Sunday, May 15, 2016

ስርዓቱ የገማው ከአናቱ ነው::አናቱ ካልተመታ አምባገነንና ሌባ መፈልፈሉን አያቆምም::


ስርዓቱ የገማው ከአናቱ ነው::አናቱ ካልተመታ አምባገነንና ሌባ መፈልፈሉን አያቆምም::
 
“በልቼ ልሙት” የማለት ፈሊጥ፤ ተጠናውቶናል፡፡ የሸጥኩትን፣ የሸቀልኩትን በተለያየ ስም ያስቀመጥኩትን፣ ንብረትና ገንዘብ ብታሰርም እየበላሁ እኖራለሁ የሚለው አስተሳሰብ በሰፊው የተንሰራፋ ይመስላል፡፡ ገንዘብን በሺዎች መቁጠር ከቀረ ሰንብቷል፡፡
እርስ በርስ የመበላላት ባህል የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡ ከታሪክ እስከ ዛሬ፡፡ ወይ በፖለቲካ ሽኩቻ፣ ወይ በኢኮኖሚ ድቀት አሳቻ፣ ወይ በባህል ልምሻ ዛቻ፣ ወይ በሶሻል ቀውስ ውድቀት አቻ፤ …አገር መበላላትን መቀበል ከጀመረችና ካመነች ቆይታለች፡፡ አያሌ የፖለቲካ ድርጅቶችን አይታለች፡፡
አስገራሚው ነገራችን፤ ትላንት የተበላውን ዛሬ በቦታው የተቀመጠው ጠንቅቆ ለማስተዋል አለመቻሉ! “የማስጠንቀቂያውን ደወል” እንኳን ሳያይ፣ ያለፈውን መራገምና ራሱን መልዐክ ማድረግ፣ ነው ፈሊጡ፡፡ አልፎም ተፈጥሮዬ ነው እስከማለት ደርሶ ወንበሩን ሙጥኝ ማለቱ፡፡
ቀጥሎም በራሱ ጊዜ “አወዳደቄን አሳምርልኝ!” ሳይል የቀደመው ባለስልጣን በወደቀበት መንገድ መንኮታኮቱ ነው፡፡ ስለ ምን አንዱ ካንዱ አይማርም? አካሄዱንስ ስለ ምን አይለውጥም? ኢ-ፍትሐዊነትን፣ ኢ-ዲሞክራሲያዊነትን፣ ሙስናን እንቋቋማለን ተብሎ በተነገረ ማስትግ፣ እዚያው ጥፋት ውስጥ ተዘፍቆ መገኘት እጅግ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን እጅግ አናዳጅም ነው፡፡
በተለይ ስለመልካም አስተዳደር መበላሸት በሰፊው እየተወራ፣ እዚያው ብልሹነት ማጥ ውስጥ በፊት ለፊት ተውጠው የሚታዩ የበላይ ኃላፊዎች ለሀገርም ለህዝብም ጠንቅ መሆናቸው አያጠያይቅም፡፡ መነሳትም አለባቸው፡፡ ህዝብ በኃላፊነት በሰጣቸው ቦታ ላይ ነውና ምዝበራውን ያካሄዱት፣ በከፍተኛ ደረጃ ነው መጠየቅ ያለባቸው፡፡የመጀመሪያው የሰንሰለት (Network) ጉዳይ ሲሆን፤ ሁለተኛው አንቱ የተባሉ ሰዎች ተጠያቂ ያለመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ ‪#‎ምንልክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.
1

No comments:

Post a Comment