ጎበዝ አልናፈቃችሁም ?? ልክ እንደ ሕወሓት ጄኔራሎች እንደ ጆቤና ጻድቃን የቤተዘመድ ፖለቲካ ተንትኖ የሚጽፍ። ሕወሓት እኮ ስትደነግጥ ሰላም ስታጣ መግቢያ ቀዳዳ ሲጠፋት ብርክ ሲይዛት ሰዎቹ ይሰባሰባሉ ይቸከችካሉ ማዘናጊያ ማስቀየሻ ማባበያ የሃሰት ዲስኩሮች ይደሰኩራሉ። ኣሁን ግን ሕዝብ ነቅቷል፤ የእከክልኝ ልከክልህ የቤተዘመድ ፖለቲካ የጎሳ ተላላፊ የመተዛዘን በሽታ በቃኝ የበይ ተመልካች ኣልሆንም ብሎ ሕዝቡ አጆቹን እያነሳ መታሰሩን በኣደባባይ አየነገራቹህ ነው ልቀቁን እያለ።
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ሕወሓቶች ለመደጋገፍ የሚያደርጉት እና በየዘመዶቻቸው ጋዜጣና ድረገጽ ላይ የሚለጥፉት ባለ ምናምን ገጽ ኣደጋ ላይ ነን የሚል ሮሮዋዊ ጽሁፍ (እከክ) ሕዝብ ላይ ሊያራግፉት አንደሚፈልጉት ሁሉ ስርዓቱ ገምቷል በስብሷል ለውጥ ያስፈልጋል ብለው የሚጽፉ የብ አዴን እና የዖሕዴድ ኣባላት ናፍቀውኛል ፤ ከባለተራዎቹ ጄኔራል ሞላ እነ ጄኔራል ገዛኢ በፊት የናፈቁን ኦሕዴዶችና ብአዴኖች ስለ ስርዓቱ ክፋትና ግፍ ተንትነው ለውጥ እንደሚያስፈልግ ልክ እንደ ሕወሓት ጄኔራሎች በጽሁፍ ይንገሩን ፤ ምነው ፈሩ ወይ ተጽፎ ኣልተሰጣቸውም ድሮ በረከት ስምዖን ነበር የሚያንጫጫው ኣሁን እሱም በሕመሙ ላይ የደሕንነት ባለስልጣናት ኣርጩሜ ኣርፎበት የታይታ ዘመኑን በለሆሳስ ኣድርጎታል።ኣሁንም ልድገመው ከብአዴን ወይም ከኦሕዴድ ስርዓቱ በስብሷል ፤ በሕዝብ ተጠልቷል ብሎ የሚቸከችክ ናፈቀን።
No comments:
Post a Comment