Monday, May 16, 2016

የስኳር ፕሮጀክቶቹ ጡዘት እና የአርባምንጭ አከባቢ ግጭት የወለደው አዲስ ግርግር


የስኳር ፕሮጀክቶቹ ጡዘት እና የአርባምንጭ አከባቢ ግጭት የወለደው አዲስ ግርግር
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎TPLF‬ ‪#‎ANDM‬ ‪#‎ብኣዴን‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬ ‪#‎SugerFactory‬
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የውሸት ካምፓኒው የሕወሓት አገዛዝ የደህንነት እና ወታደራዊ ተቋማት ባለስልጣናት አከባቢ ከበድ ያሉ ምስጢራዊ መረጃዎችን ለመያዝ ቢሞከርም በፍጹም እያፈተለከ መቸገራቸውን እና በሃገሪቱ ለሚነሱ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ አመጾች የኢሕኣዴግ አንዱ ቅርንጫፍ የሆነው የብኣዴን ካድሬዎችን ድምጻቸውን አጥፍተው ሊያጠፉን ነው በሚል በከባድ አትኩሮት ውስጥ እንዲዋልል ያደረጉት ሲሆን ብኣዴን የሕወሓትን የበላይነት እየተቅለሰለሰ ሊነጥቅ ነው የሚሉ ሕወሓታውያን እየበዙ መምጣታቸውን ከመጠቆሙም አልፎ ሕወሓት እንዲከስም በአገዛዙ ውስጥ የአማራው ሚና እየጨመረ ነው በማለት መነጫነጭ ጀምረዋል::
በሕወሓት አገዛዝ ሚዲያዎች የኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል የሚወጡ የተዛቡ እና የውሸት ምስሎች እና ዘገባዎች ከሕወሓት የደህንነት ቢሮ ተዘጋጅተው እንደሚላኩና በብኣዴን ሰዎችም ይህ ያልበሰለ ውሸት በደንብ ስለተደረሰበት የሕወሓትን ቅጥፈን በማጋለጥ ረገድ በመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ የሚሰሩ የብኣዴን ልጆች ላይ ከንፈር ሲነከስ የአማራ መገናኛ ብዙሃን ካለፍርሃት እያመጣቸው የሚገኙ ሕዝባዊ ጉዳዮች ለፌዴራል መንግስቱ የሕወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ጋሬጣ እና ስጋት እንደፈጠሩ በደህንነት ተቋማት በኩል ሕወሓቶች እየጮሑ እንደሚገኙ ተሰምቷል::ባለፈው ሳምንት በአርባምንጭ የተነሳውና የቴፒ ወጣቶች የትግል አካል ሊሆን ይችላል ተብሎ የታሰበው የግንቦት ሰባት ፓርቲ ሃላፊነቱ የኔ ነው ያለበት በሌሎች ዘንድ ሕዝባዊ አመጽ እንደሆነ የሚነገርለት የሕወሓት ዘረኛ ካድረዎች የኤርትራን መንግስት የወነጀሉበት ሕወሓት-ሰራሽ ይህ ግጭት ከቀናት በኋላ እዛም እዛም ሲጠቋቆምበት የነበረውን ጣቶቹ ወደ ብኣዴን ካድሬዎች ማዞሩ በሕወሓት እና ብኣዴን ውስጥ የቀድሞው አካል የሆነና ከበፊቱ ሾኬ በተሻለ መልኩ አዲስ ያለመተማመን መንፈስ እየሰረጸ እንደሆን ያሳያል::ጥቂት ሆዳም የሆኑ የፓርቲ አመራሮችን ቀብረን የብኣዴንን ሕልውና እናረጋግጣለን የሚሉ የብኣዴን ካድሬዎች ምንም እንደማያውቁ በመምሰል እየተቅለሰለሱ ሊፈጁን ነው በትግራይ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ሊታወጅ ነው ምናምን እያሉ የሚቀባጥሩ የሕወሓት ካድሬዎች እና ተባባሪዎቻቸው እያፏጩ ይገኛሉ::
ከፖለቲካው ግርግር ጎን ለጎን ይህን ሰሞን ከስኳር ፕሮጀክቱ ጋር በተያያዘ የብኣዴን ሰዎች ደህንነቱን እና መከላከያውን መቆጣጠር ቢያቅታቸው ባለስልጣኖቻችንን እየወነጀሉ ነው ሲሉ አሁንም የሕወሓት ሰዎች አማረው ያለቅሳሉ::በፍጹም የማይሳካ እና ለዘረፋ ብቻ ተብሎ የተቋቋመው የስኳር ፕሮጀችት አንዱም ሳይሰራ ሃገሪቷን ለከፍተኛ እዳ እንዳጋለጣትና የጥቂት ሕወሓት ባለስልጣናትን ኪስ እንዳደለበ እየታወቀ የሕወሓት አናት የሆኑ በሰሩት ከባድ ጸረ ሃገር ወንጀል ራሳቸውን ለመደበቅ ካድሬዎቻቸውን በማሰማራት የብኣዴን ሰዎችን ለመብላት አሰፍስፈው ይገኛሉ::በከፍተኛ ሙስና የሚዘፈቁት ሕወሓቶች መሆናቸው እየታወቀ የሚታሰሩ እና የሚንገላቱ ግን የብኣዴን አማሮች እንደሆኑ ካሁን ቀደም የታዩ ተሞክሮዎች ምስክሮች ናቸው::አሁንም በተዘዋዋሪ ይህን ለመድገም ሕወሓቶች እየተሯሯጡ ነው::
ሕወሓት በስልጣን ላይ እንዲቆይ የሚሹ ተቃዋሚ መሰል አሾክሻኪዎች ሳይቀር ለለውጥ የሚደረገውን የፖለቲካ እና የኢኮኒሚ ትግል አፈር ለማስገባት ከሌቦች እና ከገዳዮች ጎን ቆመው ሲያፏጩ ማየት ያሳፍራል::የመከላከያ ኢንዱስትሪ(ሜቲክ)እና አመራሮች የሕወሓት ጄኔራሎች ቅርጥፍ አድርገው ለበሉት ገንዘብ የብኣዴን አባላት እንዲቀሉ እየተፈረደባቸው ይገኛል:: አርባምንጭ ላይ ለፈነዳው አመጽ በየጊዜው በስብሰባዎች የሚቀርቡ ጸረ ሕወሓት ሰዎች ሪፖርት የብኣዴን እጅ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል በሚል በሕወሓት መራሹ የደህንነት ተቋም ሪፖርት እየተዘጋጀለት ነው::የአርባምንጭ አመጽ እና የስኳር ፕሮጀክቶቹ ጡዘት የወለደው አዲስ ግርግር ወዴት እያመራ ይሆን ??? ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
Minilik Salsawi's photo.

No comments:

Post a Comment