

የአማራ ገበሬ ጦር ቦታ ይዞ እዬተጠባበቀ ነው። አራቱ ታፍነው የተወሰዱ ኮሚቴዎቻችን በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቀዋል። ያ ካልሆነ ከፍተኛ አደጋ እንደሚጥሉ ተናግረዋል። በአራቱም አቅጣጫ ወደ ከተማዋ የአማራ ገበሬ ጦር እዬተመመ ነው። ምንም እንኳ በየኬላው የመከላከያ ጦር ዘግቶ ቢጠብቅም አማሮች መግቢያ አላጡም ።በዛሬው እለት ብቻ ሁለት ከፍተኛ የህወሓት ደህንነቶችና ሶስት የፌዴራል ፖሊሶች ተገለዋል። የህወሓት ደጋፊ ንግድ ቤቶች ወድመዋል። ፩ኛ ሁመራ ፔኒስዬን – ፪ኛ ጣና ሆቴል – ፫ኛ ሮማን ሆቴል – ፬ኛ ቋራ ሆቴል …ከቀላል እስከ ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸው ሆቴሎች ናቸው። ወርቅ ቤቶችም አላመለጡም።ህዝቡ በምሬት የህወሓት ደጋፊ የሆኑ የትግራይ ተወላጆች ጎንደርን ለቀው እንዲወጡ ሲያሳስብ ውሏል።
No comments:
Post a Comment