Saturday, April 16, 2016

አርቲስት ጌታመሳይ አበበ በ72 ዓመታቸው አረፉ

 


የጌጡ ተመስገን ዘገባ
የጠለቀ የመሰንቆ ዕውቀትና ችሎታው ‹‹የመሰንቆው ሊቅ›› የሚል መጠሪያ አጎናጽፏቸዋል። ጌታመሳይ አበበ በሰሜን አሜሪካ፣ በአውሮፓና በአፍሪቃ በመዟዟር የኢትዮጵያን የባሕል ጨዋታ በተለያዩ አለም አቀፍ መድረኮች ላይ ያንፀባረቁ አንጋፋ የባሕል ተጫዎች ነበሩ።
ጌታመሳይ አበበ በአሩሲ ክፍለ ሀገር ልዩ ስሙ አልባሶ በተባለ ቦታ በ1935ዓ.ም. ተወለደ። ባለመሰንቆው ጌታመሳይ በሙያው ተማርኮ እጁን ለሙዚቃ የሰጠው ገና ልጅ ሳለ በሚኖርበት ሠፈር አካባቢ ሠርግና ክርስትና ሲኖር መሰንቆ ይጫወቱ የነበሩትን በማየት ልቡ እጅግ ከተነሳ በኋላ ነበር። ጌታመሳይ በግል ጥረቱ እንጨት እያጎበ፣ የፈረስ ጭራ በማሰር፣ መሰንቆ መጫወት በመቻሉ ስሜቱ ወደዚህ ሙያ እንዲያመራ አስገደደው።

በሕጻንነት የጀመረው የሙዚቃ ፍቅር የተለያዩ ደረጃዎችን ተሻግሮ በበኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ለሦስት ወራት በነጻ አገልግሎት ሥራ ጀመሩ፣ ቀጥሎም በ40 ብር ወርሃዊ ደመወዝ ለስድስት ወራት ተቀጠሩ። በቀድሞው የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የባሕል ማዕከል ሲደራጅ በ1954 የቡድኑ አባል ሆኖ በድምጻዊነትና መሰንቆ ተጫዋችነት የተቀጠረ ሲሆን ከፍተኛ ሙያዊ ሥራዎችን አበርክተዋል። በመቀጠልም በሀገር ፍቅር ቴአትር በድምጻዊነት፣ በመሰንቆ ተጫዋችነትና የአገረሰብ የሙዚቃ ክፍል ኃላፊና አደራጅ በመሆን አገልግለዋል።
‹‹የመሰንቆው ሊቅ ››፤ ጌታመሳይ አበበ ከ200 በላይ ዜማዎችን የተጫወተ መሆኑ የተወሳው ከያኒው በዜማ ድርሰት፣ በድምጻዊነት፣ በኃላፊነት፣ በመምህርነት እንዲሁም የባህል ቡድኖችን በመምራት በተለያዩ አገራት ኢትዮጵያን የማስተዋወቅ እንቅስቃሴዎችን በበላይነት መርቷል።
አገራዊ እሴትን፣ የአገር ፍቅርንና ጀግንነትን የሚያንጸባርቁ ሥራዎችን በማቅረብ የሚታወቀው ጌታመሳይ አበበ ‹‹የሽምብራው ጥርጥር›› ፣ጥርጥር››፣ «ሆብዬ እመጣለሁ»,፣ ‹‹የኔ አያል›› ፣ «ሀገር መውደድ ማለት»፣ ‹‹እናት ውብ አገሬ››፣ ‹‹ወሸባዬ፣ «ዳይመኔ»፣ «የመኖሪያ ቤቴ» ፣ ‹‹ሰላሜ ሰላሜ›› እና ሌሎችም አገራዊ ስሜትን ከፍ የሚያደርጉ ሥራዎቹ ተጠቃሽ ናቸው።
‹‹የመሰንቆው ሊቅ ››፤ ጌታመሳይ አበበ በሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት ከዘፋኝነት በተጨማሪም የትያትር ሙያን ሊማር በመቻሉ ከአሥር በላይ በሚሆኑ ትያትሮች ከዕውቅ አርቲስቶች ጋር በመሆን ሠርቷል። የአቤ ጉበኛ «የደካሞች ወጥመድ»፣ የብርሃኑ ዘሪሁን «የለውጥ አርበኞች» እና የጌታቸው አብዲ «ስንት አየሁ» ትያትሮችን ላይ ተጫውቷል።
በተዘዋወረባቸው የባሕልና ኪነት ጉዞዎች ባሳዩት ጽናት በርካታ ሽልማቶችን አግኝተዋል። በ1996 ዓ.ም ባጋጠመው የጭንቅላት ዕጢ ህመም አጋጠማቸው፡፡
ባሳለፍነው ሳምንት ሚያዝያ 6/2008ዓ.ም. ባህል ማዕከል ሲመጡ በዊልቼር እገዛ ነበር፡፡ መናገርና መራመድ አይችሉም ነበር። ብዞዎችን አስለሰው ነበር፡፡ ‹‹የመሰንቆው ሊቅ ››፤ ጌታመሳይ አበበ የካባ፣ የአገር ባሕል ልብስ፣ የዋንጫና የምስክር ወረቀት ሽልማቶችን ተበርክቶላቸው ነበር።
ነበር … ነበር … ነበር …
የ ሽምብራው ጥርጥር የ ዛፎቹ ፍሬ
የትም ዞሬ ዞሬ ትዝ አለኝ አገሬ።
ነፍስ ይማ

No comments:

Post a Comment