Monday, May 23, 2016

የአንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ሐዘን ላይ መሆናቸውን ገለጹ * ቀነኒሳ በቀለ ቅሬታውን አሰማ – ወልቃይት ተወጥራለች

Hiber Radio: የወልቃይት ሕዝብ ዳግም በሕዝባዊ ስብሰባ አማራነታችን ይከበር በትግራይ ክልል አስተዳደር አንመራም ሲል ቁጣውን ገለጸ፣የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ቤተሰቦች ዛሬም ሐዘን ላይ መሆናቸውን ገለጹ፣አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለማራቶን በተደረገው ምርጫ ላይ ቅሬታውን ከድል በሁዋላ ይፋ አደረገ የሚሉና ሌሎችም ዜናዎችና ልዩ ልዩ ዝግጅቶች በፕሮግራሙ ተካተዋል

የህብር ሬዲዮ  ግንቦት 14 ቀን  2008 ፕሮግራም
<…ኢሳት እንደ ማንኛውም ሚዲያ እንቅስቃሴ ባለበት የበለጠ ትኩረት ይሰጣል። ከዛ ውጭ የማንንም ሀሳብ አናፍንም ነገር ግን በፖለቲካ ፓርቲ ስም የተቋቋመ ሁሉ መግለጫ ባወጣ ቁጥር ያንን ተከታትለን እንዘግባለን ማለት አይደለም።ቅሬታ ያላቸው ወገኖች የቅሬታቸው መነሻ ምክንያቱ የተለያየ ነው…ኢሳትን በዘረኝነት ለመክሰስ የሚሞክሩት የገዢው ፓርቲ ሰዎች የመከላከያ ሰራዊቱ ዋና ዋና ባለስልጣናት ከአንድ አካባቢ ከአንድ ብሄር መጡ ተብሎ ዕውነታው መዘገቡ ያበሳጫቸዋል።ዘረኛው ያንን ያደረገው ስርዓት ነው ወይስ ዕውነታውን የዘገበው? …> ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና ለኢሳት ስድስተኛ ዓመት በቬጋስ ያደረገውን ቆየታ መሰረት አድርገን  ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውንአድምጡት)
<…ኤምባሲ የሚባለው መጀመሪያ የአሜሪካ ኢሚግሬሽን መታወቂያችንን ሲጠይቀው ሀሰተኛ ነው አለ ቆይተው ያንኑ ሀሰተኛ ያሉትን መታወቂያ ሕጋዊ አድርገው ወደ ኢትዮጵያ ዲፖርት እንድንደረግ እየላኩ ነው ። ወገኖቻችን ድረሱልን እርዱን እኛን እየደገፉ ካሉት ጋር ቆማችሁ ካለንበት እስር ቤት እንድንወጣ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይልኩን ድምጻችንን አሰሙልን ዛሬም መፍትሄ አላገኘንም…> በፍሎሪዳ በተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ሀያ አንድ ኢትዮጵያውያን ስደተኛ እስረኞች መካከል ጥቂቶቹ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በእዚህ በፍሎሪዳ በሁለት የተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙት ኢትዮጵአውአን ስደተኞች በአምስት ሺህ ጠበቃ ቆሞላቸዋል ግን ያ በቂ አይደለም በተለይ ሰባቱ ከፍተና ችግር ላይ ናቸው ዲፖርት ለመደረግ የሚጠባበቁም አሉ ለእነዚህ ወገኖች ተረባርበን ልንደርስላቸው ይገባል አንዳንዶቺ ከመሀከላቸው በጭንቀት ለአእምሮ ህመም የተጋለቱ አሉ…> አቶ ከፍያለው ፈቃደ ከሚያሚ እና አቶ ሌሊሳ ሂካ በታምፓ ፍሎሪዳ የኦሮሞ ኮሚኒቲ ም/ሊቀመንበር ኢትዮጵያውያኑ ስላሉበት ሁኔታ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን አዳምጡት)
ቃለ መጠይቅ በእስር ቤት የሚገኘውን ወታቱን ፖለቲከና አብርሃ ደስታን ለመደገፍ በጎ ፈንድ ጥረት ከጀመረው ወጣት ጋር (አድምጡት)
በሲያትል የአርበኞች ግንቦት ሰባት የገቢ ማሰባሰቢያ ሊቀመንበሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በተገኙበት ተካሄደ ለጨረታ የቀረበው የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌና የፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ምስል በ72 ሺህ ዶላር ተሸጠ (ቃለ መጠይቅ በዝግጅቱ ላይ ከቬጋስ ተጉዞ ከተሳተፈው ወጣት ጋር ሙሉውን አዳምጡት
 ከፓሪስ ፈረንሳይ ወደ  ግብጽ ሲበር የነበረው  የመንገደኞች መጓጓዣ አውሮፕላን  ባለፈው ሃሙስ በሜዲትራኒያን ባህር ላይምስጢራዊ  አወዳደቅ እና ከጀርባው የነበሩ መላምቶች  ሲዳሰሱ።”ይህን አውሮፕላን እንከሰክሰዋለን “ማለት ለምን አሰፈለገ? (ልዩ ዘገባ)
በቬጋስ ሊፍት በጠራው ስብሳባ የዋጋ ማስተካከያን ጨምሮ የተሌአዩ የማሻሻያ እርምጃዎች እወስዳለሁ ብላል(የስብሰባውን ውሳኔ መሰረት ያደረገ ማብራሪያ)
 ሌሎችም
ዜናዎቻችን
የወልቃይት ሕዝብ ዳግም በሕዝባዊ ስብሰባ አማራነታችን ይከበር በትግራይ ክልል አስተዳደር አንመራም ሲል ቁጣውን ገለጸ
የአቶ አንዳርጋቸው ቤተሰቦች ዛሬም ሐዘን ላይ መሆናቸውን ገለጹ
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለማራቶን በተደረገው ምርጫ ላይ ቅሬታውን ገድል በሁዋላ ገለጸ
በቦሌ ወረዳ ዜሮ ስምንት ውስጥ ሕገ ወጥ በሚል የልደታ ቤተክርስቲያን በግብረ ሀይል ፈረሰ
በኦሮሚያ ክልል አሁንም የአገዛዙ ጥቃት አላቆመም 60 ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከአለማያ ዩኒቨርስቲ በአጋዚ ወታደሮች ታፍነው ተወሰዱ
የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ከጋምቤላ ከታፈኑት ህጻናት ግማሹን መልሰናል አሉ
በከበባ ስም የዋሸው የኢትዮጵያው አገዛዝ ሁሉም እንዲመቱ ቀነ ገደብ ሰጥቻለሁ አለ
ንብረትነቱ የግርማዊ ጃንሆይ የሆነ የወርቅ ሰዓት ጄነቫ ውስጥ ታላቅ ውዝግብ አሰነሳ
ኤሪትራ  ወደ ግዛቴ ዘልቀው ገብተዋል በማለት ለወራት ያስረቻቸውን የውጪ ዜጎችን በነጻ መልቀቋ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በብድርና በልገሳ ያገኘችው ገንዘብ በስርዓቱ ባይዘረፍ ኖሮ በወሬ ሳይሆን በተግባር የተረጋገጠ ልማት ይታይ ነበር ተባለ እና  ሌሎችም  ዜናዎች አሉን

No comments:

Post a Comment