Friday, July 15, 2016

ኮሎኔል ደመቀ ያለበት ሁኔታ ለጊዜው አስተማማኝ ቢመስልም ዋስትና የለም


ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በተመለከተ
ኃላፊነቱን የጎንደር ከንቲቫ ተቀባ ተባባልና የዞኑ የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር ዋኘው ይወስዳሉ!
ኮሎኔል ደመቀ ያለበት ሁኔታ ለጊዜው አስተማማኝ ቢመስልም ዋስትና የለም፤ ትናንት በነበረኝ መረጃ ኮሎኔል በነጻነት ከሕዝቡ ጋር እንዳለ ነበር፤ ሆኖም ይህ ሙሉ በመሉ ትክክል አይደለም (ማንኛውም ሰው ጋር መገናኘት በመቻሉ ብሎም የጎንደር ፖሊሶች ጋር በመሆኑ ነው ከሕዝብ ጋር ነው የሚል መረጃ የሰጡን አካላት)፡፡
ኮሎኔል ደመቀን ያለው በዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሲሆን ጥበቃ እያደረጉለት ያሉ ግን የጎንደር ዐማሮች ናቸው፡፡ ከንቲቫ ተቀባና ኮማንደር ዋኘው ለእርሱ ደኅንነት በሚል በፖሊስ መምሪያ ለብቻው ያስቀመጡት ሲሆን በሕወሓትና በቁርጠኛ የዐማራ ልጆች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል፡፡ የፖሊስ አባላቱና እየጠበቁ ያሉት የጎንደር ዐማሮች እነርሱን ቅድሚያ ካልገደሉ በስተቀር ሊወስዱት እንደማይችሉ ተናግረዋል፡፡
ኮሎኔል ደመቀን የፌደራል መንግሥት ከወሰደ የሚደርሰው አደጋ ቀላል አይሆንም፤ በሁለት ቀናት ውስጥ የተወሰዱት የኮሚቴ አባሎች ይፈታሉ የሚል መልስ ተሰጥቷል፡፡ ሕወሓት ይህን በውዴታ እንደማያደርገው የሚታወቅ ቢሆንም ዐማሮቹ ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ተዘጋጅተው እየጠበቁ ነው፡

No comments:

Post a Comment