Monday, May 30, 2016

መኢአድ ከ”አንድነት” ጋር አድርጎት የነበረውን ስምምት አጸደቀ- የሚሊዮኖች ጽምጽ

መኢአድ ከ”አንድነት” ጋር አድርጎት የነበረውን ስምምት አጸደቀ- የሚሊዮኖች ጽምጽ
መኢአድ አዲስ አመራር መርጧል። የአንድነት ሴንትሪስት ፕሮግራም ፕሮግራሙ አድርጎ አጽድቋል፡
በምርጫ ቦርድ የፖለቲካና የደርጅቶች ጉዳይ ሃላፊ የሆኑት ወ/ሮ አክሊል እና አቶ ዮሴፍ የተባሉ የምርጫ ቦርድ ታዛቢ በተገኙበት መኢአድ ጠቃላላ ጉብዬውን ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2008 ዓ.ም አድርጓል።
ከአንድ አመት ተኩል በፊት መኢአድ አድርጎት በነበረው ጠቃላላ ጉባዬ በተፈጠሩ አለመስማማቶች ምንክያት ፓርቲው ገፍቶ ሊሄድ አለመቻሉ ይታወቃል። ለፓርቲው አንድነት እና ጥንካሬ ሲባል አቶ አበባው መሐሪ ራሳቸውን ለሊቀመንበርነት ምርጫ እጩ አድርገው ስላላቀረቡ፣ ጉብዬው ላበረከቱት አስተዋጾ ምስጋናውን አቅርቦ በክብር ሸኝቷቸዋል።
ጠቅላላ ጉብዬው የተጀመረው ምርጫ ቦርድ ኮረም መሙላቱን ካረጋገጠ በኋላ ሲሆን በአጠቃላይ ከሚያስፈለገው 300 አባላት ወደ 320 የሚሆኑ ጠቅላላ ጉብዬዉን ተካፍለዋል። ጠቅላላ ጉብዬው አዲስ የአመራር አባላትን ከመምረጥ በተጨማሪ ፣ የፕለቲካ ፕሮግራም እና የደርጅቱ ሕገ ደንብ ማሻሻያዎችን አድርጓል።
ከሁለት አመታት በፊት አንድነት እና መኢአድ ዉህደት ለመፈጸም ስምምነቶች አድርገው ሕግወ ወጥ በሆነ መልኩ ዉህደቱን ምርጫ ቦርድ ማጨናገፉ ይታወቃል። ያንን አሳዛኝ ክስተት በማስታወስ ፣ ከሰሜን ሸዋ ፣ ደብረ ብርሃን የመጡ ፣ አቶ ወርቁ ተገኑ የተባሉ ሰው፣ በስብሰባው ለተገኙ የምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች ፊት ምርጫ ቦርድን ኮንነዋል።
በወቅቱ በተደረገው ስምምነት የአንድነት ፓርቲ ሴንትሪስት ፕሮግራም የዉህዱ ፓርቲ ፕሮግራም እንዲሆን፣ የመኢአድ ሕግ ደንብ ደግሞ የዉህዱ ፓርቲ ደንብ እንዲሆን ነበር የተወሰነው። በዚያ መሰረት፣ አሁን የሚዋሃድ ኦፌሴላዊ የሆነ የ”አንድነት” ፓርቲ ባይኖርም፣ የመኢአድ ጠቃላላ ጉብዬ የአንድነት ፕሮግራም የመኢአድ ፕሮግራም እንዲሆን ወስኗል።
የየነበረዉን የመኢአድ ደንብ በማሻሻል የጠቅላላ ጉብዬውን አባላት ቁጥር ከ600 መቶ ወደ 334፣ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትን ቁጥር ከ105 ወደ 81 ዝቅ አደርጎታል።
ጠቃላላ ጉብዬው ባደረገው ምርጫ፣ አቶ አበባው መሐሪ ተክተው፣ በቅንጅት ጊዜ የላእላይ ምክር ቤት አባል የነበሩ፣ ከአንጋፋ የመኢአድ አመራር መካከል የሚቆጠሩት ዶር በዛብህ ደምሴ ተመርጠዋል።
በመምህርነት ያገለገሉ፣ ከፍተኛ ትምህርቶች በጀርመን እና በኮሪያ የወሰዱና የማስተርስ ዲግሪ ያላቸው፣ አቶ አሰፋ ሃብተወልድ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡ ሲሆን፣ የተዎሎጂ ምሩቅ የሆኑት አቶ ሙሉጌታ አበባ ደግሞ ም/ሊቀመንበር ሆነዋል። የሕግ ባለሞያ የሆኑትና ከስሜን ወሎ የመጡት አቶ አዳነ ጥላሁን የመኢአድ ዋና ጸሃፊ ሆነው ተመርጠዋል።
በተጨማሪም ጉብዬ 50 የላእላይ ምክር ቤት አባላትን መርጧል። ከ31 የአገሪቷ ዞኖች ፣ ዞኖችን ወከለው የመጡ አባላት፣ በመኢአድ ደንብ መሰረት በቀጥታ፣ በዞን ሃላፊነታቸው የላእላይ ምክር ቤት ናቸው። ባጠቃላይ ምክር ቤቱ 81 አባላት ይኖሩታል።
ዶር በዛብህ ደምሴ በሥራ አስፈጻሚ ዉስጥ የሚሰሩት ሌሎች አባላት መርጠው በምክር ቤቱ በቅርብ ያጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዶር በዛብህ ቀዳሚ ተግባራቸው በተለያዩ ምክንያት ከፓርቲው የተለዩትን ማሰባሰብ እንደሆነ የደረሰንዝ ዘገባ ይጠቁማል።
ከአንድነት ጋር የተደረጉ ስምምነቶች መኢአድ ማጽደቁ፣ በርካታ የቀድሞ የአንድነት አባላትና አመራሮች መኢአድን ይቀላቀላሉ ተብሎም ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment