Wednesday, July 13, 2016

በጎንደር የተነሳው የሕዝብ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተከትሎ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የምክር ቤት ኣባላት ላይ ሕወሓት ዛቻ ጀምሯል። ‪


 በጎንደር የተነሳው የሕዝብ ጸረ ወያኔ እንቅስቃሴ ተከትሎ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና የምክር ቤት ኣባላት ላይ ሕወሓት ዛቻ ጀምሯል። 
እሪበይ ሀገሬ's photo.
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ሳንጃ እና ኣከባቢው ከባድ ውጥረት ላይ ነው፤ ዳንሻ ከፍተኛ ጦርነት እየተካሔደ ነው። መስሪያ ቤቶች ዝግ ናቸው። ስሜን ጎንደር ሰራተኞች እና ነጋዴዎች ወደየስራቸው ባለመሄዳቸው እንቅስቃሴዎች በጣም መቀዝቀዛቸው ተሰምቷል። የኣማራ ክልል ምክር ቤት ኣባላት ስለጎንደር ሕዝባዊ ቁጣ እንዳንጠይቅ በስልክ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እየደረሰብን ነው ሲሉ ጠቆሙ፤ከትላንትና ወዲያ ለሊቱን የኣማራ ክልል ባለስልጣናት እና የክልሉ የጸጥታና ደህንነት ክፍል በፍጹም በማያውቀው መንገድ ከትግራይ ተነስተው ወደ ጎንደር የገቡት የሕወሓት የደሕንነት ሃይል ኣባላት እና የሕወሓት ልዩ ሃይል ወታደሮች የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ኮሚቴ አመራሮችን ለማፈን ያደረጉት ሙከራ ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ቁጣ ቀስቅሶ ሕዝቡ በስልጣን ላይ ያለውን ኣገዛዝ እንደማይፈልግ ከትግራይ ልዩ ሃይል ወታደሮች ጋር በመፋለም በጎንደር ከተማ ጀግንነቱን እያሳየ ይገኛል።
የሕዝቡን ቁጣ ተከትሎ ለሆዳቸው ያደሩ የብ አዴን ኣባላትን ሕዝቡን እንዲያዘናጉ ያሰማራው ሕወሓት በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ዛቻ ጀምሯል። ሕዝቡ በሕወሓት ኣገዛዝን እንደማይፈልገው በተግባር ያሳየ ሲሆን በኦሮሚያ ክልል የተነሳው የሕዝብ ኣመጽን በኣማራው ክልል ደግሞታል፤ ሕወሕት በክልሉ ለሚገኙና ከክልሉ ባለስልጣናት ጀርባ ላስቀመጣቸው የራሱ ሰዎች መረጃ በመስጠት የጎንደርን ከተማ ጥሶ ሲገባ እና ሕዝብን ሲያሸብር የጉዳዩን ኣሳሳቢነት የተናገሩ የክልሉ ባለስልጣናት ኣስቸኵዋይ ስብሰባ እንዲጠራ ቢጠይቁም ሕወሓቶች ከልክለዋቸዋል።የክልሉ ምክር ቤት ኣባላት እንዳሉት ማንነታቸውን የማናውቃቸው ሰዎች እየደወሉ ነው በማለት የገለጹ ሲሆን ስለ ክልሉ ጉዳይ ኣያገባችሁም ኣርፋቹ ተቀመጡ የደወልንበትን ቁጥር ኣሳልፋቹ ብትሰጡ ማን ጋር በየትኛው ቁጥር እንደተደወለ ስለተመዘገበ እንደፋቹሃለን በማለት እየዛቱ ይገኛሉ ሲሉ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment