Thursday, April 14, 2016

ትክክለኛውን ቴዲ አፍሮን ምን ያህሎቻችን እናውቀዋለን? (ኤርሚያስ ቶኩማ

ክክለኛውን ቴዲ አፍሮን ምን ያህሎቻችን እናውቀዋለን? (ኤርሚያስ ቶኩማ)

Teddy Afro
ከኤርሚያስ ቶኩማ
ብዙዎቻችን ቴዲ አፍሮን ከሙዚቃ ሥራውና ከሐገር ወዳድነቱ ባሻገር እምብዛም የግል ሕይወቱን እና ምን አይነት ሰው እንደሆነ አናውቀውም እርሱም ቢሆን ስለራሱ ማውራት ስለማይወድ እና ይህንን ፈፀምኩኝ ብሎ ስለማያወራ የቴዲን ማንነት በግልጽ ልናውቀው አልቻልንም ሆኖም ቴዲ አፍሮ እንደዚህም አይነት ሌላ ገፅታ አለው።
★ ሐምሌ 30,1998 ዓመተ ምሕረት በድሬዳዋ ደርሶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ30 ሺህ ብር ድጋፍ በማድረግ ለወገን ደራሽነቱን አሳየን።
★ ጥቅምት 1,2002 Elshaday Relief and Development ባዘጋጀውና ከ50 ሺህ በላይ በተገኘበት የአዲስ አበባ ስታዲየሙ ኮንሰርት ከ 1 ሚሊየን ብር በላይ አሰባስቦ ለእርዳታ ድርጅቱ ያስረከበ ሲሆን በእለቱ ለአበበች ጎበና ሕፃናት ማሳደጊያ 100 ሺህ ብር ለይልማ ገ/አብ የወርቅ ብእር ሸልሟል።
★ ጥቅምት 23,2002 በህመም ላይ ትገኝ ለነበረችው ማንአልሞሽ ዲቦ መታከሚያ ይሆን ዘንድ 20 ሺህ ብር አበረከተ
★ ጥቅምት 17,2004 የወጣት አስመሮም ሃይለስላሴን ነፍስ ለማዳን ለሶማሊያ ሽማግሌዎች 700 ሺህ ብር ከፈሎ የወገኑን ህይወት አተረፈ።
★ ጥቅምት 17,2004 ለኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ማህበር የ200 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎ ለማህበሩ ያለውን አጋርነት አሳየ። ማህበሩም የምስጋና ምስክር ወረቀት ሰጥቶታል።
★ የአራት ኪሎ ወጣቶች ከአልባሌ ሥፍራ ይርቁ ዘንድ በአባቱ ስም ተቋቁሞ ለነበረው የእግር ኳስ ቡድን ለአራት አመታት በየአመቱ ግማሽ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል።
★ በራሱ አነሳሽነት ለአበበ መለሰ ኮንሰርት በማዘጋጀት የአርቲስቱን ህይወት ከህልፈት ታደገ።
★ ጥቅምት 2005 ቀድሞ ይማርበት ለነበረው ቤቲልሄም ት/ቤት የኮምፒውተር እና የሙዚቃ መሣሪያ ድጋፍ አደረገ።
★ በተለያየ ግዜያት በተዘጋጁ ዝግጅቶች ላይ እንደዚሁም እዛው ድረስ በመሄድ ለወይዘሮ አበበች ጎበና እፃናት ማሳደግያ ከመቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ እርዳታ።
★ ባለቤቱ አምለሰት ባስመረቀችው አረንጋዴ መሬት ዶክመንተሪ ፊልም ምርቃት ላይ በእንጨት ለቀማ ይተዳደሩ ለነበሩ እናት የ 20ሺብር ቼክ ሰታቸዋል።
★ እንደዚሁም ለተለያዩ ድምፃዊያን ግጥም እና ዜማ በነፃ የሰጣቸውም አሉ::
ይህ ነው የቴዲ አፍሮ ሌላው ገፅታ ይህ ህዝቡ የሚያውቀው ነው ቴዲና ድጋፍ ያደረገላቸው ብቻ የሚያውቁት ብዙ አለ።
ማሳሰቢያ:- ይህንን ፅሁፍ በድጋሚ የለጠፍኩት አንድ በምርቃና የድሮ መጽሔት ጽሁፎችን እየገለበጠ መፅሀፍ ካሳተመ በዃላ እራሱን እንደደራሲ ቆጥሮ ለመተቸት የሞከረ በጫት የደነዘዘ ወጠጤ በማየቴ ነው።

No comments:

Post a Comment