Wednesday, July 13, 2016

ለአባይ ወልዱ ታሪክ ይቀር የማይለው ስህተት ከመስራት እንድትቆጠብ የቀረበ ማስጠንቀቂያ

በትግራይ ክፍለ ሐገር ውስጥ የሚኖረው ህዝብ በሌሎቹ የኢትዮጵያ ክፍለ ሐገሮች ውስጥ እንደሚኖረው ህዝብ የስቃይ ዓመታትን አሳልፏል፡ ከነዚያ የስቃይ ዓመታት በኃላ የሚፈልገው በሰላም መኖር ነው።  አሁን ለትግራይ ህዝብ ጠላቱ ድህነትና ድህነት ብቻ ነው። ምናልባትም እንተና መሰሎቸዎችህ ተጨማሪ ጣላት ሳትሆኑ አትቀሩም። ለትውልድ የሚተርፍ፣ ታሪክን የሚያጎድፍ ፣የቅር የማይባል ስተት እየሰራህ እንደሆነ ሊገባህ ይገባል። እኔ ብዙ የትግራይ ልጆች ጓደኞቼ ናቸው። የእነሱ ወንድሞች የእኔን ወንድሞች እየገደሉ አብርን መጫወት አንችልም።  እኔ ሳለቅስ ፣ እነሱ እየሳቁ  ባህሉ አይፈቅድም።  እንደኔ አያለቅሱም ምን ሙቶባቸው?  የትግራይ ለእጆች  ጎንደርን  እንደ ሁለተኛ የትውልድ መንደር እንጅ እንደ ጠላት ወረዳ መቁጠር ነበረባቸው ወይ?  ለመሆኑ ጎንደርን ከትግራይ የሚነጣጥለው አሁን እናተ በስልጣን ያላቹት ካልሆነ በስተቀር  ባህሉ ነውን? መልክዐ        ምድሩ ነው ? የህዝቡ አሰፋፈር ነው? አባይ አንተ አታውቀው ከሆነ እንጅ እኮ የአኩስም ትልቁ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን የሰራው ፋሲል ጎንደሬው  ነው። በጎንደር ያሉ በርካታ አብያተክርስቲያናት  አቡነ ሀራ ገዳንም ጨምሮ በአጼ ዮሐንስ የተሰሩ ነበሩ ፡፡ በጋብቻ ይሁን በተለያየ ዝምድና ዓይነት ለትግራይ ከጎንደር የቀረበ አልነበረውም።  የአጼ ዮሐንስ ቤተ መንግስት 4 ወር መቀሌ ሲሆን 8 ወር  ጎንደር ደብረ ታቦር ነበር።   አንተ አሁን ያን ታሪክ እንድታስታውስ  ወይም  እንድትሰራ አይደለም የምጠይቅህ የተሰራው ከማፍረስ አቁም ነው የምልህ!!
ታሪክ ነጋሪ ትውልድን በመግደል ታሪክ አትአጥፋ፤  እያልኩ ነው የማስጠነቅቅህ።ጊዜ ተገለባባጭ ነውና ለትግራይ የትውልድ ጠላት አታስቀምጥ።አንተ ሃላፊነህ እድሜም ይገድብሃል። የማያልፍ በደል አትስራ፤ የጥል ግድግዳም አትገንባ።እባክህ እያልኩ በእንባ ጽፌልህአለሁ። ማን ያውቃል የራሄል እንባ ቸል ያላለ፤ የፈርኦንን የግፍ አገዛዝ የተበቀለ፤ አምላከ እስረኤል አንተን አንድ ቀን ይጎበኝህ ይሆናል። ከቲዎድሮስ መንደር እጅና እግር አስረህ ለመውሰድ ሰራዊት ትልካለህ? ጊዜ እንጅ የሰው ትንሽ የለውም። ከጀግና መንድር ቢበዛ ሞት እንጅ እጅ መስጠት አልተለመደም ።ሞት ደግሞ የተፈጥሮ አንድ ገጽታ እንጅ አንተ አልፈጠርከውም፡፡ የሟቹን ደም  ከእጅህ እንፈልጋለሁ እንዳለ መጽሐፍ ከአንተ እጅ በጎንደርና በወልቃይት የፈሰሰው ደም እንፈልጋለን፡፡
ከአብራራው በጊዜው

No comments:

Post a Comment