Thursday, May 12, 2016

ወያኔ በላስ ቬጋስ ቅዱስ ምሕረት የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ላይ አዲስ ጥቃት ከፈተ

ወያኔ በውጭ የሚገኙ የተደራጁ የኢትዮጵያዊያንን ተቋማት ለመቆጣጠርና መጠቀሚያው ለማድረግ ካልቻለም ለማፈፍረስ ወይም ለማዳከም የነደፈው ዕቅድ አካል የሆነ አዲስ የጥቃት ዘመቻ በላስ ቬጋስ የቅዱስ ሚካኤል የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ውስጥ መጀመሩን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ወያኔ ቀደም ሲል ወደዚህ ደብር ውስጥ አሰርጎ ባስገባው ሲሳይ ኪዳኔ በተባለው የህ.ወ.ሃ.ት. ሰላይ አማካይነት በደብሩ ውስጥ ክፍፍልና ብጥብጥ ለማድረግ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎችን ጀምሯል። የላስ ቬጋስ ደብረ ምሕረት ቤተክርስቲያን ጠንካራ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ያሉበትና በውጭ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን (ሕጋዊው ሲኖዶስ) ስር ያለ መሆኑ በስፍራው የሚያንዣብቡ የወያኔ ተላላኪዎች ላይ ጥርስ ተነክሶበት የነበረና ጊዜ ሲጠበቅለት የነበረ መሆኑንን ተገልጾልናል። የደብሩ ምዕመናን ከሁለት ዓመታት በፊት የራሳቸው ሕንጻ ገዝተው በርካታ ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ማስመረቃቸው ይታወሳል።
የህወሃቱ ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ በደብሩ ውስጥ አንዳንድ ጥቃቅን ስራዎችን በነጻ እሰራለሁ በማለት አጭበርብሮ የተጠጋ ከመሆኑም በላይ አለችሎታውና አለዕውቀቱ የተለያዩ ስራዎች ላይ ገብቶ ለመፈትፈት ጥረት ሲያደርግም እንደነበር ተጠቁመናል። ግለሰቡ ወያኔን ይቃወማሉ ብሎ የሚገምታቸውን የደብሩን የቀድሞና የአሁን የሰበካ ጉባኤአባላትን ስም ለማጥፋትና እርስ በርስ ለማጋጨት የተለያዩ ደባዎችን ሲሸርብ የነበረ መሆኑና አሁን ግን መጋለጡ ታውቋል። ይህ ግለሰብ የማይመለከተው ጉዳይ ውስጥ ዘው ብሎ ለመግባትና የደብሩን መገልገያዎች በግል ቁጥጥር ስር ለማድረግ የተለያዩ ሙከራዎችን ሲያደርግ የነበረ ቢሆንም እንዳልተሳካለት ተገልጾልናል። ሲሳይ ኪዳኔ የሚሰነዝራቸውን ፍሬ ቢስ ሃሳቦችና መሰሪ ዕቅዶች ላይ ተቃውሞ የሚያቀርቡ አባላት ላይ የተለያዩ ስድቦችን እንደሚለጥፍባቸው ለምሳሌም “እብድ” “የአይምሮ በሽተኛ” እያለ እንደሚያዋርዳቸውና ምንም ዓይነት ግብ ረገብና ሥነምግባር የጎደለው ተራ ካድሬ ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።
ከደብሩ ውስጥ አወቆች በደረሰን ጥቆማ መሠረት የወያኔው ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ ዓላማ በዋናነት ያነጣጠረው በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ በመገኘት አዘውትረው አባታዊ ምክር የሚሰጡትንና ደብሩ አሁን ለደረሰበት እድገት ገንቢ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ብጹዕ አቡነ መቃሪዎስ ላይ እንደሆነ ታውቋል። አቡነ መቃሪዎስ የግንባር ስጋ በመሆን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ በዓለም ማዕዘናት በመዘዋወር ኢትዮጵያዊያን ላይ ወያኔ የሚያደርገውን ግድያ፣ እስር፣ማሰቃየትና ማሰደድ በማጋለጥ እንዲቆም የሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት ወያኔን እንቅልፍ እንደነሳው ይታወቃል። አቡነ መቃሪዎስ በሚሰሩት ስራዎች  “የዘመናችን አቡነ ጴጥሮስ” ተብለው ቢጠሩ የማይበዛባቸው መሆኑን የሚናገሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ አገሮች ውስጥ እንደሚገኙ ይታወቃል። በተለይም ከአንድ ዓመት በፊት ሊቢያ ውስጥ ስለታረዱት ኢትዮጵያውያን በዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ተገኝተው ያሰሙት ታሪካዊ ንግግር ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ኢትዮጵያ በፋሽት ኢጣሊያ በተወረረችበት ጊዜ ”ሊግ ኦፍ ኔሽንስ” ጄኔቫ ውስጥ ተገኝተው እ.አ.አ. ሰኔ 1936 ካደረጉት ንግግር ጋር የሚያመሳስሉ በርካቶች ናችው። ከዚህም በተጨማሪ አቡነ መቃሪዎስ የዋልድባ ገዳም ውስጥ ወያኔ የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑ መናንያንና ገዳማዊያንን መኖሪያ ቤቶችና መቃብሮችን በግሬደር ሲያፈርስና ሲጠርግ በግምባር ቀደም ያወገዙና የተቃወሙ ለእውነትና ለፍትፍ ግምባራቸውን የማያጥፉ እውነተኛ የሐይማኖት አባት ናቸው።
እኝህ ታላቅ አባት ለአገራችን ኢትዮጵያ የሚሰሩትን ታላላቅ ስራዎችን ለማኮላሸትና ተሸማቀው እንዲቀመጡ ለማድረግ ክብራቸውንና ስብዕናቸውን የሚያጎድፍ የተለያየ የፕሮፓጋንዳ ስራዎችን ወያኔ በተደጋጋሚ ሲያደርግ እንደነበር የሚዘነጋ አይደለም። የዚህ መሰሪ እንቅስቃሴ ቀጣይ የሆነ አዲሲ ጥቃት በላስ ቬጋሱ ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ አማካይነት ወያኔ በአቡነ መቃሪዎስ ላይ ከፍቷል። የወያኔው ሰላይ ሲሳይ ኪዳኔ በአቡነ መቃሪዎስ ላይ የከረረ ጥላቻ ያለው ከመሆኑም በላይ እሳችው ላይ የተለያየ የሃሰት ወሬ ማስወራትና የስም ማጥፋት ዘመቻ ስልክ በመደወልና ለተለያዩ ሰዎች በግምባር በመገኘት ሲቀሰቅስ እንደነበር ተገልጾልናል። በዚህ ሳምንት ውስጥ ሲሳይ ኪዳኔ በአቡነ መቃሪዎስና በሌሎችም የቀድሞና የአሁን የቦርድ አባላት ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻ በጽሁፍ ማውጣቱንና ይህንንም አስመልክቶ ሪፖርት ለማድረግ በነገው ዕለት ወደ አዲስ አበባ እንደሚሄድ ጥቆማ ደርሶናል። ይህ ግለሰብ ሲለሚያደርገው አኩይ እንቅስቃሴና በአካባቢው ያሉ ኢትዮጵያዊያን ማድረግ ሰለሚገባቸው ጥንቃቄ ተጨማሪ መረጃ አሰባስበን እናወጣለን።

No comments:

Post a Comment