Friday, May 27, 2016

በምስራቅ ሐረርጌ ቆቦ ከተማ የሕዝብ ቁጣ በአደባባይ ተሰማ – ነቀምት ከተማ በአጋዚ ጦር ተከባለች

(ዘ-ሐበሻ) ጋብ ብሎ የነበረውና በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች ሲደረግ የነበረው የሕዝብ ቁጣ ሰሞኑን እየተቀጣጠለ ሲሆን ዛሬ ጠዋት ደግሞ በምስራቅ ሐረርጌ ቆቦ ከተማ ሕዝብ ተቃውሞን ለማሰማት አደባባይ ወጣ::
በቆቦ በተደረገው ተቃውሞ ሕዝቡ የኦህ ዴድ/ኢህአዴግ አስተዳደርን ክፉኛ ሲቃወም የነበ
ረ ሲሆን በዚህ ተቃውሞ በአብዛኛው የተሳተፉት ወጣቶች እና ሴቶች እንደነበሩም የአካባቢው የዜና ምንጮች አስታውቀዋል::
ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር ተያያዞ በተነሳውና ጋብ ብሎ ቆይቶ እንደገና ባገረሸው በዚሁ ተቃውሞ ፌደራል ፖሊሶች እንዲህ ያለውን ሰላማዊ የሕዝብ ቁጣ ለማስቆም ጥይት ከመተኮስ እስከመግደል ያለፈ እርምጃ እንዲወስዱ ት ዕዛዝ መተላለፉን ዘሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘግቧ አይዘነጋም::
በምስራቅ ሐረርጌ የተደረገውን ሕዝባዊ ቁጣ ፌደራል ፖሊስ እርምጃ የወሰደ መሆኑ ሲታወቅ እስካሁን የተጎዱ ሰዎች ዘ-ሐበሻ እንዳሉ ለማረጋገጥ ሞክራ አልተሳካላትም::
በሌላ በኩል የአጋዚ ጦር የነቀምቴን አደባባዮች እንደወረረው ከስፍራው የመጡ መረጃዎች ጠቁመዋል:: ሰር ዓቱ ከግምቦት 20 በዓል ጋር በተያያዘ ሕዝባዊ አመጽ ይነሳል በሚል ሕዝቡን ለማሸበር ጠመንጃ የታጠቁ በርካታ ወታደሮችን በየአደባባዩ ያሰማራ ሲሆን ከተማዋ በውጥረት ውስጥ እንደምትገኝ የደረሰን መረጃ ያስረዳል::

No comments:

Post a Comment