Monday, May 16, 2016

የዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ቀብር ሥነስርዓት ነገ ይፈጸማል

የዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ የቀብር ስነ ስርዓት ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ይፈፀማል፡፡
አንጋፋው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ አባት ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬን ቀብር ለማስፈፀም የተቋቋመው ኮሚቴ የቀብር ስነስርአቱ በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያን ነገ ማክሰኞ ግንቦት 9 ቀን 2008 ዓ.ም. ከቀኑ 7 ሰዓት እንደሚፈፀም አስታወቀ፡፡ በ80 አመታቸው እሁድ ግንቦት 7 ቀን 2008 ከምሽቱ 1 ሰዓት ላይ ካሳንችስ ቶታል አጠገብ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ዶ/ር ወልደመስቀል አስከሬን በአሁኑ ወቅት ቤተዛታ ሆስፒታል ይገኛል፡፡ዶክተሩ ባጋጠማቸው ስትሮክ የተነሳ ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ሶስቴ ቀዶ ጥገና የተደረገላቸው ሲሆን ለህልፈት የዳረጋቸውም ስትሮክ እንደሆነ ከምንጮች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ህመሙ ከገጠማቸው በኋላ መናገርና መንቀሳቀስ ሁሉ አቅቷቸው እንደነበር የገለፁ ምንጮች ሁለት ነርሶች 24 ሰዓት ሙሉ ይንከባከቧቸው እንደነበርም ነግረውናል፡፡

No comments:

Post a Comment