Monday, May 30, 2016

የብሄራዊ ፈተናው መሰረዝ ለሕዝብ ልጆች ድል ለአገዛዙ የፖለቲካ ኪሳራ ነው:: አንድ እውነት … !!!



አገዛዙ ያልገባው እያወቀ ሊውጠው የማይፈልገው አንድ እውነት አለ::ይህም ሕዝብ ለውጥ ይፈልጋል ሕዝብ ነጻነት ይፈልጋል:: ሕዝብ እኩልነት ይፈልጋል:: ሕዝብ የመንግስት ሌቦችን ተሸክሞ ሊጓዝ በፍጹም አይሻም:: ሕዝብ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መብቱ እንዲገፈፍ በፍጹም አይፈልግም::ሕዝብ ከቀየው ከኖረበት በጉልበተኛ የመንግስት ማፊያዎች እንዲፈናቀል አይፈልግም::በወያኔ አገዛዝ እጅግ በርካታ ወንጀሎች በሕዝብ ላይ እየተሰሩ ነው::አገዛዙ አናቱ የገማ ሲሆን ከስሩ ያሉትም አባሎቹ ሳይቀር ለውጥ ይፈልጋሉ::የሕዝብ ልጆች ነጻነትና የመብት ጥያቄ ጎን ብመቆም ታላቅ ስራ እየሰሩ ይገኛሉ::ይህ ደግሞ ለአገዛዙ የፖለቲካ ኪሳራ ለሕዝብ ደግሞ ድል ነው::የመላው ኢትዮጵያ ተማሪዎች ከኦሮሚያ ክልል ተማሪዎች ጎን ሊቆሙ የወገናዊነት ግዴታ አለባቸው::
Minilik Salsawi's photo.
የወያኔው አገዛዝ ሁሉ ነገር ከእጁ አፈትልኮ ወቷል::ካሁን በኋላ ማስተካከል ስለማይቻል ያለው አማራጭ ስልጣን መልቀቅ ብቻ ነው::የሕዝብ ልጆች ባልተሳተፉበት የመንግስት ስርዓት ውስጥ ዜጎች አያገባችሁም በተባለበት በገዛ አገራቸው ውስጥ ካሁን በኋላ ሕዝብን አስተዳድራለሁ ብሎ ማሰብ ጅልነት እና ሞራለ ቢስነት ነው::ይህን ደግሞ ማናቸውም ኢትዮጵያን እናስተዳድራለን ብለው የሚመኙ ፖለቲከኞች ሊያውቁት ይገባል::የሕዝብ ልጆች የጋራ ትግል ማንኛእንም አምባገነን ስርዓት ገዝግዞ የመጣል አቅሙ ብርቱ ነው::በኦሮሚያ ክልል የተደረጉ ተቃውሞዎችን ተከትሎ አመቱን በከፊል ከአስተማሪ ጋር ሳይሆን ከፌዴራል ፖሊሶች ጋር ሲፋጠጡ የነበሩ ተማሪዎችን ካለምንም ዝግጅት ፈተና ላይ ለማስቀመጥ ያሰበው አገዛዝ ሊያወትበት ካለመው የተማሪው ሞራል በተጫረ ክብሪት ከባድ እፍረትን ተከናንቧል::
ትግሉ አሁንም ይቀጥላል!!! የሕዝቦች ትግል ተጀመረ እንጂ አላለቀም የኢትዮጵያ ሕዝብ በተለያዩ ብልሃቶቹ አገዛዙ አያመነመነ በማደባየት ይቀብረዋል::ይህ በፍጹም የማይታጠፍ ሃቅ ነው::ፈተናውን በሰላም ተዘጋጅተው ለመፈተን ያሰቡ ተማሪዎች ፈተናው ሲቋረጥ የሚያሳዝናቸው ከሆነ በገዛ ወንድሞቻቸው ላይ አደጋ መሆናቸውን መዘንጋት የለባቸውም::ፈተናው መቋረጡ ለሃገራቸው መጻኢ እድል አስታውጾ እንደሚያደርግ ሊገባቸው ይገባል::ፈተናው በመቋረጡ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ተማሪዎችን የትግል የስኬት የድል ሞራል ከፍ እንደሚያደርገው ልሊያውቁት ይገባል::ማንም በማንም ላይ ተረማምዶ የልጥላውን መብት ተጋፍቶ ፈተና መቀመጥ ለነገ አደጋ እንደነበረው በመገንዘብ ፈተናው መቋረጡ በመላው አገሪቱ የሚኖሩ የማትሪክ ተፈታኦችን ሊያስደስት ይገባል::ተጀመረ እንጂ አልተቋጨም !!! ከሕዝብ ልጆች ጥያቄ እና እንቅስቃሴ የሚያመልጥ ማንም የለም:: …. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ብቻ ሳይሆን የአገዛዙም እስትንፋስ መቋረጡን በቅርቡ በራሱ ሚዲያ በሰበር ዜና ትሰማላቹህ::ይህ የኛ የሕዝብ ልጆች ቃል ነው:: ሁሉም ተማሪዎች ከኦሮሚያ ተማሪዎች ጎን ሊቆሙ ይገባል::ድል የሕዝብ ነው::

No comments:

Post a Comment