኢትዮጵያዊነታችንንና አንድነታችንን
በማጠናከር ለትግሉ በቆራጥነት የተዘጋጀን መሆናችንን ማሳየት ይጠበቅብናል። አንድነታችን ምንም አይነት ድንበር
ሳይገድበው ማሳየት አለብን። ከዚህም በሁዋላ ወያኔ ለሚያደርስብን ችግሮች እንቅፋት ፈጣን ምላሽ እየሰጠን
እንቀጥል እምቢ ለሀገሬ ብለን በድል ጎዳና እንጉዋዝ።
በሀገራችን ኢትዮጵያ እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በጉልበት ለነገሰው ወያኔ ህልውናውን የሚፈታተኑት አስከፊ
ተግባሮችን እንዲያቆም ስልጣኑንም ለቆ ለፍርድ ለማቅረብ ጊዜው መድረሱን የሚያሳዩ ምልክቶች በዝተዋል። ወያኔ
ምርጫ በሚባል ቋንቋ እንደማይወገድ ካወቀ የቆየው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ነው በሁለገብ ትግል ወያኔን አሽቀንጥሮ
ለመጣል የተነሳው። ዘረኞቹ ወያኔዎች ሀገር አውዳሚነታቸው ትውልድ ገዳይነታቸው ሉአላዊነትን አሳልፈው
ሰጪነታቸው ህዝቡ ይሄን ጨካኝ ባህሪያቸውን በምርጫ ካርድ እንደማይቆም ከተገነዘበ አመታት አልፈዋል።
ታዲያ ለነፃነታችን እንዲሁም ለሀገራችን ለህዝባችን ካለፈው ትውልድ ጀምሮ አዎ ብዙዎች ታስረዋል እየታሰሩ ነው
ግፍና መከራን ተቀብለዋል አሁንም እየተቀበሉ ነው ነገም ለነፃነታቸው እንደሚቀበሉ ይታወቃል። ኢትዮጵያዊው ዛሬ
በሀገሩ ላይ ስራ ለመስራት የወያኔ ካድሬ መሆን የግድ እንደሆነ እየተነገረ አለ። ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻ አይጠቅምም
ስራም ከተቀጠሩ በሁዋላ ወሬ ማቀበልና ማነፍነፍ አለበት። ዘረኛው ወያኔ በዘር ፖለቲካ የተለከፈ በመሆኑ በብሄር
ማንነት እንደ አንድ መስፈርት ነው የሚቆጥረው።
ኢትዮጵያዊ ወጣት እንደዚህ በሀገሩ የሚሰደድበት ምክንያት ከምንም በላይ ምክንያቱ ወያኔ ነው። የወያኔ የዘር
ፖለቲካ ወጣቱን አማሮታል። ወያኔ ሰብአዊ ዲሞክራሲያዊ መብቶችን በመግፈፍ ህዝብን ረግጦ እየገዛ በመሆኑ ህዝቡ
በተለይ ወጣቱ ሀገሩን እየጣለ መሰደዱን ተያይዞታል ስደት ግን መፍትሄ ሊሆን አይችልም ስለተሰደድን ወያኔ
የሚያደርስብን ግፍና በደል አይቆምም። ወያኔን አሽቀንጥረን በመጣል መገላገል ነው ያለብን ለይስሙላ ሳይሆን
ከልባችን ተደራጅተን ወያኔን ማስወገድ አለብን።
ወያኔ ከአንድ ጎሳ የተሰበሰቡ ጋዜጠኞች ቀጥሮ በነፃ ጋዜጣ ስም ራሱ በተቆጣጠረው ሚድያ ሀሰትን እውነት እያስባለ
ያስለፈልፋል። ፀረ ወያኔ ሀይሎችን በህዝብ ዘንድ ጥላቻ እንዲኖር ለማድረግ የቁራ ጩኸቱን ይጮሀል። ለብቻው
እንደፈለገ የተቆጣጠረውን ሚዲያ ህዝብን ከፋፍሎ ለማዳከም ይጠቀምበታል። ወያኔ በሱ አስተሳሰብ ሀቅና ታሪክ
ተዳፍኖ የሚጠፋ ይመስለዋል። ታሪካችንን አስረስቶ ውሸትንም ሀቅ አድርጎ ለማቅረብ ሁሌም ይተጋል ሆኖም ግን
ይህንን የወያኔ ሴራ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከተረዳ ቆይቱዋል የማህበረሰባችንን ውስብስብ ችግሮች ከመፍታት ይልቅ
ችግርን ይበልጥ እያወሳሰበ ስልጣኑን ለማራዘም በውሸት ህዝብን ሲያደናብርና ሲያደናግር ግራ ሲያጋባ የነበረው ወያኔ
ዛሬ ላይ ግን ኢትዮጵያውያን በእንደዚህ አይነት ቀላል በሆነ ተረት ተረት ማለፍ የሚቻልበት ጊዜ አይደለም። የሀገራችን
ዜጋ በታሪኩ ከግፍና ከጭቆና ጋር አብሮ የኖረ ነው ታዲያ ይህ ሆኖ ዛሬ መንፈሰ ጠንካራ ነው ጠላቱን ወያኔን ለመጣል
ቆርጥዋል። በኢትዮጵያ ሀገራችን ውስጥ የሚገኙ ፈተናዎችም ከባድና ብዙ ስለሆኑ በሌላ አለም ከሚኖሩ
ኢትዮጵያዊያኖች እገዛ ይፈልጋል።
እናቸንፋለን
No comments:
Post a Comment