Tuesday, May 24, 2016

በዓዲ ሕርዲ የትግራይ ኮማንዶ ልዩ ሃይል ተሰማራ።

የቓፍታ ሑመራ ህዝብ ከቀበሌ እስከ ፌደራል በህወሓት እጅ የቆየው ውክልናየ ኣንስቻለው እያለ ነው።
በትግራይ ክልል ቓፍታ ሑአራ ወረዳ የዓዲ ሕርዲና ዓዲ ፀፀር በሩባሳ ኣከባቢ “ለወጣቶች የቤት ማታከያ ይሰጣልና በቦታው ተገኝታቹ ተረከቡ” የሚል የመንግስት ትእዛዝ ምክንያት በቦታው የተገኙ የሁለቱ ቀበሌዎች ወጣቶች ሳያስቡት በሩባሳ ኑዋሪዎች ጥቃት ስለተፈፀመባቸው የተነሳው ግጭት የዓዲ ሕርዲና ዓዲ ፀፀር ህዝብ “የመንግስት እጅ ኣለበት፣ ህዝቡ ለማጣላት ሆን ብሎ ሰርተዋል” በማለት ከፍተኛ ቁጣ ፈጥረዋል።
የሁለቱ ቀበሌዎች ህዝብ “ህወሓት በሁሉ መስክ ኣስተዳደራዊ ዘርፎች ለኛ የሚመጥን መንግስት ስላልሆነ ከዛሬ(እሁድ 15 ጉምበት) ከቀበሌ እስከ ፌደራል ይዞብን የነበረው ውክልናችን ኣንስተናል” ብለው ኣውጀዋል።
ይሄ ውሳኔ የተላለፈው ከ15 ሺ በላይ ህዝብ ለእሁድ 14 / 09 / 08 ዓ/ም ሰለማዊ ሰልፍ ለማካሄድ እንዲፈቀድላቸው ለወረዳው ኣስተዳደር የጠየቁ ሲሆኑ ወረዳው ጥያቄው ኣግዶታል።
የሰልፉ ክልከላ ተከትለው የሁለቱ ቀበሌዎች ኑዋሪዎች ራሳቸው ስብሰባ በማካሄድ ነባር የህወሓት ታማኝ ካድሬዎች በማባረር ከህዝቡ መሃከል የራሳቸው ህዝባዊ ኣስተዳዳሪዎች መርጠዋል።
የትግራይ መንግስት ኮማንዶ ልዩ ሃይል እሁድ ሌሊት ከመቐለ ወደ ስፍራው ልከዋል።
ኮማንዶ ልዩ ሃይሉ እሁድ 15/ 09 /08 ዓ/ምሌሊት ዓዲ ሕርዲ ቀበሌ ገብተዋል።
የዓዲ ሕርዲ ና ዓዲ ፀፀር ህዝቦች “የህወሓት ውክልናችን ኣንስተናል” ከእምባስነይቲ ቀጥለው ታሪካዊ ውሳኔ የወሰኑ ተጋሩ ኢትዮጵያውያን ሆነዋል።
ህወሓት ራስዋ ስልጣኔና ራሴ የወሰድኩት የህዝብ ውክልና ለህዝቤ መልሼ ኣስረክባለው ካላለች ህዝቡ በራሱ ተነሳሽነት በኣጭር ግዜ ሙሉ በሙሉ ሊነሳት እንደሚችል ክስተቱ ኣብሪ ምልክት ነው።
የትግራይ ህዝብ ህወሓት ኣትወክለኝም ማለቱ ቀጥሎበታል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው።
it is so.
Amdom Gebreslasie's photo.
Amdom Gebreslasie's photo.

No comments:

Post a Comment