Tuesday, April 5, 2016

በመሃል ሾልከው የገቡትን የወያኔ አሳሞችን ለማሳፈር ትልቁን ድርሻ መወጣት ያለብን እኛ የለውጥ ሃይሎች ነን::

በተቀደደበት ከመፍሰስ ያውጣን::ትግል ፈተና ቢበዛውም ቀድሞ በስሎ መገኘትን ይጠይቃል::ለለውጥ እየታገንል ነው እያልን የጋራ አቋማቸውን በሆኑ የለውጥ ሃይሎች ላይ ከመዛነፍ ያድነን::በያለንበት ቦታ በየምንታገልበት መስመር የለውጥ ሃይሎች ነን የምንል ሁሉ መመካከር ይገባናል::ወያኔ መጥቶ አይመክረንም::የለውጥ ሃይሉ እየሰራ ከሚገኘው ጥሩ ስራ በላይ ለመስራት እርስ በርሱ ሊጠባበቅ ይገባል ክፍተት መፍጠር አያስፈልግም::የተያዘው መንገድ ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም ከዚህ በላይ ሊሰራ ይገባል::በመሃል ሾልከው የገቡትን የወያኔ አሳሞችን / ቅጥረኞች ለማሳፈር ትልቁን ድርሻ መወጣት ያለብን እኛ የለውጥ ሃይሎች ነን::ሁላችንም ስራችን ወያኔን በማስወገድ ስራ ላይ ብቻ መሆን አለበት::በለውጥ ሃይሉ ይሁን በተቃዋሚ ፓርቲዎች አከባቢ ያሉ ችግሮችን በውስጥ መስመር ተነጋግሮ መተራረም መመካከር እንደሚቻል መዘንጋት የለብንም::
ከወያኔ ካድሬዎች የጋራ ርብርቦሽ የለውጥ ሃይሉ ምን ይማራል::ወያኔዎች አስመሳይ ፖለቲካ ሰርተው በተዘዋዋሪ የልባቸው ለማድረስ እስከሚሮጡበት ገመድ ጨምሩ ሁሉም ድንጋዮቻቸውን የሚወረውሩት ወደ ለውጥ ሃይሉ መሆኑ እሙን ነው::እርስ በርሳቸው ባይስማሙም በይፋ አይናቆሩም ክፍተታቸውን ለመድፈን እንጂ አሳልፎ ለመስጠት አይሮጡም::የለውጥ ሃይል ይህንን በጋራ ወያኔ ላይ የመዝመት የትግል አንዱን ክፍል ልንጠቀምበት ይገባል::በቡድን አይደለም በግለሰብ ደረጃ ወያኔዎች አንዳቸው አንዳቸውን ሊመቱ ሊጠልፉ አሊያም ሊያዋርዱ ሲልም ሊያርሙ እንኳን አይፈልጉም::መስተካከል ያለበትን በውስጥ መስመር እንደሚተራረሙ ልምዳቸው መሆኑ እያየን ነው::የለውጥ ሃይሎችን እርስ በራስ የመኮራኮም የመሸረዳደድ ባህርያትን አስወግደው ዘመቻቸው ሁሉ ወያኔን በመጣል ላይ ሊሆን ይገባል::
በመሃል ሾልከው ገብተው የተቃዋሚ ተቃዋሚ የለውጥ ሃይሉ እንቅፋት ለመሆን የሚታትሩትን ሁሉ ልናሳፍራቸው እና በቃችሁ ልንላቸው በነሱ አጅንዳ ላንፈስላቸው ራሳችንን በብስለት ማገዝ ያስፈልገናል:: በተራ ወሬ እና በፈጠራ ታሪክ ሊያሽቃብጡን ስለሚፈልጉ ከነሱ ቀድመን መገኘት ግድ ይለኛል:: በየማህበራዊ ድህረገጹ የተለቀቁትን የወያኔ ሰርጎ ገቦችን በጋራ ሃይላችን ልንደቁሳቸው ይገባል::በመሃል ሾልከው የገቡትን የወያኔ ቅጥረኞች ለማሳፈር ትልቁን ድርሻ መወጣት ያለብን እኛ የለውጥ ሃይሎች ነን:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment