Saturday, May 14, 2016

የሕወሓት ደህንነት ከዚህ ቀደም በግንቦት 7 ስም የታሰሩ ሰዎችን እንደ አዲስ እንደተያዙ በማስመሰል ፕሮፓጋንዳ ሊሰራ መሆኑ ተጋለጠ



) አርበኞች ግንቦት 7 በአርባምንጭ ከተማ በወሰድኩት እርምጃ 20 የሚሆኑ የመንግት ወታደሮችን ገደልኩ ሲል መንግስት ደግሞ በኡጋንዳ በኩል አድርገው በኬንያ አቋርጠው በደቡብ ክልል ውስጥ ጥቃት ሊያደርሱ የተዘጋጁ አሸባሪዎችን ይዣለሁ ሲል መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም:: ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከአሸባሪዎች ያዝኩት ብሎ በድረገጹ ያሳየው ፎቶ ግራፍ የአሜሪካ ወታደሮች ከዚህ ቀደም ሶሪያ ላይ የማረኩትን ፎቶ ግራፍ ነበር::
File Photo
እንደ ምንጮች ገለጻ ሕወሃት መራሹ መንግስት አሸባሪዎችን ይዣለሁ ይበል እንጂ.. ወታደሮቹን ከገደሉት የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ውስጥ 4ቱ ሕይወታቸው ከማለፉ ውጭ ሌሎቹ ተሰውረውበታል:: በዚህም የተነሳ ማስረጃ በማጣቱ እንደውም ከዚህ ቀደም በአርበኞች ግንቦት 7 ስም ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎችን እንደ አዲስ እስረኛ በማስመሰል ለማቅረብና በዚህ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ሊሰራ መሆኑ ተጋልጧል:: ቦታዎችን በማስጠናትና ከኤርትራ እንደተላኩ በማስመሰል የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎች ሊቀርቡ በዝግጅት ላይ ናቸው::
ምንጮቹ እንደሚሉት ከኤርትራ የተላክን ነን ብላችሁ እመኑ እየተባሉ ብዙዎቹ እየተገረፉ ሲሆን ይህን አምነው በቴሌቭዥን ከቀረቡ ሊፈቱ እንደሚችሉ አለበለዚያ ግን አሰቃይተው እንደሚገድሏቸው እንደተነገራቸው ምንጮች ገልጸዋል::

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ድርጅታቸው በአርባምንጭ በወሰደው ጥቃት አባሎቻቸው የሕይወት ዋጋ እንደከፈሉ መግለጻቸውና ቁጥሩን ግን አለመናገራቸው ይታወሳል::

No comments:

Post a Comment