Tuesday, July 12, 2016

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሕዝብ እንዲጎበኙ በኣስቸኳይ ሊፈቀድ ይገባል።

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በሕዝብ እንዲጎበኙ በኣስቸኳይ ሊፈቀድ ይገባል። 
ከየመን ኣየር ማረፊያ በሕወሓት የደሕንነት ሓይሎች ታፍነው ኣዲስ ኣበባ በእስር ላይ የሚገኙት የነጻነት ታጋይ አቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌ እስኪፈቱ ድረስ በሕዝብ እንዲጎበኙ በኣስቸኳይ ሊፈቀድ እንዲገባ በውያኔው ኣገዛዝ ላይ ተከታታይ ጫና ሊደረግ ይገባል። ማህበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ በተለያዩ መንገዶች በኩል በኣገዛዙ ላይ ጫና በማድረግ አቶ አንዳርጋቸው በሕዝብ አንዲጎበኙ ሰፊ ስራዎች ሊሰሩ ይገባል።
አቶ ኣንዳርጋቸው ጽጌን የእንግሊዝ ኣምባሳደርን እና የፖለቲካ ኣታሼውን ጨምሮ በተወሰኑ ዲፕሎማቶች እንደሚጎበኙ ከለንደን የሚወጡ ዘገባዎች ይጠቁማሉ።እንዲሁም አቶ ኣንዳርጋቸውን ኣባታቸው ኣቶ ጽጌ እንደጎበኟቸው ይታወቃል።በሕግ ጥላ ስር ናቸው እስከተባለ ድረስ ከሕዝብ ጋር ተገናኝቶ ማውራት ባይችሉም የኣቶ አንዳርጋቸው ኣድናቂዎችና ደጋፊዎች በሩቁ በተከለለ ቦታ ላይ ሆነው እስኪፈቱ ድረስ እንዲጎበኟቸው ሊፈቀድ ይገባል።


ከኣቶ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝታቹሃል ተብለው በተለመደው የሕወሓት የሃሰት ክስ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ክሱ በሃስት የሆነ መሆኑን ኣቶ ኣንዳርጋቸው ቀርበው ሊመሰክሩ ይችላሉ ብለው ለፍርድ ቤት ቢያመለክቱም ከኣመት መንገላታት በኋላ አቶ አንዳርጋቸው ሃምሌ ፯ ቀን ፪፻፰ ዓም ፍርድ ቤት የማይቀርቡ ከሆነ ተከሳሾችን በነጻ እናሰናብታለን ሲል ሰፍርድ ቤት መናገሩን የሰማን ሲሆን እስካሁን ግን የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ኣቶ ኣንዳርጋቸው እኔ ጋር የሉም ቢልም የእንግሊዝ ዲፕሎማቶች እና ቤተሰቦቻቸው ግን ኣቶ አንዳርጋቸው ቃሊቲ መኖራቸውን እና ገብተው መጠየቃቸውን ይናገራሉ። ዓቃቤ ሕግ አቶ አንዳርጋቸው ፍርድ ቤት እንዳይቀርቡ በሰበር ሰሚ ችሎት አሳግዶ ቢቆይም ፣ ሰበር ሰሚ ችሎቱ የአቃቢ ህግን ይግባኝ እንደማይቀበለው በመግልጽ አቶ አንዳርጋቸው ቀርበው እንዲመሰክሩ ኣዟል ሲባል ሰምተናል፤በዚህም መሰረት ኣቶ ኣንዳርጋቸው በግልጽ ይሁን በዝግ ፍርድ ቤት የሕወሓት ኣዲስ ፈጠራ ካልታከለበት ሃምሌ ፯ ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ኣቶ አንዳርጋቸው የሕዝብ ልጅ ከሕዝብ ኣብራክ የወጡ እስከሆኑ ድረስ በሕዝብ ሊጎበኙ ይገባል፥ይህ እንዲሆን ደግሞ የለውጥ ሃይሉ በጋራ ቆሞ ተከታታይ ጫና በመፍጠር ጉዳዩን ሊይስፈጽም ይችላል፤ የማይሆን ነገር የለም ወያኔ ላይ ተከታታይ ጫናው ከበረታ ሕዝባዊ ጉብኝት እንዲፈቅድ ማድረግ ይቻላል። 

1 comment:

  1. minale gelbiteh sitiletif minchun aliyan tsehafiwun bititekis

    ReplyDelete