Thursday, May 12, 2016

ወታደራዊ ሹማምንቶች ስልጣኑን ተረክበው ሌላ የደርግ አይነት ስርዓት ሳይፈጠር ተግባራዊ ስራዎች ላይ እናተኩር::

 ስለ ወያኔ አገዛዝ አስከፊነት ደግሞ ደጋግሞ ከማውራት መፍትሄው አስከፊ አገዛዙን በጋራ እናስወግድ::አሁን አሁን ትግሉ ከአጥቂነት ወርዶ ወደ ወሬኛነት ቀይረነዋል::ለአስከፊነት ለእኩይነት ለክፋት ራሱን ያስገዛውን ስርዓት ገርስሶ ከመጣል ይልቅ ሁልግዜ ደካማ ጎኑን በማውራት ከመፍትሄ ፈጣሪነት ይልቅ ወሬ ፈጣሪዎች ሆነናል::ሕዝቡ ይህንን የወሬ ናዳ ከመላመዱ የመጣ ከንፈር መጣጭ ሆኖ ቀርቷል::መፍትሄውን ቢላመድ ኖሮ ፈጣን እርምጃ ይወሰድ ነበር::እርስ በርሳችን መባላት እርስ በርሳችን መወቃቀስ እስር በርሳችን መሰዳደብ እርስ በርሳችን መፈራረጅ እርስ በርሳችን መገፋፈጥ እርስ በርሳችን በሃስት ስማችንን መጠፋፋት ስራችን የሆነው የለውጥ ሃይሎች ወያኔን ወደ መደምሰሱ ስራ/ተግባር መች እንደምንገባ እስካሁን ጊዜው አለየም::ወታደራዊ ሹማምንቶች ስልጣኑን ተረክበው ሌላ የደርግ አይነት ስርዓት ሳይፈጠር ተግባራዊ ስራዎች ላይ እናተኩር::
ወያኔ ገዳይ ነው አዎ ገዳይ ነው!! ወያኔ ውሸታም ነው አዎ ውሸታም ነው!! ወያኔ ሙሰና ነው አዎ ሙሰኛ ነው!! ወያኔ አሸባሪና አሸባሪዎችን ፈልፋይ ነው አዎ ነው::ወያኔ ሞላጫ ሌቦች የተሰበሰቡበት አገዛዝ ነው አዎ ነው::ወያኔ ዘረኛ ነው አዎ ነው::ወያኔ ንጹሃንን በገፍ ያስራል አዎ ያስራል …ወዘተ… የምናውቀው እና ፀሃይ የሞቀው ሃቅ ነው::ስለዚህ ለዚህ መፍትሄው ደግሞ ይህን አስገፊ እና ግፈኛ ገዳያ እና የሌቦች ማእከል የሆነውን የማፊያ ቡድን ማስወገድ ነው:: መፍትሀው አንድ እና አንድ ብቻ ነው የለውጥ ሃይል ነኝ የሚለው አካል እርስ በርሱ ከሚገለማመጥ እና በፖለቲካ ጥላቻ ታጥሮ ከሚባላ ወያኔን ማስወገድ ቁልፍ መፍትሄ ነው::አለመተማመን እና በተናጠል ቡድን እየለዩ በጎሪጥ ጥላቻ መተያየት በፍጹም ለውጥ አያመጣም::የወደደ ይውደድ የጠላ ይጥላ…መንገዱ ይህ ብቻ ነው::
በ1997 ቅንጅት ሕዝቡን መፍትሄ ለማስተማር 6 ወር አልፈጀበትም ነበር ::ከከንፈር መጣጭነት ወደ ውሳኔ ሰጥነት ተሻግሮ በድምጹ ወያኔን እምቢ ያለውም ለዚሁ ነበር::በየቀኑ ወያኔ የሚሰራቸውን ግፎች እያነሳን ከንፈር ከመምጠጥ በጋራ ቆመን መፍትሄ የሚሆነንን ሃገራዊ ስትራቴጂ ይዘን ወያኔን በመደምሰስ ያስፈልጋል:;አንዱ የሚያደርገውን ትግል ሌላናው የለውጥ ሃይል የሚያንቋሽሽ እና የኔ ብቻ ምርጥ ብሎ የሚያስብ ከሆነ የተመነነውን ለውጥ 100 አመትም አናገኘውም::በመግባባት በመቻቻል ልዩነት ውበት መሆኑን በመቀበል ድር ቢያብር አንበሳ ያስር በሚለው ብሂል መሰረት ትልቅ ስራ ሊሰራ ይችላል ካልሆነ ግን እስካሁን እንዳለነው በወሬ እና በተምትታ የፕሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ብቻ እንደደሰኮርን እንኖራለን አሊይም ወያኔ እንደበሰበሰ ሲገነደስ ሮጠን አራት ኪሎ ቤተ መንግስት እንገባለን ተብሎ የሚታሰብ ካልኩሌሽን የተበላበት እቁብ ስለሆነ ወታደራዊ ሹማምንቶች ስልጣኑን ተረክበው ሌላ የደርግ አይነት ስርዓት ሳይፈጠር ተግባራዊ ስራዎች ላይ እናተኩር::ስለ ወያኔ አገዛዝ አስከፊነት ደግሞ ደጋግሞ ከማውራት መፍትሄው አስከፊ አገዛዙን በጋራ እናስወግድ::‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment