የአማራ ቴሌቪዥን የሳትላይት ዓለም አቀፍ ሥርጭት ከዛሬ ሐምሌ 15 ቀን 2008 ዓ.ም. ጠዋት ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል፡፡ የአማራ ክልል ቴሌቪዥን ከሳትላይት ላይ ወርዷል፡፡ ሥርጭቱ ተቋረጠ የተባለበት ምክንያት የአማራ ክልል መንግሥት የሳትላይት ኪራይ ለኢቢሲ ከፍሎ ኢቢሲ ደግሞ ለኢትዮ ቴሌኮም መክፈል ስላልቻለ ነው የሚል ቢሆንም ከባህር ዳር አካባቢ የሚወጡ መረጃዎች ግን ይህን አያረጋግጡም፡፡
አንዳንድ ለአማራ ሕዝብ ተቆርቋሪ የሆኑ የክልሉ አመራሮች የአማራውን ተጋድሎ በሚገባ እንዲዘግብ በመቁረጣቸው ምክንያት ከሕወሓት ጋር በተፈጠረ ልዩነት ነው የሚሉ መረጃዎች አሉ፡፡ ከአማራ ቴሌቪዥን ውጭ የሁሉም ክልል ቴሌቪዥኖች ከሳትላይት አልወረዱም፡፡
በብአዴን እና በሕወሓት መካከል ያለው አለመግባባት ግልጽ እየወጣ ነው የሚሉ ወገኖች ቢኖሩም የአማራውን ሕዝብ ማዘናጊያ እንዳይሆንም ስጋታቸውን የሚገልጹ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡
No comments:
Post a Comment