Monday, May 30, 2016

የሕወሓት መንግስት “እንቁልልጬ” የተሰኘ ዶክመንታሪ ፊልም በኤርትራ መንግስት ላይ ለቀቀ | ለምን በፊልሙ ላይ ግንቦት 7ን መጥራት አልፈለገም?

አርበኞች ግንቦት 7 በአርባምንጭ 20 የመንግስት ወታደሮችን ገደልኩ ባለበት ማግስት ዘ-ሐበሻ ሕወሓት መራሹ መንግስት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ የራሱን ሰዎች አስጠንቶ ዶኩመንታሪ ፊልም እየሰራ መሆኑን ምንጮቿን ጠቅሳ መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ የግንቦት 20 ማግስት የአርበኞች ግንቦት 7ን ስም ሳያነሳ በኤርትራ መንግስት ላይ ዶክመንታሪ ቪዲዮ በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ለቆታል:: ለግንዛቤና አስተያየት ይሰጡበት ዘንድ አቅርበነዋል::
ይህን ፊልም ከማየታችሁ በፊት ከዚህ ቀደም ትግራይ ሆቴልን አፈነዱ ተብለው በቴሌቭዥን የታዩትን እና አፈንድተናል ብለው የተናገሩትን የ’ኦነግ አባላት’ ተብለው በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ታይተው በኋላም ተስፋዬ ገብረአብ ደቡብ አፍሪካ ሲሰደድ እነዚህን ወገኖች እዛው አገኘኋቸው ማለቱን ያስታውሷል::
የሚገርመው በቪዲዮው ላይ ተያዙ ተብለው የቀረቡት የጺማቸው አቆራረጥ እስረኛም አያስመስላቸውም። አንዱ ደግሞ “[መያዛችንን] ባውቅ ኖሮ እዚህ ውስጥ አልገባም ነበር” እያለ ድራማው ድራማ መሆኑን ይነግረናል::
በነገራችን ላይ በዚህ ዶክመንታሪ ፊልም ላይ መንግስት የአርበኞች ግንቦት 7 ለአርባ ምንጩ ጥቃት ኃላፊነቱን ወስዶ እያለ ለምን የግንባሩን ስም ለምን መጥራት አልፈለገም?

No comments:

Post a Comment