Sunday, July 3, 2016

ዶ/ር መረራ ጉዲና የፕሮፌሰርነት ደረጃዬን ያለአግባብ ከልክሎኛል ሲሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከሰሱ


ዶ/ር መረራ ጉዲና የፕሮፌሰርነት ደረጃዬን ያለአግባብ ከልክሎኛል ሲሉ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከሰሱ
የፕሮፌሰርነት ደረጃዬን ያለአግባብ ከልክሎኛል ብለዋል
300 ሺ ብር የሚጠጋ የገንዘብ ክስም አቅርበዋል
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፕሮፌሰርነት የደረጃ እድገቴን ያለ አግባብ ከልክሎኛል ያሉት ዶ/ር መረራ ጉዲና፤ ከዩንቨርስቲው ማግኘት የሚገባኝን የአገልግሎትና ልዩ ልዩ ክፍያዎችም ነፍጎኛል ሲሉ ክስ አቀረቡ፡፡
ለፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት፣ መናገሻ ምድብ ሥራ ክርክር ችሎት የቀረበው የዶክተር መረራ የክስ ማመልከቻ፤ በዩንቨርስቲው ውስጥ ከግማሽ በላይ ዕድሜዬን ያገለገልኩና ብርቱ፣ ብቁና ተጠያቂ ዜጐችን ሳፈራ የቆየሁ ሲሆን ለፕሮፌሰርነት ደረጃና የሙያ እድገት ብቁ የሚያደርገኝን መስፈርቶች ሁሉ ያሟላሁ ቢሆንም፣ የፕሮፌሰርነት ደረጃውና እድገቱ በ3 ወር ጊዜ ወስጥ ሊፈቀድልኝ ወይም ሊሰጠኝ ሲገባ፣ ያለ ሕግ አግባብ መብቴን ተነፍጌአለሁ ይላል፡፡
ዩኒቨርሲው ያለ ህግ የነጠቀኝን መብቴን እንዲሰጠኝና የፕሮፌሰርነት ማዕረጉ እንዲፈቀድልኝ፣ እንዲሁም በዩንቨርስቲው ውስጥ ለረዥም ዓመት የሰራሁበት የአገልግሎት ክፍያም 282 ሺ 960 ብር እንዲከፈለኝ እጠይቃለሁ ብለዋል – ለፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ፡፡

No comments:

Post a Comment