ጎንደር፡ ዛሬ አንደተጠበቀው የብአዴን ኣና የትግሬ ፌድራሎች ስብሰባችዉን ጨርሰዋል፡፡ መግለጫም ከስብሰባዉ በሁላ የክልሉ መንግስት አዉጥቷል፡፡ መግለጫው ከወያኔ የተለምዶ ጸባይ አንጻር ስታይ በኔ ግምት መጥፎ ነው የሚባል አይደለም፡፡ ኮ\ል ደመቀ ለግዜው በጎንደር አስርቤት ዘመድ አየጠይቀው ኣንዲቆይ የተስማሙ ሲሆን ፍርድ ቤት ቀርቦ ጉዳዩ ያለምንም ጣልቃ ኣንዲታይ ተስማምተዋል፡፡
አራቱ ወያኔ ያገታችው የኮሚቴ አባሎች ኣንድሁ ወደ ጎንደር ማረሚያ ቤት አንዲመጡ ተስማምተዋል፡፡ብአዴን የትግራይ ክልል አባይ ወልዱ የፈጸመዉን ድርጊት ያለማጎብደድ በምሬት ተናግረዋል፡ ሆኖም ግን ለህዝቡ ሰዎችን ለመያዝ የመጣው ሃይል ለአንድነት ሲባል የፈድራል ኣንደሆነ ተደርጎ ኣንድነገር ተስማምተዋል፡፡ ሁለቱ ከትግራይ መጥተው ክፉኛ የቆሰሉት ትግሬዎች ወደ መቀሌ በሄልኮፕተር ሂደዋል፡፡
ጎንደር ከተማ ንብረታችው የተጎዳባችው ትግሬዎች የከንትባ ተቀባን ቢሮ በብዛት በመግባት ንብረታችንን ያወደሙ ሰዎች ተይዘው ካላየን አንወጣም ብለው ኣስከኣሁን ድረስ መስሪያ ቤቱን ከበው ይገኛሉ፡፡ ንብረታችው ተገምግሞ አንደሚከፈላችው ከንቲባው ቃል ቢገቡም አሻፈረን ብለዋል፡፡ ይህ ጉዳይ ሌላ ችግር ኣንዳፈጥር ተስግቷል፡፡ ስልክ በወያኔ ስለሚጠለፍ አብዛኛዉ ህዝብ ልዩ ጥንቃቄ ኣያደረገ ነው፡፡ ብ አዴን ኣስከአሁን ድረስ የዉስጥ መፍረክረክ ባይታይም ካሳ ተክለብርሃን የተባለው አዉሬ የወያኔ ዋነኛ ሰላይ አንደሆነ ይጠረጠራል፡፡
ሌላው ጉዳይ ትጥቅ ለማስፈታት ወያኔ ኣቅድ ይዟል ሁኔታዉ ከተረጋጋ በሁላ ፡፡ ትጥቅ በጎንደር ባህል ከኑሮ አስፈላጊ ነገሮች አንዱ ኣና ዋነኛው ሲሆን ወያኔ በስልጣን ሰክሮ ባህል መሆኑን ረስቶ ለማስፈታት ቢንደፋደፍ ውጤቱ ወደ ባሰ ቀዉስ መግባት ነው፡፡በረከት ስሞእን አሁንም ሳይፈራ ለወያኔ ኣልቆች የሁላችንን ውድቀት አታፋጥኑ ስል ተማጸኗል ብለዋል።
No comments:
Post a Comment